>

የለማ መገርሳ የመጨረሻው መጀመሪያ...!!! (አያሌው መንበር)

የለማ መገርሳ የመጨረሻው መጀመሪያ…!!!

አያሌው መንበር

1. ነፍሱን ይማረውና፣ ተስፋዬ ጌታቸው “የእኔን ስም ‘ቲም ለማ’ በሚባለው ውስጥ እንዳይካተት፤ አብራችሁም የ’ቲሙ’ አባል እንደሆንኩ አድርጋችሁ አትጥሩኝ። በለማ የሚመራ ወይም የተመራ ቲም የለም። የሰውዬውም አካሔዱ ጤነኛ አይደለም። ስለሆነም እኔ የ’ቲም’ ለማ አባል አይደለሁም።
 ስሜንም አብራችሁ አታንሱት”  ይል እንደነበር ሰምቻለሁ።
ለማ ቲም ፈጥሮ ነበር ወይ? ባልፈጠረው ቲም ለምን እና በማን በስሙ ተሠየመ?
ከዚያ ባለፈም ኦቦ ለማ ስለኢትዮጵያዊነት የተናገራቸው ንግግሮች በእራሱ አምኖባቸው የተናገራቸው ሳይሆኑ ተጽፈው እየተሰጡት ሳይወድ በግድ ያደረጋቸው እንደሆኑ የለማ የቅርብ ሰዎችና ወዳጆች አጫውተውኛል።
2. ኦቦ ለማ መገርሳ ኢትዮጵያዊ ስሜት የሌላቸው ሰው ስለመሆኑ ከእነ ምክንያታቸው  ዶ/ር መረራም በአንድ ወቅት (ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኘው በተሾሙ ሰሞን) አጫውተውኛል። ያው ይሔንን ካነገሩኝ በኋላ ዶ/ር መረራም እና ኦቦ ለማ በአንድ ላይ ለመሥራት ጋዲሳ ኦርሞ ብለው አብረው ለመሥራት መስማማታቸው የመረራን የፖለቲካ አቋም ውዥቀት ቁልጭ አድርጎ ቢያሳይም፤ በደህናው ቀን ወይም አቋማቸው ሳይዋዥቅ ነው የለማን ፀረ-ኢትዮጵያዊ ስሜት የነገሩኝ።
3.ኦቦ ለማ የደብረፂዮን ወዳጅ ነው። ደብረፂዮን አዲስ አበባ ሲመጣ ከሚያገኛቸው ባለሥልጣናት እና ወዳጆቹ ቀዳሚውና ዋናው ለማ ነው።
4. የለማ ሁኔታ እና አገር አፍራሽ ተግባሩ አይታወቅም የሚል ግምት የለኝም። ቀድሞም ፀረ-ኢትዮጵያዊ፤ የኦሮሚያ ክልልን ለቄሮና ለኦነግ ሸኔ ያስረከበ፤ የመከላከያ ሚኒስቴር ይሁን እንጂ የማኔጅመንት ስብሰባ እንኳን አካሒዶ የማያውቅ፤ ሥራ ቦታም መገኘት ካቆመ ወራት ያለፈ፤ በአካልም በመንፈስም ቀረቤታው ከነ ጃዋርና ደብረፂዮን፤ በዚያ ላይ እንዲህ ዓይነቱን የጥፋት ማሰሮ “በጎ ሰው” ብለን እየሸለምን ….. አገራችን ላይ የደረሰው መከራና ስቃይ እንደውም ትንሽ ነው።
Filed in: Amharic