>

የለንደኑ የኢትዮጵያ ወዳጆች የተቋውሞ ሰልፍ...! (ኢዮብ ዘለቀ)

የለንደኑ የኢትዮጵያ ወዳጆች የተቋውሞ ሰልፍ…!

ኢዮብ ዘለቀ
♦ የዛሬዎቹ… “ኢትዮጵያ ዳውን ዳውን ፤ ነፍጠኛ ዳውን ዳውን ” ከማለታቸው ከ 85 ዓመት በፊት  ልክ በዛሬዋ እለት  1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወዳጆች  ስለ ነጻነቷ ፤ ስለደረሰባት ወረራ ፤ ነፍጠኛ ልጆቿ በመርዝ ጋዝ ስለመፈጀታቸው በአንድ ድምጽ በታላቅ የተቋውሞ ሰልፍ ጮህውላታል…!!! 
—————
ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጲያን መውረሯን ተከትሎ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ወረራውን በመቃወም የተለያዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ ነበር ።
በዛው ዘመን በብሪታኒያ የኢትዮጲያ አንባሳደር ሆነው የተሾሙት ሐኪም  ወርቅነህ ለወቅቱ የብሪታኒያ ጠቅላይ  ምኒስቴር ሳሙኤል ሃዋር ፤  ብሪታኒያ ወረራውን እንድታወግዝና ለጦርነቱ ወጪ የሚሆን 20 ሚሊዮን ፓውንድ ብድር ለኢትዮጵያ እንድትሰጥ ጠይቀው  ነበር ፤ ሆኖም ግን እንደታሰበው አልሆነም  ።
ሐኪም  ወርቅነህ እሸቴ ከወራት ቆይታ በሁላ ምንም ምላሽ ባለማግኘታቸው ሐምሌ  22 ቀን 1928 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ይፋዊ መግለጫ ሰጡ ።
የመግለጫው ይዘት በአጭሩ ” ኢትዮጵያ ለጦርነቱ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ትሻለች ፤ ሀገሪቷ በሀብቷ ተጠቃሽ ስትሆን ፍላጎት ላላቸው አገራትና ግለስቦች የነዳጅና የማዕድን ሃብቷን በሊዝ ለመስጠት ትስማማለች ” በማለት ለጋዜጠኛች አሳወቁ ።
ከቀናት በሁላም የብሪታንያ መንግስት ለኢትዮጵያም ሆነ ለኢጣሊያ የጦር መሳሪያ ግዢ እንደማትሰጥ በግልጽ አሳወቀች ።
ይህንን ወራሪውን እና  ተጎጅውን እኩል የሚፈርጅውን ውሳኔ በመቃወም በዋናነት በኢትዮጵያ ወዳጆች አስተባባሪነት ከዛሬ 85 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ነሐሴ 19 ቀን 1928 ዓ.ም  በለንደን  Trafalgar Square በርካታ ሰዋችን ያሳተፈ  ከፍተኛ የተቃውሞ ስልፍ አካሂደው ነበር ።
#ምስሉ ፦ሁሉም ምስሎች የስልፋን ገጽታ የሚያሳዩ ሲሆን በመጀመሪያው ፎቶ ላይ በግራ  በኩል የሚታዩት የ Marcus Garvey ባለቤት Mrs Amy Ashwood Garvey ሲሆኑ በዛው ምስል ነጭ ሱሪ ያደረጉት ወጣቶች የሀኪም ወርቅነህ ልጆች የሆኑት ቢኒያም እና ዮሴፍ ናቸው ፤ ሁለቱም ከዚህ ሰልፍ በሁዋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ቢሆንም ከ የካቲቱ 12 ጥቃት ጋር በተያያዘ በፋሺስቶች በግፍ ተረሽነዋል ።
Filed in: Amharic