>

.. እኔን አልሆንም ነበር እኔ! (ያሬድ ሀይለማርያም)

.. እኔን አልሆንም ነበር እኔ!

ያሬድ ሀይለማርያም

ኢትዮጵያን ይዘን ቁልቁል እንውረድ እያላችሁ down down ኢትዮጵያ ላላችሁ ወገኖቼ የዛሬ እናንተነታችሁ አጼ ምንሊክን ጨምሮ የቀደመቱ አባቶቻችን እና እናቶቻችን በከፈሉት የደም እና ያጥንት መሰዋትነት ላይ የተመሠረተ መሆኑ ገብቷችሁ ወደ ቀልባችሁ የምትመለሱበት ቀን እሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ወደ ቀልባችሁ ስትመለሱ፣ ነፍስ ስታውቁ፣ እውነተኛ እና የሐሰት ትርክትን መለየት ስትጀምሩ፣ ከታሪክ መማር እንጂ በታሪክ ማቄም ፋይዳ እደሌለው ስትረዱ ያኔ ይሄን የቴዲን ዘፈን ከሱ በላይ ታዜሙታላችሁ። አፌን ሞልቼ መናገር የምችለው ነገር ከተቀረቀራችሁበት የተሳሳተ የታሪክ እና የአገር ግንባታ ትርክት ስትመለሱ፣ ከቁጣችሁ ስትበርዱና ገሚሶችም እውነቱን ላለማየት የጨፈናችሁትን አይናችሁን ስትገልጡ ያኔ ይህች መሰዋትነት የተከፈለባት አገር down ሆና ሳይሆን ከፍ ብላ እና ጸጋዋም ጨምሮላት ታገኙዋታላችሁ። ኢትዮጵያ ክፉዋን ከሚመኙት ይልቅ እኔ ልሙትልሽ የሚሏት መቶ ክንድ እጥፍ እና ብዙ ናቸው። ያኔ እናንተንም ልጆቼ ብላ እጆቿን ዘርግታ በፍቅር ትቀበላችዋለች።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! እኛም በፍቅር አብረን እንኑር! ለዛሬው እኛነታችን መሰረት ለሆኑት ጀግኖቻችን ክብር ይሁን!!
Filed in: Amharic