>

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የገጽታ ግንባታ የደረሰበት ደረጃ አሳሳቢ ነው (ታምሩ ብርሀኑ)

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የገጽታ ግንባታ የደረሰበት ደረጃ አሳሳቢ ነው

ታምሩ ብርሀኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ይህን ያደረጉት የሥራ ባህልን ለማሳየት፣ ከፍ ብሎ ዝቅ ማለትን ለማስተማር ነው ብሎ አቃሎ መውሰድ ይቻላል። የሆነው ሆኖ ይህ መሰሉ ተግባር ከተራ የገጽታ ግንባታ በላይ ፋይዳው ዝቅ ብሎ ከፍ ማድረግን ከሆነ ለምን የሚለው ጥያቄ ያስነሳል።
የሚጠርጉት የሴት ጫማ ነው። ሴትነትን ማክበር ለማሳየትም ይሆናል። እርስዎ በሚመሩት አገር እርስዎ በሊቀመንበርነት በሚያስተዳድሩት ክልል ሴቶች ላይ ምን ግፍ እንደተፈጸመ ለሚያውቀው ዜጋ ይሄ ምንድነው? ታግተው የደረሱባት ያልታወቁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ መወያያ እንዳይሆን ለሆቴል ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥትቶ የሚያስከለክል መንግስትዎን በዚህ እንዴት እንመዝነው? የተማሪዎቹ ወላጆች እንባ እንደ ኣባት ሳይቆረቁርዎ ይህን መሳይ የታይታ ሥራ ያስከብረኛል ብሎ ማሰብ ያዋጣል?
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ የሚጠበቅ ሥራ አለ። የሚመዘኑትም ያንን በማድረግ እና ባለማድረግ ነው።
የየዕለት የዜጎች አጀንዳ የማህበራዊ ሚዲያው ማሟሟቂያ ከመሆን በላይ ችግር ውስጥ ያለችውን አገር ቢያንስ በጊዜዎ ተገቢውን አመራር  በመስጠት ላይ ቢያተኩሩ አይሻልም!? መሪ የሚለካው ዝቅ ያሉትን ዜጎች ሕይወት ከፍ የሚያደርግ የተስተካከለ ኢኮኖሚ አቅጣጫ ተከትሎ ሚሊዮኖችን ከምን እበላ አውጥቶ ከፍ ማድረግ ሲቻል፣የጨቀየየውን የፖለቲካ አመራር እየጠበበ የመጣ የፖለቲካ ሜዳ ጀምረውት በነበረው ተስፋ እንዲቀጥል በማድረግ ጭምር እንጂ በዚህ የታይታ ሥራ የሚገኝ ገጽታ ግንባታ ለሊስትሮውም ለቀረው ዜጋ ከእርስዎ ሀላፊነት ጠብ የሚል ነገር አያስገኝም።
ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሮቶኮል ሹም አላቸው?
Filed in: Amharic