>

ከመስቀል እና ከአማርኛ ጋር ጥላቻ የተጠናወተው አዲሱ የሽብር ኃይል ቀን ያርዳል ፤ ሌሊት መቃብር ያፈርሳል...!!! (ህብር ራድዮ)

ከመስቀል እና ከአማርኛ ጋር ጥላቻ የተጠናወተው አዲሱ የሽብር ኃይል ቀን ያርዳል ፤ ሌሊት መቃብር ያፈርሳል…!!!

ህብር ራድዮ

* ይህን የመቃብር ላይ ምልክት ሰበራ  እንደ ቀላል ጥቃት ከማየት ይልቅ ይህ ኃይል ግልጽ የሆነ በሀይማኖት እና በብሄር ላይ ያነጣጠረ ሽብር የመፈጸም ዓላማውን ለማሳካት የት ድረስ እንደሚሔድ ማሳያ ነውና ትኩረት ሊደረግበት ይገባል…! 
 
* ወገን ንቃ ይህ ለቆመው ብቻ ሳይሆን ለሞተው ጭምር የማይተኛ ጠላት ነውና!!!
 
በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ጭምር ሙታንን ሰላም መንሳት የወንጀል አካል ነው። ለመቃብር ስፍራ ጥበቃ ያደርጋል። ከመስቀል እና ከአማርኛ ጋር ጥላቻ የተጠናወተው አዲሱ የሽብር ኃይል ግን በቀን ያረዳቸው አልበቃ ብሎት ሌትም የሙታንን መቃብር ሊያጠፋ የመስቀል ምልክት ሊያፈርስ ይንቀሳቀሳል። ይህን እንደ ቀላል ጥቃት ከማየት ይልቅ ይህ ኃይል ግልጽ ሀይማኖት እና ብሄር ላይ ያነጣጠረ ሽብር በመፈጸም ዓላማውን ለማሳካት የት ድረስ እንደሚሔድ ማወቅ ያስችላል።
ብልጽግናው የዜጎችን ህልውና ቆመውም ሞተውም እረፍት መንሳትን ዓላማው ያደረገ ኃይል እያለ እንዴት ተግባራዊ ይሆናል!? ወገን ንቃ ይህ ለቆመው ብቻ ሳይሆን ለሞተው ጭምር የማይተኛ ጠላት ነው።
የመቃብር ጠባቂው ” ሌሊት በመኪና ጭነው ያመጧቸዋል፤ የነፍጠኛ መቃብር እዚህ ምን ይሰራል? እያሉ መስቀሉን የሚቆረጠውን ቆርጠው፤ የሚሰበረውን ሰባብረው ፤ ፎቶውን ነቃቅለው ይሄዳሉ፤ ፖሊስ ጋር እስከ ላይ ድረስ ሄደናል የሚሰማ የለም፤ ሂዱልን ነው የሚሉን…” ይላሉ ቀሪውን ምስክርነት ይስሙት  አስተያየት ይስጡበት
Filed in: Amharic