የአዲስ አበባ ህገ ወጥ ም/ከንቲባ ከሥልጣናቸው ተነሱ…
ህብር ራድዮ
የማዕድን እና ኢነርጂ ሚ/ር ሆነው ተሹመዋል
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከህገ ወጥ የመሬት ወረራ እና የኮንደሚኒየም እደላ በተጨማሪ በግልም በሙስና ስማቸው መነሳት ጀምሮ ነበር። ዛሬ ከስልጣን ተነስተው ለማዕድን እና ኢ/ር ሚኒስትርነት ተሹመዋል።
የከንቲባነት ሹመታቸው ህጋዊውን አሰራር ያልተከተለ እንደነበር በጊዜው መዘገቡ አይዘነጋም።
የአዲስ አባባ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራ ሲሆን ማንን እንደሚሾም አልታወቀም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:–
– ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር
– ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
– ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
– ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር
– ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
– ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
– ንጉሡ ጥላሁን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
– እንደአወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
– ፍቃዱ ጸጋ፤ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
– ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ