>

"ቤተ መንግሥት ተቀምጠንማ ኢሬቻን አዲስ አበባ ላይ ካላከበርን ምኑን ኦሮሞ ሆንን ...!!! ዶ/ር  አብይ

 
 

“ቤተ መንግሥት ተቀምጠንማ ኢሬቻን አዲስ አበባ ላይ ካላከበርን ምኑን ኦሮሞ ሆንን …!!!

ዶ/ር  አብይ
እንግዳ ታደሰ

ደግነቱ እነ-ሽመልስ አብዲሳ ሳይደብቁ፣ፖለቲካ ኮሬክትነስ የሚሉትን ኩላኩል ቃላት ሳይጠቀሙ እንደወረደ የመንግስታቸውን ስራ ፊት-  ለፊት በገሃድ እየነገሩን ነው።
“እሬቻን አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ተቀምጠንማ አዲስ አበባ ላይ ካላከበርን ምኑን ኦሮሞ ሆንን ብለው ዶ/ር  አብይ ተናግረዋል” ብሎም እውነቱን ሳይቀባባ ኦ.ቢ.ኤን ላይ ዘረግፎታል ። እሬቻ አ.አ መከበሩ ችግር የለውም ! ከጀርባው ያለው ደባ ግን የሰባበርናቸው accessory ተከታይ ፥ ተጓዳኝ አገኘናቸው መገለጫ ቃላቶች መሆናቸው ነው ።
አብሮኝ የሚሰራ አንድ ኖርዌጅያዊ ! አብይ በሚሊተሪ ልብስ ሆኖ ፎቶውን ሲያይ! ይሄ አይደለም እንዴ ኖቤል ሽልማት እዚህ መጥቶ የወሰደው ? ብሎ ጠየቀኝ ። አዎ አልኩት። ታድያ የሚሊተሪ ልብሱ ማሳያ ዲክታተር መሆንን አያሳይም ከኖቤል ሽልማቱ ማግስት በተጻጻሪ አለኝ ?  ያኔ ነው ያላሰብኩትን ነገር ፈረንጁ ያስባነነኝ እንዳስብበትም ያደረገኝ።
በዚህም ሆነ በዚያ ሰዎቹ አካሄዳቸው አገርን አንድ የሚያደርግ ሳይሆን የሚበታትን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው ። ለዚህች አገር መፍትሄ ሁሉም ባለድርሻ አካላት stakeholders ቁጭ ብለው በሰለጠነ መንገድ ተወያይተው የሃገሪቱን ችግር ካልፈቱ ያለነው ገደል አፋፍ ላይ ነው ። ይህ ሟርት አይደለም።
በአጨብጫቢዎችና ፥ በተደጋፊ ተደማሪ ተቃዋሚዎች አይዞህ ባይነት የአገር ችግር አይፈታም ። መንግስቱ የውር ድንብር አካሄድ እየተጓዘ ነው። የቅራኔ አያያዞችን አፋልሶ ንጹሃንን እያሰረ ነው። ሽመልስ አብዲሳ በቃለ መጠይቁ ላይ ስለ- #አዲስአበባ የተናገረውና የያዙትንና ያቀዱትን ፕላን ለተረዳ ሰው ሌላ እሳተ ጎመራ ነው የሚያፈነዳው።
በድኑ ብአዴን’ ከንቅልፉ ባንኖ ሲነሳ የብልጽግና ፓርቲ መከፈል አይደለም ድራሹ ይጠፋል። ለዚህ ደግሞ እትዬ ትህነግም ሆነች ኦቦሌሶ ኦነግ በብልጽግና ውስጥ ያሰማሯቸው ሰዎች የአብይን ሞት እያፋጠኑለት ነው። እሱም አባይ ወንዝ እንደሚያንገላታው ግንድ አይነት ከወዲያ ወዲህ እየተንገላታ ነው ። የአመራር ቅልጥፍና አራት ኪሎ ቤ.መ ውስጥ ፎቶ በመነሳትና ዛፍ በመትከል እንዲሁም በጎስፕላዊ የቃላት ውበት ህዝብን በማደንዘዝ የሚለካ አይደለም።
አብይ ከመቶ ሚልዮን ህዝብ በላይ እየመራ ! ግብጽን የሚያህል ትልቅ አሳማሽ አገር ከራስጌ ነው ግርጌ አስቀምጦ ከበባውን በኦሮሙማ ስሌት አስኬደዋለሁ ብሎ ከገመተ ከህወሃት አልተማረም ማለት ነው። ሟርት አይደለም ! አገሪቱ ተወጣጥራለች ። መፍትሄው ቁጭ ብሎ መነጋገር ብቻ ነው።
Filed in: Amharic