>

የ “ደፋሪና ተደፋሪዎቹ” ድንገቴ ግሪሳ ዜና ...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የ “ደፋሪና ተደፋሪዎቹ” ድንገቴ ግሪሳ ዜና …!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

*ዛሬ  ለምን በዚህ ደረጃ ማስጮህ ተፈለገ???
 
* ማፈሪያ አርቲስቶቻችንስ አንዱ መምህር ተብዬ ከ20 በላይ ወንድ ህጻናትን ግበረ-ሰዶም ፈጽሞባቸው ፍርድ ቤት በነፃ ሲለቀው የት ነበራችሁ? 
 
በአዲስ አበባ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ምን ሊሠራ እንደታቀደና ምን ዓይነት ሴቶች ተመርጠው እንደገቡ መመርመሩ አይከፋም?!?
 
የፌስቡክ መንደር ሰሞኑን “የኢትዮጵያ አባቶች ልጆቻቸውን ደፈሩ” በምትል ጩኸቷ ከፍየሏ ሞት በላይ እሪሪ ያለ ጩኸት ያለቅጥ ከፍ ብሎ ሲለፈፍባት ከርሟል። እኔም የዜናውን ያለልክ መጮህ ሰምቼ ቀጣዩን ምን ይሆን ብዬ ጆሮዬን አጥቤ በጉጉት መጠባበቅ ዠመርኩ። ብጠብቅ፣ ብጠብቅ ወፍ የለም። ብቻ የእኛ አርቲስቶች እየተቅለሰለሱ ተራ በተራ እየወጡ ምንጩ የማይታወቀውን ዜና እንደጉድ አስውበው የህዝቤን አንጀት እየበሉ ያንቆረቁሩታል።
•••
ጭራሽ የሆነች ትንሽዬ ልጅ ነጭ ቬሎ አልብሰው ቀይ ቀለም ከኋላዋ ከቀሚሷ ላይ አፍስሰው ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ። ወንድ ህጻናት ተደፈሩ ብለው ኃዘን ተቀምጠው ሲያበቁ በድንኳናቸው መሃል የሰቀሉት የሟች ፎቶ ግን  የሴት ምስል ያለበት መሆኑ ግራ ያጋባል። ወንድ ልጅ ተደፈረ ብሎ የሴት ፎቶ ለጥፎ ማልቀስ ምን ይባላል? እውነት ነው ሴት ልጅ በየትኛውም ዕድሜ ክልል ውስጥ ብትገኝ ተደፈረች ነው የሚባለው። ድርጊቱም አረመኔያዊ ጾታዊ ጥቃት ነው። ለወንጀሉ ሌላም ስም የለውም። የተደፈሩት ወንድ ህጻናት ከሆኑ ግን ይሄ ጾታዊ ጥቃት አይባልም። ወንጀሉ ግብረሰዶማዊነት ላይ ነው የሚያርፈው። ወንድ ልጅ ሴትን ፆታዊ ጥቃት ይፈጽምባታል። ይሄ ተፈጥሮአዊ ወንጀል ነው። ወንድ ልጅ ወንድ ልጅን ሲደፍር ግን ጾታዊ ጥቃት በሚል መሸፈኛ ለማለፍ መሞከሩ ስህተት ነው። ወንጀሉ በቀጥታ መጠራት ያለበት ግብረሰዶም ተብሎ መሆን ነው ያለበት። ግብረሰዶም መፈጸሙን በመጥቀስ ነው በስሙ መጠራት ያለበት። ነገር ግን በዘመነ ህወሓትም ሆነ በዘመነ ብልጽግና ይህቺን ስም ግን ማን ደፍሮ ይጥራት? ኣ?
•••
ድርጊቱ አይደረግም ማለቴ አይደለም። አይሆንምም እያልኩም አይደለም። የእኔ ዋናው ችግሬ ደግሞ እንደ ዳንሳና ጩፋ ራዕይም ህልምም አለማየቴ ነው። ነገር ግን የሆነ ነገር ሳይና ስሰማ ትከሻዬን ይከብደኛል። ይሸክከኛልም። የሆነ ሰው እያወራልኝ እንኳ ሰውዬው ውሸት እንደሚያወራልኝ ቀልቤ ነው የሚነግረኝ። ሽግር እኮ ነው ዕዳ ነው እኮ የገባሁት። እናም ይህቺ የሆነ ቦታ ተቦክታ በአርቲስቶቻችን አስተናጋጅነት ለህዝብ ጆሮ የቀረበችዋን “የደፈሩ ተደፈሩ ” ዘፈንና ጩኸት በሰማሁም ጊዜ ድርጊቱ አይደረገም ብዬ ሳይሆን እንደው ግን አልዋጥልህ ብሎኝ ሳወጣ ሳወርድ ነበር የከረምኩት። ኋላ ላይ ግን ሚስተር ካምፕ የተባለ አንድ ፀረ ኢሉሚናቲ ክርስቲያን ወንድም የልቤን ሀሳብ ዘረገፈልኛ። ተባረክ አቦ። https://www.youtube.com/watch?v=ox98ZIK1qvQ&feature=share እናንተም እስቲ ነገርየዋን በደንብ መርምሯት። ያውም እነ መዓዛ አሸናፊ የሚመሩት የሉጢ መብት ተከራካሪ መንግሥት ነው አሁን ማንይሙት ለህፃናቱ አዝኖ እንዲህ የሚጮኸው? አትሞኙ። ይልቅ ወንድሜ መምህር ደረጄ ነጋሽን እህ ብላህ ስማው። ወደፊት መንግሥት ያቀደው ዕቅድ አለ ማለት ነው። በሚቀጥለው ዓመት የሆነች የታቀደች ዕቅድ አለች ማለት ነው። እናም ነቃ በል።
•••
በአዲስ አበባ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ምን ሊሠራ እንደታቀደና ምን ዓይነት ሴቶች ተመርጠው እንደገቡ መመርመሩም መልካም ነው። የሰይጣን ዕቅድ ይፈርሳል። ሰይጣንም ይወድቃል። ነውር ኢትዮጵያ ላይ የይልከሰከስ ይሆናል እንጂ ተረጋግቶ ለመኖር አይመቸውም። ፈፅሞም አይሳካም። ኦርቶዶክሳውያን የማታ ጸሎቱን አታቋርጡ። በየቤታችሁም ምከሩ። ጸሎታችሁን አጠንክራችሁ ከስግደት ከእንባ ጋር ወደ ፈጣሪ አቅርቡ። ወጥሩ አጋንንቱ ራሱ ጮሆ ከኢትዮጵያ ይወጣል።
•••
አሁን ይህ የደፈሩ ተደፈሩን ዜና ያለጊዜዋ ያመጡት በግልጽ የኢትዮጵያውያን አባቶችን ቅስም ለመስበር በመፈለግ ነው። በሚቀጥለው ዓመት ግበረሰዶማዊነትን በኢትዮጵያ ሕጋዊ አድርገው ለማስፋፋት የሚፈልጉ አካላት ቀድመው ኢትዮጵያዊ አባትነትን መስበር የፈለጉ ይመስላል። ኢትዮጵያውያን አባቶችን ለማነወር፣ ለማሸማቀቅ፣ ነውረኞች የነዙት መርዛማ ሴራም ነው ብዬ እገምታለሁ። ኢትዮጵያውያን አባቶችን በማሸማቀቅ እና አንገት በማስደፋት በሚቀጥለው ዓመት በመላ ኢትዮጵያ በየትምህርት ቤቶቹ ሊሰጥ ለታቀደው ድብቅ ሴራና የግብረ ሰዶማዊያን ዕቅድ ከወዲሁ አጃቢ ለመፈለግ የተሠራች ቀመር መሆኗንም መጠርጠር ብልህነት ነው። ወዳጄ ከአሁኑ ካልባነንን ወደፊት ፈጽሞ ዋጋ እንደሌለን ዕወቁ። ከምር መምህር ደረጄን ነጋሽን እህ ብላችሁ ስሙት። በህይወቱ ተወራርዶ በገባበት ታላቅ አርማጌዶን ጦርነት አጋዥ ሁኑት። አይዞኝ ደሬ። እናሸንፋለን። ደግሞ ለሉጢ።
•••
አርቲስቶቹ ግን ያሳፍራሉ። መረጃ ሳያጣሩ፣ መቼ ማን ተደፈረ ሳይሉ፣ እንደ በግ እንደ ከብት እንደበቀቀን እንዲሁ የተሰጣቸውን አጀንዳ ኪሎውን እንኳ ሳይመዝኑ የኢትዮጵያ አባቶችን ሁሉ ክብር አንድላይ ደፍጥጠው፣ የራሳቸውን አባቶች ክብር ሁሉ በዚህ መልኩ ለማዋረድ መጯጯኋቸው እጅግ አሳፋሪ ነው። ኧረ ለመሆኑ እናንተ እስከዛሬ የትአባታችሁ ነበራችሁ? አንዱ መምህር ተብዬ ከ20 በላይ ወንድ ህጻናትን ግበረሰዶም ፈጽሞባቸው ፍርድቤት በነፃ ሲለቀው የት ነበራችሁ? በየቤቱ ለዚሁ ተግባር በተቀጠሩ መምህራኖች አማካኝነት በየትምህርት ቤቱ በወንድ ህጻናት ላይ ይሄ ነውር ሲፈጸም የት ነበራችሁ?  በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ያሁሉ ክርክር ሲደረግ የት ነበራችሁ? እናም የተሰፈረ የሉጢዎች አጀንዳ ተሸክማችሁ እያመጣችሁ የኢትዮጵያ አባቶችን ክብር አታዋርዱ። ጠብቁ ደግሞ በዚህ ድብቅ አጀንዳ ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁላችሁንም እግዚአብሔር ያዋርዳችኋል።
•••
በኢትዮጵያ ሰዶማውያን ወንዶች የሉም እያልኩ አይደለም። ህፃናትን የሚደፍሩ ሰዶማውያንም የሉም እያልኩም አይደለም። ሞልተዋል። ነገር ግን አሁን እንዲህ ነጠላ ተዘቅዝቆ የተጮኸለትን ዜና እኔ ደግሞ አብሬ ከጯሂዎቹ ጋር እጮህ ዘንድ ተደፋሪዎቹም ደፋሪዎቹም የት አሉ? ካሉስ ለምን አይከሰሱም? ለምን ህዝብ እንዲያውቃቸው አይደረግም? ብዬ ለመጠየቅ እገደዳለሁ። ኣ! አሁን ማን ይሙት መንግሥት ነው አዝኖ ግብረሰዶማውያንን የሚያሳየን? ስሙን ራሱ መች ይጠራዋል? ሰዶማውያንን መቼ በስማቸው ይጠራል። የህጻናት መደፈር በሚል ጥቅል ካርቶን ውስጥ ጠቅልሎ ይጠራልኛል እንጂ። ፐ አትቀልዱ። እናም ወዳጆቼ በልክ ነገሩን መርምሩ። በነጭ ቬሎ ላይ ቀለም የተደፋበት ነጭ ቀሚስ የለበሰች ህጻን ፎቶ እያለጠፋችሁ አትበጥረቁ። ልክ እንደዚያው ወንድ ግብረሰዶም ተፈጸመበት ያላችሁትንም አሳዩን። ኢትዮጵያ አባታዊ ሀገር ናት። የአባቶችን ክብር የሚዘከርባት ሀገር ናት። አባትነትን አታርክሱ። ኢትዮጵያዊ አባትነት ረቂቅ ነው። ቅዱስ ነው። ልዩም ነው። ኢትዮጵያዊ አባትነት በተራ ርኩሰት የሚናድም አይደለም።
•••
አዎ እርግጥ ነው ህጻናት ሴቶችን ያለ ዕድሜያቸው መዳር አለ። እሱን ማስቆም አንድ ነገር ነው። ማኅበረሰቡን ማንቃት አንድ ነገር ነው። ደግሞስ ህፃናትን የሚደፍሩ አረመኔዎችን ፖሊስ ለምን አይከስም? ፍርድቤትስ ለምን አይፈርድም? መገናኛ ብዙሃንስ የግብረሰዶም ደፋሪ ወንዶችን ፎቶ፣ ቪድዮ ለምን አያሳዩንም? እስቲ አንተ አሁን ይሄን የምታነብ አንባቢ አባትህ ይደፍርሃል? ታዲያስ የአንተ አባት እንዲህ ባለ ወራዳ ተግባር ላይ የማይሳተፍ ከሆነ የሌላውንስ አባት በምን ሞራልህ ነው በጅምላ የምትከሰው? ኣ ? ወንጀለኞች የሉም እያልኩ ግን አይደለም። ወንጀለኞች ቢኖሩም የዐቢይ መንግሥት ለፍርድ አያቀርባቸውም ነው እያልኩህ ያለሁት። ይኸው ነው።
•••
ጥቂት ራሳቸው ሉጢ የሆኑ ሰዎች ነገሩን አጩኸው ምስኪን ንፁሐን አርቲስቶችንም በስሜት ነድተው ጉዳዩንም ሳይመረምሩ እንዳለ እንደወረደ ተቀብለው ሳያላምጡ አብረው ውጠው ኋላ ላይ መልሰው እኛ ላይ ይተፋሉ። መጀመሪያ መጠየቅ ማንን ገደለ? ማነው የደፈረው? ማነውስ የተደፈረው? ስንት ሰው? መቼና የት? ብሎ መጠየቅ። ከዚያ ወጥቶ መፎከር፣ ማቅራራትም ይቻላል። አሁን አዳሜ እያንዳንድሽ ብትጠየቂ አንድሽም መልስ የለሽም። ሚዲያ ላይ ሰምቼ ነው የምትዪው። ወሬያም። እስቲ እነዚህ ደፋሪ የተባሉ አባቶችን መንግሥትም አርቲስቶችም፣ መዓዛ አሸናፊም ያሳዩን። እነ እገሌ ናቸው ይበሉንና በአደባባይ እንፍረድባቸው። መፍረዱ ይቅር መንግሥት እስቲ ወንድ ደፋሪዎችን በድፍረት በስማቸው ግብረሰዶማውያን ብሎ ይጥራቸው። እስቲ ወንድ ነው በስማቸው ይጥራቸው። ጾታዊ ጥቃት እያለ ለመሸወድ አይሞክር። ይሄ ጾታዊ ጥቃት አይደለም። ግብረሰዶማዊነት ነው። ጌይ፣ ሉጢነት ነው። ወንጀልም፣ ነውርም፣ ኃጢአትም ነው። ህጻን ወንዶችን ደፍሮ ጾታዊ ጥቃት የሚል ካባ ማልበስ ነውር ነው።
•••
እናም መንግሥት ለሚቀጥለው ዓመት የሆነ ያቀደው ዕቅድ ስላለ ነው አስቀድሞ የኢትዮጵያ አባቶች እንዲጠሉ እያደረገ ያለው በሚለው በሚስተር ካምፕና በመምህር ደረጄ ነጋሽ ኃሳብ እኔም እስማማለሁ። በሚቀጥለው ዓመት በትምህርት ቤት ሊሰጥ ላቀደው የሥነ ጾታ የግብረ ሰዶም ትምህርት ከወዲሁ ኢትዮጵያውያን አባቶች እንዳይቃወሙት ለማሸማቀቅ የተፈጠረችም ዘዴ ናት የምትመስለው የሚለውንም ጥርጣሬ እኔም እጠረጥራለሁ። እናም ንቃ ወገኔ።
•••
አሁን በዚህ ዘመን ያሉ ጥቂት የማይባሉ ወጣት ወንዶች በፊልምም፣ በገንዘብም በሱስም ሰዶማዊነትን እየተለማመዱ እንደሆነ ግልጽ ነው። እሱ አይካድም። የጎረምሳን፣ የጫታሙን፣ የሀሺሻሙን፣ የአምቡላሙን የእኔ ቤጤ ዘማዊውን ስህተት ለኢትዮጵያ አባቶች መስጠት፣ ኢትዮጵያውያን አባቶች ላይ መደፍደፍ ግን ፍፁም የሆነ ነውር ነው። ሥነ ሥርዓት አድርጊ። አንቺ አርቲስት ተብዬዋም በጅምላ አባቶችን፣ ወንዶችን ከመክሰስሽና በአደባባይ ለህጻናት አዛኝ መስለሽ ከማቅራራትሽ በፊት። መቼ? ማን? የት? ብለሽ ጠይቂ። ዝም ብሎ ከመለፋደድ በፊት ነገሩን መርምሪ። ድራማ አትስሪ፣ የፊልሙ ተባባሪም አትሁኚ።
•••
መምህር ደረጄ ነጋሽ እንዲህ ዓይነት ድርጊት በማውገዝ የተቃውሞ ሰልፍ ሲጠራ የከለከለው መንግሥት አይደለም እንዴ? አስገድዶ መድፈር አለ፣ እየበዛም ነው መንግሥት ሕጉን ያጥብቅ ሲል አርፈህ ተቀመጥ ብሎ ሰልፉን የከለከለው መንግሥት አይደለም እንዴ? የሃይማኖት አባቶችን ጁፒተር ሆቴል ድረስ ሄዶ በግብረ ሰዶማዊነት ላይ መግለጫ እንዳይሰጡ አፈር ከደቼ አስግጦ ከጋዜጠኞች ፊት አበሻቅጦ ያባረረው የአሁኑ የWHO ሊቀመንበር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አይደለም እንዴ? ደረጄ ነጋሽ በሚጠራው ፀረ ሰዶማውያን መግለጫና መርሐ ግብሮች ላይ የመንግሥት ሚዲያዎች እንዳይገኙ የሚያደርገው ራሱ መንግሥት አይደለም እንዴ? 17 የዐማራ ህጻናት ሴቶች ታፍነው ሲሰወሩ የዛሬዋ መዓዛ አሸናፊ የት ነበረች? እና ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው መንግሥት ሆዬ ወንጀሎቹን ሳያሳየን ወንጀሉ አለ ብሎ ማጮህ የፈለገው? ያውም የወንጀሉን ስም በግልጽ ሳይጠራ። ግብረሰዶም ሳይለው በፆታዊ ጥቃት ካባ ጠቅልሎ። እናም ንቃ ወገኔ !! የተሰጠህን ሁሉ ሳታላምጥ አትዋጥ። ሰምተሃል።
•••
ኢትዮጵያውያን አባቶች ኩራት ናቸው። ሞገስ ናቸው። ፍቅር ናቸው። ሃይማኖተኞች ናቸው። ይሄ ዓይነት ክብር ግን ይሄን ኢንተርኔት ሠራሹን መጤውን፣ ወጠጤውን፣ ቃሚውን፣ አጫሽ ሰካራሙን፣ የዝሙት ፊልም ሲመለከት የሚያድር የሚውለውን ኮተታም የእኔ ቢጤ ዘማዊ ፍንዳታ ኢትዮጵያን አሰዳቢ አባት ተብዬን ግን አይመለከትም። እሱ እንኳን ልጁን ተማሪዎቹን አይምርም። አባት እናቱንም አይምርም። ደግሞም የዘመኑ ሰዶማዊ ቀጪ ሕግም የለውም። እግዚአብሔር ይገስጽህ።
የኢሉሚናቲ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ
•••
#ማስታወሻ |~ በቀጣይ፦
•ፎርጅድ ንጉሥ፣
•ፎርጅድ ፓትርያርክ፣
•ፍርጅድ ጳጳስ፣
•ፎርጅድ የሴት ቄስ፣ እያመረተች እያስደመመችን ስላለችው ስለጎዣምና የጎዣም ዐማራ ጥቂት እተነፍሳለሁ። የጎዣም ዐማራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በዚህ መጠን ፈንጂ፣ ድጅኖ፣ ድማሚት ይዞ ይዞራል ብዬ መቼም አስቤ አላውቅም ነበር። የሆነው ሁሉ ግን እየሆነ ነው። በዚህ ዙሪያ በአጭሩ እተነፍሳለሁ። እስከዚያው ፦
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ሰኔ 3/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic