>

ሽኩቻ ነው ምርጫ... ?!? (ዳዊት ሰለሞን)

ሽኩቻ ነው ምርጫ… ?!?

ዳዊት ሰለሞን
በህወሓት ይዘወር ለነበረው ኢህአዴግ ምርጫ በየአምስት አመቱ የሚመጣ ድግስ ለቀሪው ህዝብ ደግሞ ምርጫው በደሙ የሚመረቅ መሰዊያው ሆኖ ቆይቷል…!
ህወሃት ከኢህአዴግ ጋር ሆና አገር አቀፍም ይሁን የክልል ምርጫ አደረግኩ እያለች ስታደርቀን መክረሟን ማንም አይዘነጋላትም።
ህወሃት ምርጫ ያለችውን የምርጫን መስፈርት እየጠቀሱ የአንቺ ምርጫ ሳይሆን የብቻ ሩጫ ነው ያሏትን ስትገድል፣ስታስር፣ስታሳድድና  ስታነውር ቆይታለች።
በህወሓት ይዘወር ለነበረው ኢህአዴግ ምርጫ በየአምስት አመቱ የሚመጣ ድግስ ለቀሪው ህዝብ ደግሞ ምርጫው በደሙ የሚመረቅ መሰዊያው ሆኖ ቆይቷል።
ህወሃት አሁን ፌደራሉን ለቅቃ ትግራይን ቤዟ አድርጋ ብትቀመጥም የምርጫ ጋኔኗ አለቀቃትም።እናም የአዲስ አበባውን ወጣት ባታገኘውም የትግራይን ወጣት ደም በመሰዊያዋ አቅርባ ድግሷን ልታደምቅ “ምርጫ ወይም ሞት “እያለች ነው ።
ህወሃት እንኳን አሁን በትግራይ ተወስና ቀሪውን የኢትዮጵያ ክፍል ይዛ ለአቅመ ምርጫ አልደረሰችም እናም በትግራይ ህወሃት ምርጫ ልታደርግ አትችልም ።
እርግጥ ነው ።ህወሃት ምርጫውን እንደቀድሞው በማድረግ ልታሳካው የምትችለው ነገር ለሽኩቻው ከብልጽግና ጋር መዘጋጀቷን ማሳየት ነው ።
ምርጫው የድምፅ ውጤት የሚጠበቅበት ሳይሆን ለብልጽግና ቁመናን ማሳያ ነው ።እናም ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ይላል እንጂ ህወሃት ምርጫውን መቼም ይሁን ከማድረግ ወደኋላ አትልም ።
ነገሩ ምርጫ የሚል ስያሜ ተሰጠው እንጂ አላማውም ሆነ ግቡ ምርጫ ማድረግ ፣ህገ መንግስት ማክበር አይደለም ።ምርጫው የፖለቲካ ስካሩ፣መካረሩና በኢህአዴግ ቤት ያለው ሽኩቻ መገለጫ ነው ።
በግሌ ህወሃት ከዚህ ቀደም ያደረገቻቸውን ይሁን ቀጣዩን ምርጫ በማለት ለመጥራት እቸገራለሁ ፈረንጆቹ እንደሚሉት  Pseudo-election የይስሙላ ምርጫ ስለው ኖሪያለሁ።
Filed in: Amharic