>

በኦሮሚያ የተፈጸመው « የዘር ፍጅት አይደለም!» ለምትሉ ሰዎች የጄኖሳይድ ዎችን አስር መስፈርቶች እነሆ...!!! (ሉሉ ከበደ)

በኦሮሚያ የተፈጸመው « የዘር ፍጅት አይደለም!» ለምትሉ ሰዎች የጄኖሳይድ ዎችን አስር መስፈርቶች እነሆ…!!!

ሉሉ ከበደ

…..አንዳንድ ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን ተደጋጋሚ የዘር ጭፍጨፋ ፤የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንቅስቃሴ መሆኑን ለመቀበል ሲቸግራቸው አያለሁ ፡፡ የአማራውን ብሄረሰብና ኦርቶዶክስን  ኢላማ ያደረገ ፤ በፖሊሲ ደረጃ ተቀርጾ የተቀመጠ ዘርን የማጥፋት እቅድ መኖሩን ወያኔ ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ፤ ጀምሮ መጨረስ እያቃተው ጭፍጨፋው ሲቆም ሲቀጥል ከርሟል ፡፡ አሁን ደግሞ ኦህዴድ ስልጣኑን ከነጠቃቸው በኋላ በሚያስገርም ፍጥነት ስራው እንዲከናወን ተደጋጋሚ ሙከራ እየተደረገ ነው ፡፡ ፕሮጀክቱን አሁን በዋናነት ቄሮ በጃዋርና በነበቀለ ገርባ እየተመራ ተያይዞታል ። ኢትዮጵያ ውስጥ ጄኖሳይድ ሊፈጸም መሆኑ ያልገባችሁ ሰዎች አንድ ማገናዘቢያ ላቅርብላችሁ ፡፡

የእኛን እነሱ ፖለቲካ ድምር ውጤት  የሆነው የዘር ማጽዳቱ ዘመቻ..!?!


ፕሮፌሰር ግሬጎሪ የተባሉ ተመራማሪ  «ጄኖሳይድ ዋች»  የሚባለውን ድርጅት ይመራሉ ፡፡ አላማቸው በአለም ላይ እንደሩዋንዳ አይነት የዘር እልቂት እንዳይደገም መከላከል ነው ፡፡  ጄኖሳይድ እንደሚፈጸም የሚያረጋግጡ አስር ደረጃ መስፈርቶችን አጥንተው ተመራምረው ምልክቶቹ ብለው አስቀምጠዋል ፡፡ አቀርብላችኋለሁ ፡፡ ወዴት እንደምንሄድ የቱጋ እንደደረስን እራሳችሁ ንገሩኝ ፡፡
1 . CLASSIFICATION  ከመላ ህዝብ መካከል አንድን ወገን ኢላማ ለማድረግ ለይቶ ማስቀመጥ ። « እኛና እነሱ » የሚል መስመር አድምቆ መስራት :- በሀይማኖቱ ፤በብሄረሰቡ ፤ በቀለሙ ፤ ወዘተ… ምሳሌ ፤ ጀርመንና አይሁድ ፤ ሁቱና ቱትሲ ፤ በዚህ እርምጃ ላይ የሚጨመረው ነገር  ዜግነትን መንፈግ ፡፡ ዜግነትን መግፈፍ በሀገራችን ተግባር ላይ ከዋለ ሀያስምንተኛ አመቱን ይዟል ፡፡ ኢትዮጵያ ለአስር ብሄረሰቦች ተሰታለች ፡፡ ማለትም አስር ክልልሎች አሉ ፡፡ እያንዳንዱ ክልል የመሬቱ ባለቤት ክልልሉ የሚጠራበት ብሄረሰብ ነው ፡፡ ስለዚህ ሌላው ሁሉ የመምረጥም የመመረጥም መብት የለውም ፡፡ ሰባት ቤት ዘር ማንዘሩ እዚያው ተወልዶ አድጎ እያለ ፤ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተመደበለት ክልል ውጭ የዜግነት መብትና ነጻነት የለውም ፡፡ መሪውን መምረጥ አይችልም ላስተዳዳሪነትም ሊመረጥ አይችልም ፡፡ ኦሮሚያ ክልል እንደምሳሌ ብንወስድ ኦሮሞ ያልሆነ ሁሉ ቢማርም የስራ ቅድሚያ አይኖረውም ፡፡ በፖሊስ በልዩ ጦር ገብቶ የማገልገል መብት የለውም ፡፡ የሀገሩ ህዝብ በመታወቂያ ማንነቱ እንዲለይ ይደረጋል ።
2. SYMBOLIZATION  ለማጥፋት የተፈለገውን ህዝብ አጉልቶ ለማሳየት ወካይ ስም ወይም ምልክት መለጠፍ :- ለምሳሌ ለአማራው ህዝብ የተሰጠ ወካይ ቃል «ነፍጠኛ » ምልክት  ፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ልሙጥ ባንዲራ ፡፡ « ሚኒሊካውያን » ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ጽንፈኛ ዘረኛ አክራሪዎች ሁሉ ፤ ይህን ባንዲራ ሲያዩ ይንዘፈዘፋሉ ፡፡ ከፊሉ በፍርሀት ሊሆን ይችላል ከፊሉ በጥላቻ ። ለሩዋንዳ ቱትሲዎች የተሰጠ ቅጽል ስም « በረሮ » የሚል ወካይ ቃል ተለጥፎባቸው ነበር ፡፡ በመሰረቱ ቅጽል ስም መስጠት በራሱ መጥፎ ነገር አይደለም ፤ መጥፎ ትርጉም ሲፈጠርለት ነው እንጂ የሚከፋው ፡፡ ለምሳሌ  « ነፍጠኛ ፤ የኦሮሞ እናቶችን ጡት ቆረጠ» በትውልድ ውስጥ ጥላቻን ለማስረጽ ይህን የውሸት ታሪክ በመደበኛ ትምህርትነት ህጻናት በኦሮሚያ ውስጥ ይማሩታል ፡፡ ስምንተኛ ክፍል ፡፡ በተቆረጠ ጡት ሀውልት ስእል ተደግፎ ትምህርት ሆኗል ፡፡ «አማራ የእናትህን ጡት የሚቆርጥ ነው ፡፡» የሚል አስተሳሰብ በውስጣቸው ያደገ ልጆች ናቸው አሁን በቀላሉ ሰው ማረድ የቻሉት ፡፡
3 DISCRIMINATION  መድሎ ፤ የዘር ልዩነት ፡፡ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ ያለው ቡድን የጠላውን ማህበረሰብ መብት ይገድባል :- ሰባዊ መብት ይረግጣል ፡፡ የፖለቲካ መብት የኢኮኖሚ መብት ይረግጣል ፡፡  ለምሳሌ ከሰላሳ ሺህ በላይ የአማራ ክልል ተማሪዎች ከየክልሉ ዩኒቨርስቲዎች እንዲባረሩ ተደርገዋል ፡፡ መስፈርቱ አማራ መሆናቸው ብቻ ነው ፡፡ አስራሰባት ልጃገረዶች አንድ ወንድ ጨምሮ ታፍነው ወደደረሱበት አልታወቀም ፡፡  ሀያስምንት አመታት ሙሉ እጅግ ግዙፍ የሆነና ያላቋረጠ ከመንግስት ስራ የመፈናቀል እድል ገጥሞታል አማራ ፡፡ ከቤት ከንብረት ከተወለዱበት ቀዬ መፈናቀል  የአማራው ተወላጆ ች እጣፈንታ ሆኖ ነው ያለው ፡፡ እርግጥ የክልል መሬትን ለማስፋት ሲባል አንዱን ባንዱ ላይ እያስነሱ ሲማሌም ኦሮሞም ሌላውም ተፈናቅሏል ፡፡  ያ ግን እንደአማራው ከጅምሩ በእቅድ በፖሊሲ የተያዘ አይደለም ፡፡ የአማራው በደል ናዚ ጀርመን በአይሁዶች ላይ ካደረሰው በደል ጋር የሚመጣጠን የሚመሳሰል ነው ፡፡ አሜሪካኖች እስከ ሀምሳዎቹና ስልሳዎቹ በአሜሪካ ህንዶችና በጥቁሮች ላይ ይፈጽሙት የነበረው ግፍ ነው ፡፡ የኛን የተለየ  የሚያደርገው ነገር አለም በስልጣኔ መጥቃ ባለችበት በዛሬዋ ጀንበር እየተፈጸመ ያለ መሆኑ ነው ፡፡
4 DEHUMANIZATION ከሰውነት ተርታ ዝቅ ማድረግ ፡፡ አንዱ የህብረተሰብ ቡድን የሌላውን የህብረተሰብ ቡድን ሰብእዊ ሰውነት ያሳንሰዋል :- ለምሳሌ በኦሮሞ ጽንፈኞች ዘንድ ፤ አማራ « ሲዳ ሃማ » ይባላል ፡፡ « መጥፎ ድንጋይ » ማለት ነው ፡፡ « ኢቢዲ ሲዳማ ፤ አፉፈን ኒዳማ  » እየተባለም በጽንፈኛ  ኦሮሞዎች ይዘመር ነበር ፡፡ ትርጉሙ « አማራ ያቀጣጠለው እሳት ፤ እፍ ቢሉት ይጠፋል » እንደማለት ነው ፡፡  <ቆማጣ > ተብሎም ይለያል ። በእነ ህውሀት አይነት ጽንፈኛ ትግሬዎች ዘንድ ደግሞ አማራ « ሐድጊ » አህያ የሚል የጥላቻ መጠሪያም አለው ፡፡ ይህ ነው ሰውን ከሰብአዊ ሰውነት አሳንሶ ማቅረብ ማለት ፡፡ ኢላማ የተደረገው ክፍል እንደሰው እንዳይቆጠር መስራት ፡፡
5 ORGANAZATION ድርጅት። ጄኖዳይድ ምንጊዜም የተደራጀ ስራ ነው:- በ1983 አም  ወያኔና ኦነግ በበደኖ በአርባ ጉጉ አማሮችን እያረዱ ገደል ከጨመሩበት ጊዜ ጀምሮ አብይ አህመድ ተራውን ከወሰድበት ወር ጀምሮ እስከተፋፋመበት እስከ ትላንትናው ድረስ በአማራውና በኦርቶዶክስ ላይ የተወሰደው የማጽዳት እርምጃ የተደራጀና በእቅድ የተመራ ነው ። ቡራዩ ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ ሰለባዎቹ ያስረዱበትን ሁኔታ አስታውሱ « ከጥቃቱ በፊት ከየት እንደመጡ የማናውቃቸው ያካባቢው ያልሆኑ ወጣቶች በቡድን በቡድን ሆነው ቤት ተከራይተው ይኖሩ ነበር ፡፡ የሚናገሩት ኦሮሞኛ ብቻ ነው ፡፡ አብሮ አብሮ እየሆኑ ሲወጡ ሲገቡ ነው የምናያቸው … » እያሉ ከጭፍጨፋው የተረፉ ይናገሩ ነበር « እነዛው ልጆች ናቸው መጨረሽ ላይ እንደዚያ ያደረጉን » ጄኖሳይድ በሚፈጸምበት ሀገር ውስጥ  መንግስት በቀጥታ ሀላፊነት መውሰድ ስለማይፈልግ  ድርጊቱን የሚያስፈጽመው ኢመደበኛ በሆነ አደረጃጀት የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በመጠቀም ነው ፡፡ ጃዋር የሚመራው ቄሮ በበቂ  በጀትና ስንቅና ትጥቅ የተደራጀ አካል መሆኑን የሚጠራጠር ዜጋ ይኖራል ? በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው ዘር የማጽዳት ቅስቀሳና የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ዝም ብሎ ባጋጣሚ የሚደረግ ነው ? እስካሁን እንዳየነው ቄሮ ጭፍጨፋ ባካሄደባቸው ቦታዎች ሁሉ የሰሞኑን  መጠነሰፊ ጭፍጨፋ ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ሀይል በመጠቀም ከባህል መሳሪያ እስከዘመናዊ የጦር መሳሪያ በመታጠቅ ባልታሰበ ሰአትና ሁኔታ ድንገተና ወረራ በማድረግ ሁለገብ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በስም ዝርዝር እየተደገፉ ጭፍጨፋዎች ሲደረጉ ነው የተመለከትነው ….
 
በአርሲ ፤ በሻሽመኔ ፤ በዝዋይና ሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች የተፈጸመውን የዘር ፍጅት « ጄኖሳይድ አይደለም » ለሚሉ ሰዎች  «ጄኖሳይድ ዋች » የሚባለው ድርጅት ፤ ጄኖሳይድ ማለት ምን ጊዜ እንደሚሆን ለማሳየት ያወጣቸው አስር ደረጃዎች በመተዳደሪያ ደንቡ ተቀምጠዋል ፡፡ ሀገራችን ከተፈጸመው  ጭፍጨፋ  ጋር ለማነጻጸር እንዲረዳችሁ ፤ እርከኖች አቅርቤላችኋለሁ ፡፡ የትኛው ቦታ ላይ እንዳለን ለእራሳችሁ ፍረዱ ፡
6 .  POLARAIZATION     ጽንፈኞች ማህበረሰብን ጫፍና ጫፍ ዋልታ ረገጥ በሆነ የተራራቀ የሀሳብ ልዩነት ውስጥ እንዲገባ ያደርጋሉ :- 
ፕሮፓጋንዳ ያጧጡፋሉ ። ምሳሌ ፤ በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ቴሌቭን ባልሳሳት ከአምስት ከስድስት ወር በፊት አንዲት ጽንፈኛ ሴት ፤ ኦሮሞ ወንዶች ነፍጠኛ ሴቶችን እንዲፈቱ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ባሉበት በቴሌቪዥን ትቀሰቅስ ነበር ። « እኛ እናገባችኋለን የነፍጠኛ ሴቶችን ፍቱ » ትል ነበር ፡፡ አቶ በቀለ ገርባ ኦሮምኛ ከማይችል ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገበያዩ ኦሮሞዎችን ይመክሩ ነበር ። ቀደም ሲል ጁሀር የተባለው ጽንፈኛ የጄኖሳይድ መሪ « ከነፍጠኛ ጋር ከመኖር መሞት ይሻለኛል » ሲል በመገናኛ ብዙሀን ተደምጧል ፡፡ ባሌ ሮቤ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ነዋሪዎች በተሰበሰቡበት አንድ አባት መድረክ ላይ ቆመው ፤  ከአማራና ከጉሙዞች ጋር እንዳትገበያዩ ፤ ንብረት እንሽጥላችሁ ቢሉም እንዳትገዟቸው ። ንብረቱ የኛው ነው ፤ ከየትም አላመጡት ። ብለው ሲያስጠነቅቁ  ፤ እድሜ ለማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ቪዲዮውን እስኪበቃን ተመልክተነዋል ፡፡ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከቤተመንግስት የሚኒሊክን ሀውልት አፍርሰን ፤ የጀነራል ታደሰ ብሩን ሀውልት እናቆማለን ሲሉ ተሰምተዋል ፡፡  የተጋባ ፤ የተዋለደን ፤ አብሮ በፍቅር የኖረን ህዝብ የሰሜንና የደቡብ ዋልታ ያህል እንዲራራቅ መስራት ማለት ይህ ነው ፡፡
ጽንፈኛ የጄኖሳይድ አንቀሳቃሾች ለዘብተኛ ናቸው የሚሏቸው  የራሳቸውን ማህበረሰብ አባላትንም ይገድላሉ ፡፡ በሩዋንዳ ያለቁት ቱትሲዎች ብቻ አልነበሩም ፤ ለዘብተኛ ናቸው ያሏቸውን ሁቱዎችንም ፈጅተዋል ፡፡ በም እራብ ወለጋ ውስጥ በተደጋጋሚ ኦነግ ናቸው የተባሉ  ሽፍቶች ፤ ኦሮሞ የሆኑ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን ግለሰቦችን ሲገሉ ዘወትር የሚሰማ ዜና ነው ፡፡
በጣም ልብ የሚነካው ፕሮፌሰር ግሬጎሪ በጥናታቸው ያረጋገጡት ነገር ፤ ኢላማ የተደረገው የህብረተሰብ ክፍል በምንም መልኩ የጦር መሳሪያ እንዲኖረው ራሱን ለመከላከል የሚያስችለው አንዳችም ድርጅት ሆነ መከላከያ እንዲኖረው አለመፈቀዱ ነው ፡፡ ይህ በቀጥታ በአማራው ህዝብ ላይ የተጣለ ፈተና ነው ፡፡ በቀላል ማስረጃ ለማቅረብ በኦሮሚያ ክልል 30 ዙር  ወታደራዊ ስልጠና ተካሂዷል ፡፡ ያውም ቀደም ሲል በጫካ ደፈጣ እያደረጉ ንጹሀን አማሮን ሲያርዱ ሲያቃጥሉ የነበሩ የኦነግ ሽፍቶች እንዳለ ማለት ይቻላል ተቀላቅለው ፤ ወታደራዊ ስልጠና ተሰቷቸው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ተብለዋል ፡፡ ምናልባት ባንድ ዙር አስር ሺህ ቢሰለጥን ምን ያህል ሀይል በተጠንቀቅ እንደሚገኝ መገመት ይቻላል ፡፡ ለማነው ዝግጅቱ ? ወደ አማራው ክልል የመጣን እንደሆነ በየጊዜው ገበሬውን ትጥቅ ለማስፈታት የሚዘመተው እንዳለ ሆኖ ፤ አንድም ዙር የወታደራዊ ስልጠና ክልልሉ እንዲሰጥ አልተፈቀደለትም ፡፡ የትግሬው ነጻ አውጭ በፈለገው ጊዜና ቦታ እንደልቡ ጦር ሰራዊት ሲያሰለጥን ሲያደራጅ የሚናገረው የለም ፡፡ አማራው ግን አንድ ዙር ለማሰልጠን ሙከራ ቢያደርግ ለክልልሉ መሪዎችና ለጀነራል አሳመነው ሞት ምክንያት ሆነ ፡፡ ሰለጠነ የተባለውም ተበተነ ፤ ግማሹም እስርቤት ታጎረ ፡፡
7 . PREPARATION 
ሰባትኛው ደረጃ የዝግጅት እንቅስቃሴ ነው ፡፡ የታቀደውን ዘር የማጽዳት ስራ ከመጀመር በፊት ሀላፊዎች ተሰብስበው ምን እንደሚሉ ና እንደሚያደርጉ ይወስናሉ ፡፡ « ተጠቅተናል » ወይም «ልንጠቃ ነው » በሚል እንወክለዋለን የሚሉት ወገን ላይ ፍርሀት ይነዛሉ ፡፡ ተበደልን የሚል የሮሮ ዘመቻ ይከፍታሉ ፡፡ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በስፋት ያለመታከት ይሰራል ፡፡ ሊያጠፏቸው የፈለጉ ማህበረሰቦች ላይ ክስ ማብዛት ይቀጥላሉ  ፡፡
 ከሁለት አመት በፊት በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ  የጃዋር ቡድን አዘጋጀው የተባለ ቪዲዮ ተሰራጭቶ ነበር ፡፡  አንዲት ወጣት የኋሊት የፊጥኝ በገመድ ታስራ በደረቷ ወድቃ ፤ በቶርቸር እየተሰቃየች እንዳለ በሚያስመስል ድምጽ እየቃተተች ፤ የሰቆቃ ድምጽ እያሰማች « አማሮች እንዲህ እያደረጉኝ ነው ኦሮሞ ድረስልኝ … » እያለች መልክት ታስተላልፍ ነበር ፡፡
የትግሬው ነጻ አውጭ ሰዎች መቀሌ ከተሰባሰቡ ጊዜ ጀምሮ ለትግራይ ህዝብ የሚሉት ምንድነው ? « ተከበናል ፤ ተወረናል ፤ ተዘጋጁ ፤ መሳሪያዎቻችሁን ወልውሉ » ነው ፡፡
አሁን በቅርቡ ከሀጫሉ ሞት በኋላ የተከሰተውን የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ የተለየ ስእል ለመስጠት የኦሮሞ ጽንፈኞች እየሰሩ ነው ፡፡ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ጽንፈኛ ፤ … የጽንፈኛው ቡድን ደጋፊዎች ነገሩን ገልብጠውት ፤ በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ እንደተፈጸመ አድርገው  እያቀረቡ ነው ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጡ ፤ ለመንግስታት የውሸት ደብዳቤ በማስገባት ትክክለኛውን ነገር  የአለም ህብረተሰብ  እንዳያውቅ በማደናገር ዘመቻ ላይ ተጠምደዋል ፡፡ አማራ በተገኘበት እንዲገደል በመቀስቀስም ላይ ናቸው ፡፡
ፕሮፌሰር ግሬጎሪ እንዳጠኑት ሌላው የዝግጅት እንቅስቃሴ መታጠቅ ነው ፡፡ የጦር መሳሪያ  ወደሀገር ማስገባት ፡፡ ማከፋፈል ፡፡ ይህ ለአዲስ አበባም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ግልጽ የሆነ ታሪክ ነው ፡፡ በየጊዜው  ይህን ያህል የጦር  መሳሪያ ፤ ይህን ያህል ሺህ ሽጉጦች ፤ ቦንቦች ፤ ወደሀገር ሲገቡ እዚህ እዚያ ተያዙ እያለ ፤ ዜናውን  የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ይነግረናል ፡፡ በአማራው ክልል እንደሚደረገው በአዲስ አበባና በዙሪያው እንዲሁም በሌላው ክፍለሀገር ቤት ለቤት አሰሳ እየተደረገ የገባው ጦር መሳሪያ ሲሰበሰብ አላየንም ፡፡  ወይም « ህገወጥ ትጥቅ አስረክቡ » ተብሎ ትዛዝ በመንግስት ሲሰጥ አልሰማንም ፡፡ መግባቱ ይነገረናል ፤ ከዚያ በቃ ፡፡ ኮንቴይነር ሙሉ ገጀራዎች ወደሀገር ሲገቡ ይነገረናል ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ድሮ ገጀራ አይታወቅም ፡፡ በብዛት ስራ ላይ አይውልም ፡፡ አንዳንድ ጥንታዊ ጎራዴ ባንዳንድ ቤት ሊኖር ይችላል ፡፡ ባገር ልጅ አንጥረኞች የሚሰሩ ረጃጅም ቢላዋዎች ይኖራሉ ፡፡ አንዳንድ ማህበረሰቦች የሚታጠቋቸው በተለይ ሶማሌ አፋርና ኢሳ እንደባህል እቃ ፡፡ ለዘመቻ ተይዞ የሚወጣ ገጀራ ያየነው አሁን ነው ።  ጽንፈኞች ከፍ አድርገው እየነቀነቁ አደባባይ በመንጋ ይዘው ሲወጡና ሰውንም ሲጨፈጭፉበት  ጥቅሙን ያወቅ ነው በቄሮ ነው ፡፡ በሀረር  ከተማ ኮንቴይነር ሙሉ ሜንጫ በግብርና መጋዘን ውስጥ ሲወርድ ፤ «ምንድነው ? » ቢባል « ለግብርና አገልግሎት የሚውል ነው » ተባለ ፡፡ ሗላ ላይ ለጽንፈኞች በድብቅ   እንደተከፋፈለ ተነግሯል
8.  PERSECUTION : 
  በስምንተኛ ደረጃ ፕፌሰሩ ያስቀመጡት «አሳዶ ማጥቃት ፤ መግደል ፤ በሀይማኖቱ በዘሩ በፖለቲካ ልዩነቱ  ወዘተ …» ምክንያት ፣:- ሰለባዎቹ ተለይተው ይታወቃሉ ፡፡ ታውቀዋል ፡፡ ብሄራቸው ፤ ዘራቸው፤ ጎሳቸው ፤ ሀይማኖታቸው ተለይቷል ፡፡ ሀያስምንት አመት ወሀኋላ ሄደን እንጀምርና አማራውና ኦርቶኮክሱ ያለፉበትን መንገድ እንየው ፡፡ ሰለባ የሆነው ወገን ሰብ አዊ መብት በስራቱ እጅግ ይጣሳል ፡፡ ከኖሩበት ፤ ካደጉበት ፤ ሀብት ካፈሩበት አካባቢ ንብረታቸው ተወርሶ ፤ ወይም እንዲወድም ተደርጎ ይባረራሉ ፡፡ የትግሬው ነጻ አውጭ ዘረኞች ሀገሪቱን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን የሞትና የመፈናቀልን ፈተና ከአማርውህዝብ በላይ ያስተናገደ ማንም በኢትዮጵያ እንደሌለ ሁላችንም እናውቃለን ፡፡ የተቃጠሉ አቢያተ ክርስቲያናትን ቆጥሮ የሚጨርስ ሰው አለ ?   ወያኔ መራሹ ኢሃደግ በአማራው ላይ ሲፈጽመው የነበረውን ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ በተተኪዎቹ እስካሁን መቀጠሉን አንካካድም ፡፡ « የሚገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ይወጣና ጭፍጨፋው ይካሄዳል»  ስምንተኛው ነጥብ ውስጥ ፤ ሰሞኑን በሻሸመኔ በአርሲ እንደተደረገው « ስም ዝርዝር ይዘው ነው የመጡብን » በማለት ነው ከአደጋው ያመለጡ ሰዎች ያለቅሱ የነበረው ፡፡
ወያኔ የአማራን ሴቶች እንዲመክኑ ያልታወቀ መርፌ በመውጋት ስራ ሰርቷል ፡፡ የጄኖሳይድ አንዱ ፈርጅ ነው  ፡፡ ጄኖሳይድን የሚያንቀሳቅሱ ወገኖች የአለም ህብረተሰብን ትኩረት በጣም ይከታተላሉ ይላሉ ግሬጎሪ ፡፡ የፈጸሙት ግፍ ትኩረት ካልተሰጠውና ማንም አለም አቀፍ ተቋም እንደተባበሩት መንግስታት አይነት ድርጅት ምላሽ ካልሰጠ ፤ ጨፍጫፊዎች ፤ የሰሩትን ሰርተው ያለተጠያቂነት እንደሚኖሩ ያምናሉ ፡፡ በድርጊቱ ይገፉበታል ፡፡ ወንድማችን እስከንድር ነጋ ከአመት በፊት በሀገራችን ምን እየተደረገ እንዳለ ለአለም ለማሳወቅ ሞክሯል ፡፡ ቄሮ ብሎ ራሱን የሚጠራ የጥቂት ግለሰቦች ቡድን ጄኖሳይድ ሊፈጽም ይችላል ብሏል ፡፡ ነገሬ ያለው ወገን አልተገኘም ፡፡ ይሄው ዛሬ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ የመጨረሻውን ስራ ለመስራት ጽንፈኞች ቢንቀሳቀሱም ፤ ወንበሩ ላይ ያለው ወገን በሰጠው አጸፋ ምላሽ ለጊዜው ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ቀላል የማይባል ህይወትና ሀብት ንብረት ቢወድምም ፡፡
9 . EXTERMINATION : 
 መፍጀት ፤ በብዛት መግደል ፡፡ በዘመቻ መልክ በጅምላ መግደል ፤ በመንጋ ማረድ ይጀመራል ዘጠነኛው እርከን ላይ :- 
የአንድ ነገድ አባላት ወይም ያንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወይም የአንድ ሀይማኖት ተከታዮች በፈለገው የቁጥር መጠን ይሁን ተለይተው ሲጨፍፈጨፉ ጄኖሳይድ ይባላል ፡፡
እዚህ ደረጃ ላይ አንድ በጣም ያስደነገጠኝ ነገር አለ « … When it is sponsored by the state , the armed forces often work with militants to do the killing. …. » በርካታ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናት ከሻሸመኔም ከአርሲም ጄኖሳይዱ ከተፈጸመበት ቦታ አስተዳዳሪዎችና በርካታ ፖሊሶች  ታስረዋል፡፡ ገዳዮች ፍጅቱን እንዲያቀላጥፉ የክልሉ ፖሊሶች መሳሪያቸውን ሰተዋል የምትለዋን ዜና አልሰማችኋትም ?
10 . DENIAL
      ሁሉም ነገር ከተጠናቀቀ በኋላ የመጨረሻው ደረጃ « ክህደት» ነው ክህደት:- እስከመጨረሻው ይቀጥላል ፡፡ አልገደልንም ፤ አላረድንም ፤ አላቃጠልንም ፤ ተጠያቂነት ከመጣ በዚህ ይጸናሉ ፡፡ አስፈላጊው ቅጣት ካልተሰጣቸው ድርጊቱን ደግመው አንደሚፈጽሙ ማረጋገጫ ምልክት ነው ይላሉ ፕሮፈሰሩ። አጣብቂኝ ውስጥ ከገቡ ራሳችንን ነው የተከላከልነው ሊሉ ይችላሉ ፡፡ ጥፋቱን ሁሉ ተጎጂዎቹ ላይ ለመደፍደፍ ይጥራሉ ፡፡ ሰሞኑን በሀገር ቤት ውስጥ የተሞከረው እና በከፊል የተሳካው ኦፕሬሽን ደጋፊዎች « ጄኖሳይድ » በኦሮሞ ላይ ተፈጸመ እያሉ ጥፋቱን በነፍጠኛ ላይ እያላከኩ ነው ፡፡ በአብይ መንግስት ላይ እያላከኩ ነው ፤« ፈጀን » ብለው ፡፡ አብይን አማራ ነው የሚሉት፡፡ አብይ ደግሞ የራሱ መንግስት አባላት እንዳሉበት ነግሮናል ፡፡
ከጄኖሳይ እርከኖች በየትኛው ደረጃ ላይ እንገኛለን ታዲያ ጎበዝ ?????? እስቲ አንድ ነገር በሉ !!!!! ኢትዮጵያና ህዝቧን አምላክ ይታደግ !!!
Filed in: Amharic