11:59 am - Friday March 24, 2023
Posted by
admin |
02/09/2020
|
ጋይስ….. አገራችን እንዳትፈርስ…!!!
አሳዬ ደርቤ
ከንቲባው ዘርፎ አይከሰስ- ሽመልስ ዘልፎ አይወቀስ
ድሆች በቆጠቡት ብር- የካድሬ ጎጆ ይቀለስ
ታከለ ወረደ ስንል- ታከለች በቦታው ትንገስ
ሸገር ቤቷን ተነጥቃ- በሰላም ዳቦዋን ትጉረስ
.
ጋይስ…. አገራችን እንዳትፈርስ
ለትምህርት የሄዱ ሴቶች- ጫካ ውስጥ ቀልጠው ይቅሩ
የዘር ጭፍጨፋ ፈጽመው- ‹‹ግጭት›› በማለት ይጥሩ
ኀዘን፣ ንዴታቸውን- አንገት በማረድ ይግለጹ
ቤታችንን በማቃጠል- ንብረት በማውደም ይመጹ
.
ጋይስ…. አገራችን እንዳትፈርስ
የመኮነን ሐውልት ይንኮት- እንዳሻቸው ያፈናቅሉ
ኦሮሞ በያዘው ወንበር- አማራን ዳውን ይበሉ
መሬቱንም ሰማዩንም- በጎጥ ቀላድ ይካፈሉ
ጃዋር የታሰረ እለት- አጃቢው ሆነን እንታሰር
ፖሊስ የከበበው ቀን- ሟቾች ሆነን እንቀበር
የነፍጠኛውን ሥርዓት እናውግዝ- የገዳ ሥርዓት እንማር
ልማት ይጥፋ- ምርጫው ይቅር
.
ጋይስ- አገራችን እንዳትፈርስ
ሲመቷችሁ አታልቅሱ- ሲቀሟችሁ አትክሰሱ
ዝም ብላችሁ ቀበሮ ጋር- ከዐቢይ ፓርክ ተናፈሱ፡፡