>

ቄሮ በመላው ኢትዮጵያዊ ላይ ጦርነት አውጇል ! (አሌክስ አብርሃም)

ቄሮ በመላው ኢትዮጵያዊ ላይ ጦርነት አውጇል !

(አሌክስ አብርሃም)

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እሄንን አውቆ ራሱን ማዘጋጀት አለበት።
ቄሮ በመላው ኢትዮጵያዊ ላይ ጦርነት አውጇል !
(አሌክስ አብርሃም)
አቅመደካማ ሰዎችን በድንጋይ እና ገጀራ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፎ በመግደል ፣ሴቶችን በመድፈር እንዲሁም ህፃናትን ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከነህይታቸው በማቃጠል የሚታወቀው ‹‹ቄሮ የሽብር ቡድን ›› ከደይቃዎች በፊት በመላው ኢትዮጵያዊ ላይ ከሐምሌ 1 /2012 የሚጀምር ጦርነት አውጇል!!ይህ መግለጫ በፌስቡክ በፍጥነት እየተሰራጨ ያለና በማንኛውም የኦሮሞ አክቲቪስትም ሆነ የቄሮ ደጋፊዎች ማስተባበያ ያልተሰጠበት በመሆኑ እንዲሁም ቡድኑ እስካሁን እያደረገ ያለውም ድርጊት ከሞላ ጎደል አደርገዋለሁ ብሎ ከሚፎክርበት ጉዳይ ስለማይለይ ለጥንቃቄ ይህን ፅፊያለሁ፡፡
እንግዲህ በመግለጫው ባሰፈረው የሽብር ጥሪ መሰረት ወደአዲስ አበባ የተዘረጉ የኤሌክትሪክና የውሃ እንዲሁም ሌሎች የልማት አውታሮችን ማውደም ፣ ከፀጥታ አካላት የጦር መሳሪዎችን መዝረፍና የጦር መሳሪያ ልምድ ላላቸው አባሎቹ ማስታጠቅ ፣ በኦሮሚያ ክልል ካለቄሮ ፈቃድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ሰው መግደልና የምንግስት ተቋማትን ማፈራረስ ከሐምሌ 1 /2012 ጀምሮ እንደሚፈፅም በግልፅ እወቁልኝ ብሏል፡፡ይህንንም የማደርገው ‹‹ነፍጠኛ ስርዓትን ›› ለመደምሰስ ነው ብሏል፡፡ማንም ኢትዮጵዊ እንደሚያወቅ በዚህ ወቅት ነፍጠኛ ስርዓት የሚባል የለም ! ‹‹ነፍጠኛ ›› በሚል የኮድ ስም የሚጠሩት በተለይም የአማራ ብሔር ተወላጆችን መሆኑ ግልፅ ነው !
እንደሚታወቀው … ሰው መግደል ፣ የልማት አውታሮች ማውደም እና ከፀጥታ አካላት መሳሪያ በጉልበት ነጥቆ መታጠቅ በየትኛውም መስፈርት ሰላማዊ ትግል አይደለም ፡፡ በመሆኑም መላው ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊቱና ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር ፣እንዲሁም ተደራጅቶ አካባቢውን በመጠበቅ ይሄን ነፍሰ ገዳይ ቡድን በህጋዊና ህጋዊ መንገድ መከላከል ይጠበቅብታል !
በዚህ አጋጣሚ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ኦሮምኛ መናገር የማይችሉ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የዚህን ዱርየ ቡድን አስፀያፊ ድርጊት የማይደግፉ ብዙ ሚሊየን ኦሮሞዎች ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ታውቆ ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ ይህንን መግለጫም ለዓለም አቀፉ መሃበረሰብ በማድረስ ቀድሞ በአሸባሪነቱ ዓለም ያወቀውን የጥፋት ቡድን የበለጠ ማጋለጥ ነገ በየትኛውም ዓለም ተደብቀው በሰው ዘር ላይ እልቂት የሚጋብዙ አባላቱን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡
ገዳዩ ሲገድል ያላፈረውን ግድያውን ለመቃወም የምናፍርበት ምክንያት የለም !! 
Filed in: Amharic