>

ኢትዮጵያ የ'ፖለቲካ' ቡድኖች (ደረጀ ዘለቀ)

 ኢትዮጵያ ፖለቲካቡድኖች

(ክፍል 1)

 

ደረጀ ዘለቀ 

     በረጅሙ የሰው ልጆች ታሪክ አስገራሚና አስደናቂ እድገቶች የተመዘገቡትን ያህል አሳዛኝና አስፈሪ ውድመቶችንም አስመዝግቧል። የሰው ተፈጥሮ በተቃርኖ የተሞላ ነውና ከዚህ አዙሪት መውጣት አይቻልም። ዓለማችን እራስዋ የተቃርኖ ውጤት ናት። ስለሆነም የሰው ልጅእንደ ዘመኑና ንቃተ ኅሊናው እድገት ወንጀልን የሚከላከል ህግ ያወጣል። ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ደግሞ አጥፊውን ላይ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ያወጣውን ህግ ይጠቀማል። በዚህ አሁን ባለንበት ክ/ዘመን በሰው ልጅ ላይ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች እንደወንጀሉ ክብደትተመጣጣኝ የእርምት እርምጃ ይወስዳል። በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘው ጄኖሣይድ ነው። ክሱም የሚታየው በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ነው። እንደአለመታደል አገራችን ኢትዮጵያ ይሄው ወንጀል በተደጋጋሚ ተፈፅሞባታል። በገዢዎች ቢካድም መዝገብ ይዞትቁጭ ብሏል። ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ አቅም በመጥፋቱ ወንጀሉ አሁንም አልቆመም። እስክንድር ነጋ ይሄው የጄኖሳይድ አደጋ ተጋርጦብናል ብሎ ከተናገረና ለሚመለከተው አካል በይፋ ማመልከቻውን ካስገባ በኋላ እንኳን ለመስማት የሚዘገንን ወንጀል ጄኖሣይድተፈፅሟል። የመንግሥት ድርጊቱን መካድ ደግሞ መጪውን ጊዜ በሁለት መንገድ እጅግ አስጊ ያደርገዋል። አንደኛ፦ በመንግስት ትብብር የተደረገ ሊሆን ይችላል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የመንግስት ዝምታ ወንጀል ፈፃሚዎችን ያበረታታል የሚለው ነው። የሆነው ሆኖ መንግስትዜጎቹን ከእንደዚህ አይነት ውጤቱ አስከፊ ከሆነ ድርጊት እንዲከላከል አጥብቀን እናስገነዝባለን። የተፈፀመውንም ወንጀል ህግ ፊት ለማቅረብ የሚደረገውንም ጥረት እናግዛለን።

በዚህ ጉዳይ የመንግስት ፍላጎት ይታወቃል እንዳለፈው ዘመኑ ሁሉንም ነገር አደፋፍኖ ለማለፍ ነው። በተጨማሪ በዚህና መሰል ድርጊት በጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ የሚሰጡ መልሶች እጅግ አሣሣቢ ናቸው። ‘ለዲሞክራሲና ለወደፊቷ የበለፀገች ኢትዮጲያ የተከፈለ መሥዋዕትነትየሚሉትን’ ለማለት ነው። የቡራዩውን ጭፍጨፋና እርሱን ተከትሎ በተነሳው የተቃውሞ ሰልፍ የተፈፀመውን የመንግስት ‘ነውረኛ’ እርምጃ ያስረዱበት መንገድ ፍፁም ስህተት ብቻ ሳይሆን የውስጣቸውን እምነት ያጋልጣል። የመጨረሻ ‘ውጤቱ’ ለውጤቱ ማማር የተወሰደውንእርምጃ ትክክለኛነት ይመሰክራል? በእንግሊዘኛው( The end justifies the means) የሚለውን ማለት ነው። ጠ/ሚሩን ለመደገፍ ሰልፍ ወጥተው (ቢያንስ ሀሣባችን ከጠ/ሚሩ ሀሣብ ጋር አንድ ነው ብለው ወጥተው) በራሱ ወታደሮች ካስገደለና በማጎሪያ ከአሰቃየ በኋላ ነው እንዲህየሚለው። ዘላለማዊው ቃል እንደሚለው ‘አንድ ሰው በምን እንደሚያምን ማወቅ ከፈለግህ የሚሰራውን ተመልከት ነው። እርሱ የሚሰራው ሌላ የሚያወራው ሌላ። እምነት በስራ ይገለፃል። ( The end justifies the means) ይሄ አስተሣሰብ፤ በሰው ልጅ ታሪክ፤ በተደጋጋሚ ተሞክሯል።ኮሚኒስት አገሮች በሙሉ ሞክረውታል፣ የአምባገነኖች ተወዳጅ መንገድ ነው። በጠቅላላው ለሰው ልጅ ፀር ነው። እኛ ወደፊት ለምንገነባው ብልፅግና ዛሬ አንተ ሙትልን አይባልም። ማንም በማንም ህይወት ላይ ስልጣን የለውም ከሰጪው በስተቀር።

አገራችን አሁን ያለችበት ደረጃ እንዴት ደረሰች?… ብዙ የተባለበት ነው። እኔም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ እጅግ ያሣስበኛል። ስለሆነም የተሰማኝን እንደዚህ በታች እንደገባኝ እገልፀዋለሁ። ምክኒያቱ በአጭሩ- በተለያየ ጊዜ የሚያጋጥመንን ችግር በተመሣሣይ ዘዴእየደጋገምን ለመፍታት ስለምንሞክር ነው። መላውን ዓለም ሲንጥ የኖረው የሶሺያሊዝም አስተሣሰብ ለአለፉት 46 ዓመታት አገራችንን አላላውስ ብሎ ጠፍንጎ እንደያዛት ይታወቃል። እንደፕሮፓጋንዳው ሳይሆን መሬት ላይ ያለው እውነት ይኸው ነው።  በተለያየ ጊዜ መሪዎች ስልጣንይይዛሉ። የየራሣቸው ‘ርዕዮተ ዓለም’ ይቀርፃሉ (ይርባም አይርባም) ያንን የሚያስፈፅም ‘ካድሬዎች’ ይኖራቸዋል። ኘሮፌሰር መስፍን ‘ሎሌዎች’ ብለው ይጠሯቸዋል። ተስማሚው ስም ይሄው ነበር ግን ‘ካድሬ’ ብዙ ሰው የሚያውቀው ቃል ስለሆነ በሱው እንጠቀም። ከዚያ በኋላመመሪያ ‘ከላይ ይፈሣል/ይወርዳል፣ ካድሬ ተቀብሎ እንደስልጣን እርከኑ ወደታች ያወርደዋል። የመጨረሻ ቡራኬውም ሆነ እርግማኑ የሚወርድበት የኔ ብጤ ህዝቡ ነው። መቃወም ሌላው ቀርቶ ጥያቄ መጠየቅ ፀረ- የሚል ስም አሰጥቶ ለከፋ ነገር ያደርሣል። የችግሮች ሁሉ መፍቻ፦ፀረ-አብዮት፣ ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-ሰላም፣ ፀረ-ህገ መንግሥት ወዘተ… ብሎ ተቃዋሚን ማጥፋት ነው። ከደርግ አንስቶ እስካሁን ድረስ አገር የሚመራው በዚሁ ዘዴ ነው። ከፍተኛው ካድሬ የማእከላዊ ፓርቲ አባል ይሆናል። የተቀረው በየደረጃው ስልጣን ይይዛል። ፓርቲውን እስከታዘዘድረስ ስልጣኑ ለቦታው የማይገሰስ ነው። የካድሬ ችግሩ ከእውቀት የፀዳ መሆኑ ነው። የተማሩ አሉበት እንዳትሉ፤ የካደሩ እለት ሁሉም ትምህርት አክትሟል። የአንድ አምባገነን አገልጋይ ከመሆንና ትክክለኛው አካሄድ የመሪው ብቻ እንደሆነ ከመተረክ አያልፉም። ርእዮተ ዓለሙምከውጭ የተገለበጠ፣ ትርጉም ላይ የጠፋ፣ መያዣ መጨበጫ የሌለው፣ ውጥንቅጡ የወጣ፣ ለምሁራን እጅግ ፈተና የሆነ (ቲዎሪውን ለመፈተን የፈለጉትን) ነው የሚሆነው። ውስጡ ግን ጠላት ብሎ የፈረጀውን እንዴት እንደሚያጠፋ የሚገልጥ ሰነድ ነው። ደርግ ህዝቡን ጠቅላላበመውረስ ቋሚ ንብረት አልባ ሁሉንም ድሃ አድርጎ በእያንዳንዱ ህዝብ ህይወትና ንብረት ላይ እያዘዘ ወደማይቀረው ሄደ። ቀጣዩ ኢህአዴግ ደግሞ የደርግን የድሃ ማድረግ ፖሊሲ እንደያዘ በተጨማሪ አማራና ኦርቶዶክስን ኢላማ ያደረገ ፖሊሲ ያዘ። አከርካሪያቸውን መትተነዋል አሉ።በነገራችን ላይ ይሄ ዓረፍተ ነገር በእኩል ደረጃ ትክክልም ስህተትም ነው። ወደኋላ እመለስበታለሁ። አሁን ደግሞ በዚያኛው ላይ ተጨማሪ፤ አማራ እንዳበቃለት በማመን ኦርቶዶክስ አልባ አገር ለማድረግ እየተሰራ ነው። የብልፅግናውን ሰነድ ማየት ነው። ከደርግ ጀምሮ የተሰራተቀጣጣይ ልማት የትም አይታይም። አንዱ የሰራውን ተከታዩ ያጠፋውና/በጅምር ይተወውና ሌላ የራሱን ይጀምራል። በብድርና በዕርዳታ የመጣ ገንዘብ በዚህ መልኩ ይጠፋል። ካድሬ ያጠፋል  ህዝብ ይከፍላል። አገር ይቆረቁዛል። ጊዜው እየረዘመ ሲመጣ ‘የከሸፈ’ የሚባለው ጎራተቀላቅሎ ታሪክ መሆን ይመጣል። ጠብመንጃ የያዙ ‘ፓርቲዎች’ ጠብመንጃዎቻቸውን በህዝብ ተነጥቀው (ጠመንጃው) ሁለተኛ እጃቸው እንዳይገባ በህግ ታግደው፤ የመንግሥትን ንብረት ለ’ፓርቲ’ ስራ ማዋል በህግ ተከልክሎ፤ በአጠቃላይ ሁሉም ሰው ከህግ ስር እኩል መሆኑተረጋግጦ መደንገግ አለበት። የመጨረሻው ስልጣን የህዝብ መሆኑን በማረጋገጥ ማደራጀት ካልቻልን ዕጣ ፈንታችን ይሄው ነው የሚሆነው። እድገታችንን በተመለከተ ያሉብንን ችግሮች ሣይንሳዊ በሆነ መንገ ፍልስፍናንና እንዲሁም ቴከኖሎጂን በመጠቀም በቀላሉ መፍታት  ይቻላል። አሁን ያሰብንበት እንዳንደርስ ከፊትለፊት የተጋረጡብን፣ ሁሉንም ነገር በማዕከላዊነት ሥም ጠፍንገው የያዙ፣ ከላይ ሲያይዋቸው በእምነት የተለያዩ የሚመስሉ በግብር አንድ ዓይነት ቡድኖች ናቸው። ለራሴ እንዲመቸኝ   ሁሉንም ስማቸውን ሲወለዱ በወጣላቸው ስምነው የምጠራቸው። ስራቸውንም በገባኝ መጠን እገልፀዋለሁ። ልሳሳት እችላለሁ፣ ግን አይመስለኝም።

እነኝህ ቡድኖች እንወክለዋለን የሚሉት ጎሣ እንዳላቸው ይታወቃል/ የሚጠቀሙበት ክፍለ ህዝብ በደንብ ይገልፀዋል። ስለሆነም የምገልፀው ስለየቡድኑ ብቻ ይሆናል። በየጎሣው የከፋፈሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ስለየቡድኖቹ ቢጠየቅ በአንድ ድምፅ የሚለውን ግን በእርግጠኝነትየሚለውን መናገር እችላለሁ። የትግራዩ አባት እንዳሉት ‘የተሰበሰቡበት በአንድ … ነበር’ ነው የሚሉት። ምክኒያቱም እነኝህ ቡድኖች ያተረፉለት ነገር ቢኖር ከሰላምና ብልፅግና በስተቀር ሁሉንም አይነት አፍራሽ ነገር ነው። እንደምናየው ነው። የህዝብ ጥያቄ ሌላ፣ የለም ጥያቄህ ይሄአይደለም ጥያቄህ መሆን ያለበት እንደዚህ ነው የሚሉ እነርሱ። የፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያው በእጃቸው ስለሆነ ያልተጠየቀ ጥያቄ ተጠይቋል ማለት ቀላል ነው። እውነተኛውን ጥያቄ በተመለከተ ብዙ ጊዜ ጥያቄዎቹ በተወካይ ይቀርባሉ፤ ያ በውክልና የተላከው ተወካይ/ዮች ‘ፀረ-ህዝብ’ ይባልና ደብዛው ይጠፋል። ላለፉት 46 ዓመታት ታሪካችን ተመሣሣይ ነው። የሚቀያየሩት ስልጣን ላይ ሰዎችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም የሚጠቀሙበት ቃላት ብቻ ነው። ስለሆነም ሁሉም ቡድን የሚራኮተው ስልጣኑን በማንኛውም መንገድ ለመቆናጠጥ ብቻና ብቻ ነውማለት ይቻላል/ነውም።

ህወአት ለዚህ ፊትአውራሪው ነው። ራሱን ያደራጀው ታሪክ አዋቂ የሆኑትን የትግራይ አዛውንት/ መሳፍንት ‘አድሀሪ’ የሚል ስም እየለጠፈ በመፍጀት ነበር። ከዚያ ቀጥሎ ጠቅላላ ህዝቡ ‘እስኪገብር’ ፍዳውን አስቆጥሮ ነው። የጭካኔው ለከት ማጣት ብዙ የተባለበት ነው።ትግራይ ውስጥ ያልገቡበት ጓዳ የለም። አማራ ፍፁም ጠላታችን ስለሆነ ዘላለማዊ እረፍት መንሳት አለብን ብለው የተማማሉ ናቸው። ኤርትራ ከ’አማራ’ አገዛዝ ተላቅቆ ያ አካባቢ የትግራይ መር ግዛት እንዲሆን ይጥራል። ለዚህም ለ’ትግራይ’ ከታገሉት የሚልቅ ታጋዮቹን ለ’ኤርትራ’ ነፃነት ገብሯል። ይሄ መሥዋዕትነት በሻዕቢያና ደጋፊዎቹ እውቅና ቢነፈገውም።  ስለትግራይ መበደል ብዙ ቢሉም ሚዛን የሚደፋው ይሄኛው ነው። ለዚህም ስኬት የአማራውን መሬት ሁሉ በመንጠቅና አማራውን ከፋፍሎ በማዳከም/ማህበራዊ እረፍት በመከልከል ያቀደበትለመድረስ ይታገላል። ዓላማው የህዳሴ ግድብን፣ የራስ ደጀንን ተራራ ያካተተ ኤርትራን ጨምሮ አገር መመስረት ነበር። አሁን ያሰቡት ሁሉ ተበላሽቶ እዚያው የፈረደበት ህዝብ መሀከል ገብተዋል። አሁን የፌደራል መንግስቱን ስልጣን የያዙት ትብብር/ይሁኝታ ተጨምሮበትየሚፈፅሙትን እያቀዱ ነው። ካለተጨማሪ መስዋዕትነት ህግ ማስከበር የሚቻል/የሚፈለግ አይመስልም። ሁኔታው ትግራይ ለብቻው ገለል ካለ ለእኛ ይቀላል ይመስላል። የደርግም ስህተት ይኸው ነበር ይሄኛው የተማመነው አማራው አያሳልፈውም ብሎ ነው። የአማራው ቡድን ግንሁኔታው አላመች ብሎት ካልሆነ ምኞቱ ይኼው ነው።

ብአዴን፦ይሄ ቡድን በህወአት ፍቅር የወደቁ የሌላ ቡድን አባላት የመሰረቱት ቡድን ነው። በህወአት ተፅፎ የተሰጣቸውን ፀረ-አማራ ሰነድ መመሪያቸው ያደረጉ፣ እስከትግል መጨረሻ ህብረ ብሔር የነበሩ፣ አማራ ጨቋኝ ነው ብለው የሚያምኑና ይህንንም መተዳደሪያ ደንባቸው ላይያሰፈሩ ናቸው። ከክልሉ ውጭ ያለ አማራ ነፍጠኛ ነው ብለው የሚያምኑ፤ በክልሉ ውስጥ የሚኖረውን ደግሞ ትዕምክተኛ ብለው የፈረጁ ናቸው። በሽግግሩ ዘመን ከመጀመሪያው የመንግስት ሰራተኞች በክልላቸው ይስሩ ተብለው ሁሉም ወደየክልላቸው ሲገቡ፣ ክልል አለኝ ብሎየሄደውን አማራ የመንግስት ሠራተኛ በሙሉ አልቀበልም ብሎ ከነቤተሰቦቻቸው የበተነ። በሰዐቱ ለምን አልተቀበላችኋቸውም ተብለው ሲጠየቁ ‘ዲሞክራት አማራ’ አላገኘንም ብለው ያላገጡ። ገና በጠዋቱ ይህንን ነፍጠኛ በሉት ብለው ለፍጅቱ ቡራኬ የሰጡ (በድርጅቱ ሊ/ርየተነገረና እስከአሁን ሰዐት ማሥተባበያ

ያልተነገረበት) ይህንንም ለማስፈፀም 27 ዓመታት ሙሉ ከህወአት ጎንለጎን ቆመው አማራውን በሁሉም መልኩ ያዳከሙና እስከመጨረሻው ሰዐት ድረስ የተፋለሙ ናቸው። የባህር ዳሩን ሰልፍ ያስታውሷል። የህወአት የአማርኛው ክፍል በትክክል ይገልፃቸዋል። የትዕዛዝ ነገር ካልሆነአሁንም ልባቸው መቀሌ ነው። አሁንም አማራ ከሚለው ጋር ነው ፀባችን የሚሉ ናቸው። የድንበርና የርስት ጥያቄዎችን አማራውን በሚጎዳ ሁኔታ እየወሰኑ በርካታ ቦታ ያሣጡት። ከ’ለውጡ’ በኋላ እንኳን አመራር ሆነው ለአማራ መቆርቆር ያሣዩትን ላይ እርምጃ የሚወስዱ።ከአገሪቱ የጎሣ አወቃቀር በተለየ ከፍተኛ አመራሮቹ በደፈናው የሌላ ጎሣ አባላት የሆኑ (ብዙዎቹ የህወአት አባላት)። ለአለፉት 27ዓመታት የክልሉን በጀት ለትግራይ ክልል ሲያሸክሙ የከረሙ። አሁንም ይህንን አድልኦ የማይታገሉ። በአጠቃላይ በአገሪቱ የፖለቲካ ህይወት አማራውአያገባውም ብለው የሚያምኑ ናቸው። የአማራ ህዝብ ለምን ተሸክሞ እንደያዛቸው አይታወቅም።የህወአትን የአማራውን አከርካሪ እንዳይነሳ አድርገን መተነዋል ትርክት እንደገና እናንሳ ። ከላይ እንደገለፅኩት ይኼ አባባል እኩል እውነትም ስህተትም ነው። አማራው በሃይለኛውመመታቱ ትክክል ነው። ስህተቱ የተመታበት ቦታ ላይ ነው። አከርካሪውን ቢሆን ኖሮ እነእርሱም እስካሁን አራት ኪሎ ነበሩ። ሲደበድቡት የኖሩት ጭንቅል ጭንቅላቱን ነበር ፤ ሁለቱን እጆቹንና እግሮቹን ጠፍንጎ ይዞ ያስደበድበው የነበረው ይኸው ጉደኛ ብአዴን ነበር። ሁለቱምከእውቀት ነፃ ስለሆኑ ጭንቅላቱ አከርካሪ መስሎአቸው ነው። እንግዲህ ሰው ጭንቅላቱ ላይ በተደጋጋሚ ሲመታ የሚሆነው ወይ በአደጋው ይሞታል፤ ካልሞተ ደግሞ ዱላው እየበዛበት ሲሄድ ራሱን መሳት ይጀምራል። በማስከተል ሚዛኑን ይስትና ይወድቃል አንዳንዴ የሞተየሚመስልበት ጊዜ አለ። በአማራውና በእነኝህ ቡድኖች መሀከል የተፎጠረው ይኸው ነው። ሞቷል ብለው ምርኮ ለመሰብሰብ ቢከቡት/ የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጉዳይ ያስታውሷል መቐለ የከተታቸውን ውርደት አቅምሷቸዋል። የአማራው ቡድን ግን በለውጥ ሰበብ አሁንምእዚያው አለ። ህዝቡ ራሱን ከዚህ ቡድን ካላራቀ መጨረሻው ቅርብ ነው።

Filed in: Amharic