
ይህ ሁሉ ለጠቅላልዩ ያልታያቸው ለምን ይሆን?!?

መስከረም አበራ
* በጣም ልብ ይነካል፤ ያማልም በሬው መውጫ አጥቶ ከእምቦጭ ጋር ይታገላል!
* ጉማሬው እምቦጭ እስከ አንገቱ አንቆ ይዞ መተንፈሻ አሳጥቶታል!
* ወፏ ሁልጊዜ የምትንሳፈፍበት ሐይቅ በአረም ተወሮ እምቦጭ ላይ አርፋለች!
ጣና ቢደርቅ ከገዳማቶች ባሻገር የውሐ ውስጥ የአሳ ዝርያዎችን፣ ጉማሬዎችንና ብርቅዬ አዋፋትን እንዲሁም መድኃኒት የሚሆኑ ዕፅዋትን ጭምር ነው የምናጠው። ይህ ሁሉ ለጠቅላልዩ ያልታያቸው ለምን ይሆን?!?
ጠ/ሚ አብይ አንድ ስራ ሲይዙ አምነውበት፣ በእምነታቸው ጉልበት እስከ መወሰድ በሚያደርስ እልህ እንደሆነ በቤተመንግስቱ ፕሮጀክት፣አሁን ደግሞ ዛፍለመትከል በሚያደርጉት ጥረት አያለሁ።
እንዲህ በሞት ሽረት አይነት በጭካኔ የሚሰሯቸውን ስራዎች የሚሰሩት ደግሞ የሃገራችንን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት ዋናውን ቋጠሮ ያገኙ በሚመስሏቸውነገሮች ይመስለኛል-የቤተ-በመንግስቱ ፕሮጀክት የታሪካችንን መራር ቁስል ማከም ፈልገዋል፣በዛፍ ተከላው ደግሞ ስማችንን ጥላሸት የቀባውን ድህነት ለመቀነስ የEcoglogyው ሚና ቀላል እንዳልሆነ ገብቷቸው ነው።
እኛ “ይህን አቆይተው ፀጥታውን፣ደህንነታችንን ቢያስከብሩ ምነው?” በምንልበት ሁኔታም እርሳቸው የችግራችን ዋና ቋጠሮ በመሰላቸው ነገር ላይ መግፋታቸውን ቀጥለዋል።በጠ/ሚው አስተዳደር ላይ በርካታ የሚያደናግሩኝ ነገሮች ቢኖሩም(አንዱ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ላይ ያለው አቋም ነው) ሃገርን ያራምዳል ብለው ባሰቡት ነገር ላይ ለሚደክሙት ድካም ትልቅ ክብር አለኝ።ለምን ዛፍ ተከሉ ብዬ የምናገረው አማራሪነት የለኝም!
