>

የውሀ ሙሌቱን ድርድር ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ማፈንገጥ ዋጋ እንዳያስከፍለን...!!! (ያሬድ ጥበቡ)

የውሀ ሙሌቱን ድርድር ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ማፈንገጥ ዋጋ እንዳያስከፍለን…!!!

ያሬድ ጥበቡ
*  “የዴሞክራሲ ምህዳሩ ጠበበ፣ ሽግግሩ ሃዲዱን እየለቀቀ ነው” መልእክት የያዘው የአሜሪካ ባለሥልጣን፣ ይህን መልእክት እንደማስፈራርያ እያቀረበ በአንፃሩ አቢይን “በህዳሴው ግድብ ግንባታና ውሀ ሙሊት ጉዳይ የአፍሪካ አደራዳሪዎችን ትተህ ወደዋሽንግተን ተመለስ….! እንዳይለው ስጋት አለኝ!
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ከሆነው ሚስተር ፖምፒዮ ጋር ለመነጋገር ካርቱም መግባቱን ሰምቻለሁ። ከዚህ በፊት ወደ ሩስያ ባቀናበት ወቅት አሜሪካን በአደራዳሪነት እቀበላለሁ በማለት የሠራው ስህትተ ኢትዮጵያችንን ለወራት የዲፕሎማሲ አጣብቂኝና የጦርነት አደጋ ውስጥም ከቷት ነበር። እድሜ ለኮቪድ 19፣ የዓለሙ ትኩረት ወደ ህልውና በመሽጋገሩ ከዚያ ውጥረትና አደጋ ለማምለጥ ችለናል።
አሁን አቢይ ከፖምፒዮ ጋር ካርቱም ላይ በሚያደርገው ግንኙነት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈፅም ስጋት አድሮብኛል። 20 የሚሆኑ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የላኩትን “የዴሞክራሲ ምህዳሩ ጠበበ፣ ሽግግሩ ሃዲዱን እየለቀቀ ነው” መልእክት የያዘው የአሜሪካ ባለሥልጣን፣ ይህን መልእክት እንደማስፈራርያ እያቀረበ በአንፃሩ አቢይን “በህዳሴው ግድብ ግንባታና ውሀ ሙሊት ጉዳይ የአፍሪካ አደራዳሪዎችን ትተህ ወደዋሽንግተን ተመለስ፣ ያን ካደረግክ የኮንግሬስማኖቹን ጫና ለመቋቋም የትራምፕ አስተዳደር ይረዳሃል” የሚል ማታለያ ሊያቀርበለት እንደሚችል መገመት ይቻላል። አቢይም የአሜሪካ አስተዳደር ድጋፍ የሚያስፈልገኝ ወቅት ነው ብሎ ካመነ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ሊሳሳትና በአሜሪካ አደራዳሪነት ተጀምሮ ወደነበረው ጠረጴዛ እመለሳለሁ እንዳይል ስጋት አለኝ። የኢትዮጵያ አምላክ ከመሰል ስህተት እንዲጠብቀው ፀልዩ። አብይ በቅጡ ካሰበበት መውጫ መንገድ ያለው ይመስለኛል። እስረኞቹን አስመልክቶ ዓለምአቀፍ የፍትህ ሥርአትን የተከተለ ሂደት እንደሚኖር ቃል ሊገባ ይችላል። ምርጫውን በሚመለከት፣ የኮቪድ19 ስጋቱ የተጋነነ እንደነበርና በሚቀጥለው ግንቦት ምርጫውን ለማካሄድ እየሠራ መሆኑንና በአዲሱ የኢትዮጵያ ዓመት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ቃል ሊገባ ይችላል። የህዳሴ ግድቡንና የውሀ ሙሌቱን በተመለከተ ግን ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ማፈንገጥ ያለውን አደጋ በማሳየት፣ በቁርጠኝነት መናገር ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ይችላል ብዬ አምናለሁ።
Filed in: Amharic