>

ለካናዳ ጠቅላይ ሚኒስተር የተጻፈ ግልጽ ደብዳቤ

ለካናዳ ጠቅላይ ሚኒስተር የተጻፈ ግልጽ ደብዳቤ

(በቫንኩቨርና አካባቢዋ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ካናዳውያን)

 

(An open letter to Prime Minister of Canada Justin Trudeau  translation )

https://youtu.be/_9tanqK89M4

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር (Dear Mr. Prime Minister),

እኛ በቫንኩቨርና አካባቢዋ የምንገኝ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ካናዳውያን በቅርቡ በኦሮምያ ክልል በጽንፈኛ የኦሮሞ ቡድኖች የተፈፀሙትን የንፁሃን ዜጎች አሰቃቂ ግድያና ንብረት መውድም፤ እንዲሁም የነዚህ ጽንፈኞች ደጋፊዎች በካናዳ ውስጥ የሚያደርጉት የውሸት ወሬ እጅግ አሳስቦናል።

•       በ June 29, 2020, ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተደረገውን አሰቃቂ ግድያ ሰበብ በማድረግ 239 የንፁሃን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ከፍተኛ የንብረት ውድሚያ በኦሮምያ ክልል ተፈጽሟል።
•       ግድያውና ንብረት ማውደሙ አስቀድሞ የተዘጋጀና የተቀናበር እንደነበር የተለያዩ ዘገባዎች አስታውቀዋል። ዘገባዎቹ ጽንፈኞቹ ስም ዝርዝር ይዘው በየቤቱ እየሄዱ ጥቃት ይፈጽሙ እንደነበር ዘግበዋል። ግድያውና ንብረት ማውደሙ ያተኮረውም የአማራ፤ የጉራጌና የተለያዩ የኦሮሞ ጎሳ ባልሆኑና ክርስትያን ኢትዮጵያውያን ላይ ሲሆን ከኦሮሞ ዘር የሆኑ ክርስትያን ዜጎችም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
•       አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የተፈናቃዮች ቁጥር ከ8420 በላይ እንደሆነና አሁን ያሉትም በአብያተ ክርስትያናት ተጠልለው ነው። ተፈናቃዮቹም በቂ ምግብና መኝታ እንደሌላቸው ዘግባዋል።
•       አንዳንድ ዘገባዎች የfederalና የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናትና የጥበቃ ሃይሎች ጥቃቱ ሲፈፀም ለተጠቂው ህዝቡ ቶሎ አለመድረሳቸውንና አንዳንድ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት በጥቃቱ መሳተፋቸውን ዘግበዋል።
•       በአገር ውስጥ ያሉት ጽንፈኞች ጥቃቱን የፈፀሙት በውጭ አገራት የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ ጽንፈኛ የኦሮሞ ቡድኖች ከፍተኛ ድጋፍና አነሳሽት ጭምር ነው። እነዚህ በውጭ አገራት የሚኖሩ ጽንፈኞች በሚኖሩባቸው ከተማዎች “ኢትዮጵያ ትውደም” “ነፍጠኛ ይውደም” በማለት ሠልፍ አድርገዋል፤ በማህበራዊ ድህረ ገጾችና በተለያዩ ሚዲያዎቻቸውም ጠብና ጥላቻን እየዘሩ ይገኛሉ። ከዚያም አልፈው መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው እያሉ ለሚኖሩባቸው አገሮች የውሸት ደብዳቤ እየጻፉ ናቸው።መንግስታት
• የኢትዪጵያ federal መንግስት በጥቃቱ የተጠረጠሩትን በመያዝና በማሰር የወሰደውን አፋጣኝ እርምጃ እንደግፋለን።

ስለዚህ ከካናዳ መንግስትና ከአለም አቀፉ ህብረተሠብ የሚከተሉትን እንጠይቃለን፦

1.      በቂ ማስረጃም የተገኘባቸው በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡምና ያለበቂ ማስረጃ የታሰሩትም ጉዳያቸው ታይቶ ነጻ እንዲወጡ ለኢትዪጵያ መንግስት እንዲያሳስቡ፤
2.      ለተፈናቃዮች አስፈላጊውን ሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርጉ፤
3.      ኢትዪጵያ አሁን የምትተዳደርበት Ethnic-Federalism እንደገና እንዲገመገም ማሳሰብ፤
4.      ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ የfederalና የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናትና በጥቃቱ የተሳተፉ ጉዳያቸው ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማሳሰብ፤
5.      ጠብና ጥላቻን የሚዘሩ ጽንፈኛ የኦሮሞ ቡድኖችን እንዲቃወሙ፤
6.      በኢትዪጵያ ውስጥ ያለውን ጉዳይ እውነቱን ማውቅና በጽንፈኛ የኦሮሞ ቡድኖች የሚሰራጩትን ደብዳቤዎች በጥንቃቄ ማየትና ማየት።

እናመሰግናለን,
በቫንኩቨርና አካባቢዋ የምንገኝ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ካናዳውያን (Concerned Ethiopian-Canadians in Metro Vancouver)

MP Peter Julian speech on Ethiopian-Canadians Against Genocide in Ethiopia… August 1st  2020 Vancouver BC
https://youtu.be/ZtyhehD_p84

MAL Raj Chouhan speech on Ethiopian-Canadians Against Genocide in Ethiopia …August 1st  2020 Vancouver BC
https://youtu.be/_koRIlK7fVs

Mayor Mike Hurley speech on Ethiopian-Canadians Against Genocide in Ethiopia.. August 1st  2020 Vancouver BC
https://youtu.be/EuIz14uB-c0

Filed in: Amharic