>

መራራ  ፖለቲካ ያልገባቸው ፖለቲከኛ "!! (ከአለባቸው ደሳለኝ)

መራራ  ፖለቲካ ያልገባቸው ፖለቲከኛ ”   !!

    ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)
* ታሪክ የሞራል ክብረ ህሌና ነው :: 
ታሪክ በቂም በቀል የሚመሰረት ትርክት ሳይሆን በፍቅርና በመተሳሰብ የተገመደ አብሮነት ነው ፤ በቂም በቀል ሐገር አይገነባም …!
 
የምንሰማቸው. የምናያቸው የማይረቡ ነገሮችን  ውለው አድረው  ስሜታችንን እየተፈታተኑ እንድንፅፍም እንድንናገርም  ይገፋፉናል ::
ውስጣችንን አድምተው  ይፈታተኑናል ::
   አንዳንድ ሰዎች መማር መመራመር ብርቃቸው ሆኖ በለላቸው ወኔ  ባዶ ግልብ ስሜታቸውን ሲያቀረሹብን መታገስ እየከበደን ነው .::
  ከሞራልና ከስነ ምግባር ውጭ የማንፈልገውን  መጥፎ  ነገር እንድናስብና እንድንፈፅመው በግድ  ይገፋፉናል ::
የዛሬው   ትኩረቴን የሳቡት ፣.የቀድሞው የሚኢሶኑ ፖለቲከኛ የአሁኑ ኦፌኮው ፣ መራራ. ጉዲና (ፕሮፌሰር)  ናቸው ::
በቅርቡ የሜንጫውን አክትቪስት ጀዋር ሙሀመድን እንኮኮ ብለው አዝለው እንደ ፍንዳታ እያደረጋቸው በተጋቱት አልኮል መጠን ለተሰበሰው ታዳሚና  ለኢትዮጵያ ህዝብ የማይመጥን ንግግር. ሲያሰሙ በቴሊቪዥን መስኮት ተመልክተን ” ዘ” ይገርም ሻሸመኔ !! ሽማግሌው እንደልማዳቸው ተደናበሩ ከማለት በዘለለ ብዙም ትኩረት የሰጣቸው ሰው አልነበረም : :
አባቶቻችን ሊቃውንቶች ሲናገሩ …… ግን
” በእጃችሁ የያዛችዃት ወፍ እያለች ሰማይ ለሰማይ በምትበረው ወፍ  አትወራረዱ” ይላሉ፤ ፡፡
 በእርግጥ መራራ ስብሰባውን የጀመሩት ከመሸታ መልስ ወይም በዞረ ድምር (አንጎበር) እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ  ::
የጥቁሩን ሱናሜ :  የአድዋውን የጦር መሪ የኢትዮጵያን ንጉሰ ነገስት መንግስት  በአለም የወርቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን የፃፉት ** የአኩሪዋ ጥቁር ኮኮብ ** ንጉስ** በመባል የሚሞገሱትን የእምዬ ምንይልክ ታሪክ ዝቅ አድርገው አጉድፈው  የነፍጠኛ ስርአት በማለት   የአድዋውን ጀግና በማንቋሸሽ ነበር ዝባዝንኬ ትረካቸውን የጀመሩት   : :
በነገራችን ላይ አፄ ምንይልክ በእናታቸው ኦሮሞ ሲሆኑ የእጅጋየሁ አዳሞ ልጅ ናቸው ::
ጥያቄው የሚነሳው እዚህ ላይ ነው :: ለዚያውም የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ መምህር !!!
አገርን አለማወቅ ሕዝቡንና ታሪኩን አለመረዳት አላማ ቢስነትን ጨምሮ  ለሐገር ለብሔራዊ ደህንነት አለመጨነቅ የጅሎች ምርጫ ብቻ እንደሆነ ያልተረዱት መራራ  የመቻቻል ጥበብ በፖለቲካው ሳይንስ ውስጥ ፈልገው. አለመልመዳቸው  ሌላውን አስደንጋጭና  አሰገራሚ  አጋጣሚ ቢሆንም በሳቸው መሰሪ አላማ ስንት ትውልድ እንደተሰነካከለ ለመፍረድ በተግባር እየነገሩን ስለሆነ ነገን መጠበቅ ትርጉም የለውም ::  ::
 እኛ የኢትዮጵያ ልጆች ብቻ ሳንሆን ድፍን አፍሪካውያን ፣ እምዬ ምንይልክም ሆኑ ቀደምት ጀግና አባቶቻችንን  ለሐገራችን ከከፈሉት አኩሪ ገድል በስተጀርባ አፈር የማያበላሸውን ታሪካቸውን: ስናገላብጥ የምናገኜው ምስክርነት :ለመንፈሳችን ነፃነት ለአላማችን ፅናት ይሰጠናል ::
ስለሆነም  ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች  ታሪክን ተደግፈን  የምንቆምባቸው ምርኩዞቻችን ናቸው  : :
 መራራ ይህን ሐቅ ክደው  ለማታጠግብ ትንሽ ኩርማን   ጉርሻ የማታ እንጀራቸውን ያጡና  የኢትዮጵያን ህዝብ  አክብሮት በማሳጣት መልካምነቱን የተፈታተኑት. ናቸው ::
በተለይ አንዳንዶቻችን ለመራራ እንሰጣቸው የነበረንን ግምት. እራሳችንን እንድንፈትሽ ትልቅ አጋጣሚን ፈጥሯልናል  ::
ግምታችንም ስህተት እንደነበረ ስንረዳ  የምናውቃቸው መራራና የማናውቃቸው መራራን እያወዳደርን በእርግጥ አዕምሯችን እስኪ ደክም ድረስ እንድናስብ አድርገውናል  ::
ብዙዎቻችን መራራ እንደጠበቅናቸው ትልቅ ያልነበሩ ግን እጅግ በጣም የወረዱ   ትንሽ. ሰው ሁነው አግኝተናቸዋል : :
ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ተባብረን ተፈቃቅረን ተዋደን. ያሳለፍናቸውን  ወርቃማ ዘመናት  ትውልድ ያፈራሉ ያልናቸው መራራ  ትውልድ ገዳይ ሆነው ወጣቱን  ለበቀል እንዲዘጋጅ ሲገፋፉና  በየመድረኩ ላይ የነፍጠኛ ስርአት እያሉ ሲያላዝኑ መስማት ጨርሶ ከአንድ እድሜ ጠገብ ሽማግሌ የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው::
እንደ ትውልድ ቅብብሎሽ እንደ ፣ አንድ ሀላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ  በሐገራችን ውስጥ.፣ያሉብንን ችግሮች በጋራ ተመካክረን እንዳንፈታና ይዘን የቆየናቸውን የጋራ ባህላዊ እሴቶቻችንን እንዳይበላሹ መካሪና ሸምጋይ. አድርገን ስናስባቸው የነበሩት መራራ :  በተገላቢጦሽ በዚህ ደረጃ ወርደው እናያቸዋለን የሚል ግምት ባይኖረንም እራሳቸው ሲተገብሩት ግን አይተናል ሰምተናል :  :
  በነገራችን ላይ መራራ የካዱት የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አብረዋቸው በክፉም በደግም ያሳለፉት የፖርቲያቸውን  የኦፌኮን አባላትንና. ፖርቲያቸውን ጭምር ነው :  ለንዋይ አሳልፈው  የሸጧቸው: :
 ከማን እንደሆነ በትክክል ባይናገሩትም. ነፃ ላወጣህ ነው  ለሚሉትም የኦሮሞ ህዝብ ታአማኒነትን አጉድለውበታል : :
ብታምኑም ባታምኑም መራራ ያልተረዱት ቁም ነገር ከአስገዳጅና ተቆጣጣሪ ከሆነው የሜንጫው ደባላቸው ከጅዋር ሙሐመድ እራሳቸውን እንኳን  ነጻ ማውጣት. እንደማይችሉ በአስር ጣቴ ፈርሜ አረጋግጣለሁ ::  ብታምኑም ባታምኑም ::
 መራራ  ክብራቸውንም ስማቸውንም  በራሳቸው  ደካማ ፍላጎት ስለለወጡት ታላቅ የፖለቲካ ሞት ሞተዋል: : በነገራች ላይ
ገጀራ ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት መፍትሔ አይደለም ::
 ሜንጫ የሰውን ልጅ ህይወት ያጠፋል እንጅ የዲሞክራሲ መሰረት አያመጣም ::
ሜንጫና ገጀራ ጤነኛ አስተሳሰብ ያላቸው ሕዝቦች የሚይዟቸው የመስቀል ወይንም የጨረቃ ምልክቶች ሳይሆኑ  የሽብርና የአማፅ ማስፈፀሚያ መሳሪያዎች ናቸው ::
ሜንጫና ገጀራ አንጋቾች ሰው ይገድሉበታል መጠፋፋትን ያስተምሩበታል እንጅ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ አይመልሱበትም ::
የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የሚመለሰው ሰው ሰው በሚሸቱ አርቆ አስተዋይ አሳቢዎች ሲፈጠሩ በሜንጫና በገጀራ ጉልበት ሳይሆን በፍቅርና በበሰለ አስተሳሰብ ነው ::
መራራ ያልተዋጠላቸው  ታሪክ የሰብእና ሙግት ነው ::
ታሪክ የሞራል ክብረ ህሌና ነው ::
ታሪክ በቂም በቀል የሚመሰረት ትርክት ሳይሆን በፍቅርና በመተሳሰብ የተገመደ አብሮነት ነው ::በቂም በቀል ሐገር አይገነባም
በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን አነሰም በዛም እንደ እምነታች ፈጣሪን እንፈራል  ::
ከክፉ ሰዎች እርቀህ  ፣ ደግ ስራ፣ ስራ የሚለውን የአባቶቻችንን ትውፊት የሞራል ግዴታም ጭምር አርገን ስለምንቀበለው ለሐገርና ለወገን መልካም መስራት ውዴታችን ብቻ ሳይሆን የዜግነት  ግዴታም ጭምር አድርገን ነው፣ የምንወስደው ፡፡
 መልካም ነገር የምንሰራው ከሞትን በኋላ ወደ መንግስተ ሰማይ ለመግባት ብቻ ሳይሆን መልካም ነገር ሰርተው  እንደ አለፉት ደጋግ አባቶቻችን አልፋና ኦሜጋ የሆነውን የኢዮጵያን ስም ከፍ አድርገን ለማሳየት ነው  ::
 ለዚህም ነው ፤ አፈር ሳይጫነን መቃብር ሳይዘጋብን በፊት የምንሰራው  መልካም ተግባርን በሐገራችን ላይ የዘላለለም አኩሪ ታሪክ ለልጆቻችንና ለእኛ የዘላለም ስንቃችን ነው የምንለው : :
ለእውነተኛ አላማ ሲባል ዋጋ መክፈል ታላቅ ብስለትና ጨዋት ቢሆንም መራራ ግን. ስለዚህ እድል ሳይበቁ በነበር መታለፋቸው እጅግ ያሳዝነናል: :  መራራ  ፖለቲካ ያልገባቸው ፖለቲከኛ ::
ሲያልቅ አያምር ይባል የለ ::
እኔም ል ዛሬው በዚሁ አበቃሁ: :
በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን
Filed in: Amharic