>

ኢትዮ 360 ምናላቸው ስማቸው ለአድማጮቹ መልዕክት አለው!

ለኢትዮ 360 ሚዲያ ተከታታዮች!! –

 

 

———ባለፈው አንድ አመት በመስራችነት እና በዋና ስራ አስኪያጅነት እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሙያ ያለምንም የሀላፊነት ደሞወዝ ያለመታከት ስሰራ መቆየቴ ይታወሳል:: ይህ ሚዲያ እዚህ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስም ትልቅ ዋጋ ከፍያለሁ:: ይህም ሆኖ ግን በስራየ ለመቀጠል የሚያስችል ሁኔታ ስለሌለ በትናትናው እለት ባካሄድነው ጠቅላላ ጉባዔ ስራየን የለቀቅሁ መሆኑን ለማስታወቅ እወዳለሁ:: ይህ በእንዲህ እያለ በሶሻል ሚዲያ 3 የቦርድ አባላት እና 3 ቴክኒሻኖች ለቀቁ እንዲሁም ተሰነጣጠቁ የሚለው ወሬ እና ዜና ሀሰት መሆኑን ለመግለፅ እፈልጋለሁ:: እስካሁን ድረስ “ለምጣዱ ሲባል ” እንዲሉ ብዙ ችግር እያጋጠመኝም ቢሆን ለሀገሬ እና በስቃይ ላይ ለሚገኘው ህዝባችን ስል ብዙ ዋጋ ከፍያለሁ:: በሀገራችን ያለው ሁኔታ እየተሻሻለ ካለመሄዱም በላይ ኢትዮጵያዊያን በጋራ የመስራት ችግር እንዳለብን ስላረጋገጥኩ ከዚህ በኃላ ወደ ግል ህይወቴ በማምራት ቀሪውን ዘመኔን ለማሳለፍ መወሰኔን እንድታውቁልኝ ለጠላትም ሆነ ለወዳጅ አስታውቃለሁ::

 

ምናላቸው ስማቸው የፌስ ቡክ ገጽ

Filed in: Amharic