>

የግራኝ አሕመድን ሰማነው፥የጃዋር መሐመድን ግን አየነው...!!! (ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው)

የግራኝ አሕመድን ሰማነው፥የጃዋር መሐመድን ግን አየነው…!!!

ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

 

        ከእሾህ ወይን፥ከኵርንችት በለስ እንደማይለቀም እያወቅንም ቢሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን መግለጫ አነበብነው።ይገርማል! ባይሆን የሩቅ ዘመኑን በጆሮ ብቻ የሰማነውን እና በታሪክ የተረዳነውን እውነት ለማጠራጠር ሞክሩ እንጂ እንዴት በዐይናችን በብረቱ ያየነውን እውነት ለማጠራጠር  ትሞክራላችሁ?
       ምኑን ነው የሃይማኖት ገጽታ ያላበስነው? የት እና እንዴት ነው ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ለማሳቀቅ የተሞከረው? እንዲያው ማፈር የሚባል ነገር የለም? ሠላሳ ዓመት ሙሉ “አላህ ወአክበር” እየተባለ ኦርቶዶክሳውያን መታረዳቸው፥እስከ ሕይወታቸው ጭምር መቃጠላ ቸው ከእናንተ ተሰውሮ ነው፥ይህን መግለጫ ያወጣችሁት? ዕርድ የሚጠብቀው ኦርቶዶ ክስ ተቀምጦ እያለ እንዴት ነው አራጁ እስላም የሚሳቀቀው? ማን ተናግሮት ማንስ ነክቶት ነው የሚሸማቀቀው? መንግሥት እንደሆነ “የታረዱት በሃይማኖታቸው ምክንያት አይደለም ፤” እያለ እየተናገረላችሁና እያስፈራራላችሁ ነው፥እናንተን ምን አስጨነቃችሁ? በእርግጥ “ወንድማማቾች ነን፤” የሚለው ንግግራችሁ እውነት እና ትክክል ነው።አዎን፥እስከ ዛሬ ከተፈጸመብን ነገር እንደ ተረዳነው፥እንደ ቃየል እና እንደ አቤል ወንድማማቾች ነን።የአቤ ልን የደሙን ጩኸት ከእግዚአብሔር በቀር ማንም አልሰማውም።የኦርቶዶክሳውያንንም የደማቸውን ጩኸት የሚሰማው እርሱ ብቻ ስለሆነ እናንተም መንግሥትም ልትሰሙ አትች ሉም።ምክንያቱም በጥፋቱ ውስጥ የእናንተም የመ ንግሥትም እጅ ስላለበት ነው።”የፀ ጥታ”(የሽብር) አካሉ፦ሀገር እየወደመ፥ሰው እየታረደ “ከመንግሥት መመሪያ አልተሰጠ ኝም፤” ማለቱ ምን ይመስላችኋል?
       ምን ታደርጉ፥ነገሩ ሁሉ ተገላባብጦ ለሀገሪቱ እናንተ ባለቤት፥እኛ ግን ባዕድ ሆነናል ።በእንግድነት አክብረው የተቀበሉት እንግዳ ቤት አስለቅቆ ባለቤት ሲሆን እንዲህ ነው። ይህ ዘመን ያላሰማን እና ያላሳየን ነገር የለም።በእውነቱ በመካከላችን ያለው የሃይማኖት ልዩነት ብቻ አይደለም።ሌላም ልዩነት አለን።እናንተን የሚናፍቃችሁ ዐረባዊነት ነው፥ትግላ ችሁ ሁሉ ሀገርኛው ፊደልና ቋንቋ ጠፍቶ ዐረብኛው ፊደልና ቋንቋ እንዲነግሥ ነው።እኛ ግን ከኢትዮጵያዊነት ሌላ የምንደርበው ካባ፥የምንደፋውም ዘውድ የለንም።በመጽሐፍ ቅዱስ፦ “እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፤”የተባለች ኢትዮጵያ፦ለትከሻችን የወርቅ ካባ፥ለአንገታችን የወርቅ ሐብል፥ለጣታችን የወርቅ ቀለበት፥ለእጃችን የወርቅ በትር፥ለራሳ ችን የወርቅ ዘውድ ናት።
          ” ጩኸቴን ቀሙኝ፤”አለ የሀገሬ ሰው።ቅዱስ ሲኖዶሱ፦”ፈዝዞ ይሁን ደንዝዞ” መግ ለጫ ከማውጣት ይልቅ ዝምታን መምረጡን አይታችሁ “ተጨፈጨፍን፤” ብላችሁ በጨው በታጠበ ዐይናችሁ አፍጥጣችሁ በመግለጫ መጣችሁ።ለመሆኑ የት ቦታ ነው ኦርቶዶክሱ “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤” ብሎ ያረዳችሁ? ኦርቶዶክስ ስመ ሥላሴን ጠርቶ ፦ይቀድሳል፥ይዘምራል፥ማዕዱን ይባርካል እንጂ አያርድም።ሜንጫውም ሰይፉም ያለው በእናንተ እጅ ነው፥በእኛ እጅ ያለው መስቀል ብቻ ነው።ለመሆኑ “በእስልምና ሊቃውንት” ላይ ያነጣጠረ ግድያ የፈጸመው ማነው? ይህችማ ባለፈው በገዛ እጃችሁ መስጊድ አቃ ጥላችሁ በገዛ አፋችሁ እንደ ጮኻችሁት አይነት ቲያትር ነው። ባይሆን ያልተበላበት ሌላ ድርሰት ፈልጉ።አይ እናንተ፥”ሙስሊሙ ሕብረተሰብ በዚህ ተንኳሽ ተግባር ሳይወናበድ፤” አላችሁ? ለመሆኑ ምንድነው የተተነኮሳችሁት? በእኛ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማች ሁብን ዝም በማለታችን እያፌዛችሁብን ነው? እባካችሁ በሞታችን አትቀልዱብን።
Filed in: Amharic