>
5:30 pm - Tuesday November 2, 6315

ለአመታ ታቅዶ ቆይቶ በሰኔ 23  የተቃጠለው ሆጊሶ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ...!!! (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

ለአመታ ታቅዶ ቆይቶ በሰኔ 23  የተቃጠለው ሆጊሶ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን …!!!

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

አሁንም ክርስቲያቹ መግቢያ መውጪያ አጥተው በስጋት ይኖራሉ.!
 
የሰኔ 23 ቀን በምዕራብ አርሲና በባሌ እንዲሁም በሌሎች ኦሮሚያ ዞኖች ላይ ከተደራጁ የቄሮ አጥፊ ቡድኖች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ እና የንብረት ውድመት ደርሷል። በዚኽ ወቅት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት በኮኮሳ ወረዳ የሆጊሶ ከተማ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ነው።
ኮኮሳ ወረዳ ሆጊሶ ቀበሌ መድኃኔ ዓለም እስከ 1991 ዓ.ም. ድረስ በሲዳማ ሥር የነበረ ቢሆንም ከዚያ ወደ ኦሮሚያ ተከልሎ በባሌ ሀገረ ስብከት ሥር ሆኖ ቆይቶ በአሁኑ ደግሞ በምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሥር ይገኛል።
ቤተ ክርስቲያኑ የተመሠረተው በ1946 ዓ.ም ሲሆን በእቴጌ መነን እንደሆነ ይነገራል። ቦታውን መርጠው እንዴት እንደሰሩት ባላውቅም እቴጌ መነን በሞቱ ወቅት ለሳቸው ሕዝቡ ሐዘኑን ለመግለጽና መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ድንጋይ ተክለው መታሰቢያ እንዳደረጉ የአካባቢው ሽማግሌዎች ይናገራሉ።
በቦታው 200 ያክል ክርስቲያኖች ሲኖሩ አካባቢው በሙሉ ሙስሊሞች ናቸው። የክርስቲያኖች አኗኗር እጅግ አሳዛኝ ሲሆን በተለይ በሃይማኖታቸው ምክንያት በመንግሥት መዋቅሩ የሚደርስባቸው በደል ዛሬ የጀመረ አይደለም።
ቀበሌው ወደ ከተማ አስተዳደርነት ሲቀየር የከተማ ካርታ ፕላን በሚል ሰበብ የቤተ ክርስቲያኑን መሬት በግማሽ ከፍሎ መንገድ ሲያወጣና ሲወስድ ለዘመናት ተተክለው የኖሩ አጸዶችን ጨፍጭፈው አጥፍተውባቸው ከወረዳ እስከ ኦሮሚያ ፕሬዘዳንት በወቅቱ አቶ አለማየሁ አቶምሳ ድረስ አቤቱታ ቢያቀርቡ ሰሚ አልነበራቸውም።
የአካባቢው ሰዎች ከብቶታቸውን እየለቀቁ የእንስሳት መዋያ አድርገው ቆይተዋል። ሰኔ 23 በአክራሪዎቹ ሙስሊሞች ሲቀነባበር የቆየው አደጋ ቀን ጠብቀው ሆጊሶ መድኃኔ ዓለምን እሳት ለቀው ሙሉ በሙሉ አቃጥለውታል።
አሁንም ክርስቲያቹ መግቢያ መውጪያ አጥተው በስጋት ይኖራሉ። ባለፈው እሁድ የነበረውንም ግርግር በቪዲዮ መረጃውን አቀርባለሁ። የሚያሳዝኑና እንቅልፍ የሚነሳው የሴት እህቶቻችንን የሰንበት ተማሪዎችን ሕይወት ለብቻው በማስረጃ ወደ ፊት አቀርበዋለሁ። ብዙ ሥራ ይጠብቀናል እንዘጋጅ።
Filed in: Amharic