>

በቤንሻንጉል ጉምዝ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል! ማሳያ ነጥቦቹም...!?! (ኤርሚያስ ለገሰ)

በቤንሻንጉል ጉምዝ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል! ማሳያ ነጥቦቹም…!?!

ኤርሚያስ ለገሰ

     1.1. በቤንሻንጉል ጉምዝ አስቀድሞ መዋቅራዊ( ህገ-መንግስታዊ) በሆነ መንገድ ” እኛ” እና ” እነሱ” የሚል አደረጃጀት ተፈጥሯል።
 ( ምሳሌ: በቤኔሻንጉል ጉምዝ ህገ- መንግስት መሰረት የክልሉ ባለቤቶች በርታ፣ ጉምዝ፣ ሽናሻ፣ ማኦና ኮሞ ናቸው። እጅግ አስገራሚው ነገር የህዝብ ብዛት ስብጥሩ ግን 31% አማራና አገው፤ 22% በርታ፤ 13% ኦሮሞ፤ 8% ሺናሻ ሲሆኑ የተቀሩት ከሺናሻ ቁጥር በታች ናቸው።)
   1.2. የሚገደሉ ሰዎች አስቀድሞ ስም ዝርዝራቸው ተለይቷል።
   (ምሳሌ: እንዲገደሉና ንብረታቸው እንዲዘረፍ ታርጌት የተደረጉት አማራን አገው ናቸው።)
       1.3. ግድያው የተፈፀመው እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ነው። ከአንድ ቤተሰብ እስከ 5 ሰዎች አሰቃቂ በሆነ መንገድ ተገድለዋል።
  ( ምሳሌ: የአቶ ስጦታው አወቀ ቤተሰቦች ሆነው የተገደሉ ሚስትና ሶስት ልጆች)
       1.4. ግልጽ ፍረጃዎች ነበር።
 ( ለምሳሌ:- ከተለመደው የእነ ሽመልስ አብዲሳ “ነፍጠኛ” ማዕከላዊ መልዕክት በተጨማሪ “ቀያዮችን ግደል” የሚለው በጥቅም ላይ ውሏል።
          1.5. ግድያው ግልጽ ተልዕኮ ተይዞ በታቀደና በተደራጀ ቡድን የተፈፀመ ነበር።
 (ምሳሌ: በጄኖሳይዱ የተለያዩ የውስጥና የውጪ ሃይሎች ተሳትፈውበታል።
            1.6. ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ መንግስት እና የሚዲያ ተቋማቱ ነገሩን የማደባበስና የመካድ ስራ ሰርተዋል።
    (ምሳሌ: የመንግስት ልሳን የሆነው የአማራ ብዙሃን መገናኛ የሰራውን ዜና አንስቶታል። የመንግስትና የብልጽግና ንብረት የሆኑት ኢቲቪ፣ ፋና፣ ዋልታ፣ ፕሬስ ድርጅት አይተው እንዳላዩ ሆነዋል። በዚህ አጋጣሚ በእነዚህ ተቋም የሚሰሩ ጋዜጠኞች እጅግ እያሳዘኑኝ መጥተዋል።)
           1.7. በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናትና የፀጥታ ሀይሎች በቀጥታም በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ነበር።
     (ምሳሌ: የአማራ ማስ ሚዲያ ለጥፎ ባነሳው ዘገባው ጥቃት የደረሰባቸው የአማራና አገው ተወላጆች ናቸው። ግድያው ከመፈፀሙ በፊት የአማራና አገው ተወላጆች ስጋት እንዳለባቸው ለአካባቢው መንግስት አሳውቀዋል። መንግስት አስቀድሞ ቢያውቅም በቸልተኝነት በመመልከት የሰዎች ህይወት እንዲጠፋ አድርጓል።
Filed in: Amharic