>

የብአዴን የውርደት ታሪክ ራሱን ደገመ!!! በተወልደ በየነ (ተቦርነ)

የብአዴን የውርደት ታሪክ ራሱን ደገመ!!!

በተወልደ በየነ (ተቦርነ)
* የኦዴፓ አማርኛ ተናጋሪ ክፍል…!!!  
* አንድ ቀን እንዲህ በደሙና በእርዱ፣ በሞቱና በሲቃው፣ በእንባውና በልቅሶው በተዘባበታችሁበት ህዝብ ፊት – አንድ ቀን – ተገቢውን ዋጋችሁንና የውርደት ሸማችሁን ተከናናንባችሁ ማየታችን አይቀርም!  
 
ብአዴን ቀደም ሲል የህወሓት የአማረኛ ተናጋሪው ክፍል ይባል ነበር ።ለዚህ ስያሜ ያበቃው ደግሞ የራሱ ህልውና የሌለው የህወሓት ተላላኪ እና ጉዳይ ፈጻሚ ሆኖ መኖሩ ነበር።በህወሓት ተፅእኖ ስር ለመዉደቁ ማሳያ ከሚሆኑት መካከል
~የህወሓት ምስረታ የካቲት 11
~የብአዴን ምስረታ ህዳር 11
~የህወሓት አርማ በቀይ መደብ ላይ ቢጫ ኮከብ
~ብአዴንም ይሄንኑ ቀለም አቀማመጥ በመለወጥ ብቻ አርማ አድርጎታል
~የብአዴን ትልቁ የትግል መዝሙር” እንዳያልፉት የለም ” እንኳን የዜማ ድርሰቱ የህወሓት ነው።በእነዚህ እና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ሎሌ ሆኖ የኖረው ብአዴን አንፃራዊ ለውጥ እንዲመጣ ትልቅ ሚና የተጫዎቱ ጓዶቹን አስበልቶ ለተረኛ ሎሌነት ዝግጅቱን አጠናቋል። ብአዴን ፈሪ ድርጅት ነው እንደምንም አዝለህ ቤተመንግሥት ብትከተው እንኳን በአጥር ዘሎ ያመልጣል።ዛሬ የሆነውም ይሄው ነው!
 
ዘመነ አጋሰስ!
እንደ እነዚህ ያሉ አጋሰስ መጋዣዎች ግን የአማራ ህዝብ በታሪኩ ገጥሞት የሚያውቅ አይመስለኝም! ምን ሆነው ነው ግን ሰዎቹ? ምንድነው ግን እንዲህ ከሰው በታች አውርዶ ያቀለላቸው? እንዲህ ዓይነቱ ወራዳነት ከአማራ ህዝብ እምብርት ይወጣል የሚል ግምት በህይወቴ ኖሮኝ አያውቅም ነበር! የእውነት? ምን ዓይነት ውርደት የማይሰለቻቸው ጉዶች ናቸው ግን? እነዚህ ናቸው በአማራ ህዝብ ጉሮሮ ላይ እንደ አልቅት ተሰንቅረው ደሙን እየመጠጡና እያስመጠጡት ያሉት የሰው አሽክላዎች! በስመ አብ ወወልድ! ካባ ለባሽ ጀግና ጠፍቶ አጋሰሶች ካባ አልባሽ ሆነው አረፉት! ሆዳም አህዮች! እናንተን ነበር እንጂ ቀድሞ ማለት! እንደነዚህ ዓይነት ወራዶችንስ አንድ ላይ ሰብስቦ ነበር እምቦጭ ውስጥ መጨመር! አሳምነው ጽጌ – አሁን ገና በትክክል – ውስጤ ነው! አንድ ቀን እንዲህ በደሙና በእርዱ፣ በሞቱና በሲቃው፣ በእንባውና በልቅሶው በተዘባበታችሁበት ህዝብ ፊት – አንድ ቀን – ተገቢውን ዋጋችሁንና የውርደት ሸማችሁን ተከናናንባችሁ ማየታችን አይቀርም!
“ይህ የናንተ ዘመን፣
ለካስ ከስሮ ኖሯል – የዘመን መናኛ፣
ያጠናፈረው ነው – የመታው መጋኛ፣
የደገመው ዳፍንት፣
ከፍ ብሎ አጋሰስ – ዝቅ ብሎ ጌኛ!”
  ( – ዮሐንስ አድማሱ፣ ይህ የናንተ ዘመን…)
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
እንባችንን ያብስ!
በደላችንን ይይ!
አላጋጮቻችንን ይመልከት!
ከአጋሰሶቻችን ያውጣን!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
Filed in: Amharic