>

የዓለም የጤና ድርጅት የእንግሊዝ ተመራማሪዎች ለኮቪድ -19 ጽኑ ሕሙማን ላገኙት መድኃኒት እውቅና ሰጠ (ኢ.ዜ.አ)

የዓለም የጤና ድርጅት የእንግሊዝ ተመራማሪዎች ለኮቪድ -19 ጽኑ ሕሙማን ላገኙት መድኃኒት እውቅና ሰጠ

ኢ.ዜ.አ

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ ለመጀመርያ ግዜ “ህይወትን ሊያድን የሚችል መድሀኒት” ተገኝቷል!
ይህ “ዴክሳሜታሶን” የተባለ ርካሽ መድሀኒት አዲስ ግኝት ሳይሆን ለአመታት የተለያዩ ህመሞችን ለማከም ሲውል የቆየ እንደነበር ተዘግቧል፣ በበርካታ ሀገራትም ገበያ ላይ ይገኛል ተብሏል። መድሀኒቱ በተለይ ቬንትሌተር እና ኦክስጅን የሚጠቀሙ ፅኑ ህሙማን ላይ ከፍ ያለ ውጤት አሳይቷል ተብሎ ተገልጿል።
ይህን መድሀኒት ለቫይረሱ ህክምና ሊውል እንደሚችል በምርምር መገኘቱ “ትልቅ ስኬት” ተብሎ የተገለፀ ሲሆን መድሀኒቱን ቀደም ብሎ መጠቀም ቢቻል ኖሮ በአለም ዙርያ የበርካታ ሺህ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ይቻል ነበር ተብሏል።
የ 35 ፓውንድ (1,500 ብር) ዴክሳሜታሶን ህይወት ሊያድን ይችላል ብሎ ቢቢሲ የዘገበ ሲሆን ይህ በተለይ ለድሀ ሀገራት ትልቅ ተስፋ አለው ብሏል። ይሁንና መድሀኒቱ ሙሉ ለሙሉ ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች የመፈወስ አቅም እንደሌለው ይፋ የተደረገው ምርምር ያሳያል።
በኮሮናቫይረስ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል የተነገረለትን ዴክሳሜታሶን የተሰኘውን መድኃኒት በእንግሊዝ የኦክፎርድ ተመራማሪዎች ይፋ ተደርጓል።
ይሄን ተከትሎም ለተለያዩ መድኃኒቶች የእውቅናና የቅድመ እውቅና የሚሰጠው የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ-19 ምክንያት የሚሞቱ ጽኑ ሕመምተኞችን ሞት ለመቀነስ ተስፋ ሰጪ ነው ለተባለው መድኃኒት የመጀመሪያ ደረጃ እውቅና ሰጥቷል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ለእንግሊዝ መንግስት፣ ለሆስፒታሎች፣ ለኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና ለህሙማኑ ለዚህ መልካም ዜና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ዶክተር ቴድሮስ እንደተናገሩት መድኃኒቱ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።
መድኃኒቱ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሰበብ የጽኑ ሕሙማንን ሕይወት የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት ከመታደጉም በተጨማሪ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።
ለመድኃኒቱ እውቅና የሰጠው የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው ፤የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ላለባቸው እንዳልሆነ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል። በመድሀኒቱ ውጤት ተስፋ እያረግን ጥንቃቄያችንን እንቀጥል!
Filed in: Amharic