>

ስለ ዐማራ ለመጮኽ ዐማራ መሆን አይጠበቅብኝም። ሰው መሆን በቂ ነው!!! [ ዘመድኩን በቀለ ]  

ስለ ዐማራ ለመጮኽ ዐማራ መሆን አይጠበቅብኝም። ሰው መሆን በቂ ነው!!!
 [ ዘመድኩን በቀለ ]  

እንዴት ነህ አማራ?

«ዘውድአለም ታደሰ»

እንዴት ነህ ግዮኑ – እንዴት ነህ አማራ
አንት የታሪክ ዶሴ – አንት የሰሜን ጮራ
ተነሳብህ አሉ – የተሳለ ሳንጃ – የጨከነ ካራ
እንዴት ነህ አማራ?
ገደሉህ ይሉኛል – አረዱህ ይሉኛል
ህመምክን ስሰማ – መንፈሴን ያመኛል
ደከመ ይሉኛል ፥ መረረው ይሉኛል
ላድንህ ባልችልም ፥ የቀመስኩት ሁሉ ይጎመዝዘኛል!!
እንዴት ነህ አማራ?
አንተ ያገር ካስማ – አንተ ያገር አጥር
ግማሽ ጎኔ ሞተ – ሞትህን ስቆጥር
ተሸለተ ሲሉኝ – መኖሬን ጠላሁት
ሳቅና ደስታዬን – በቅፅበት አጣሁት!!
እንዴት ነህ አማራ?
ደምህን እረጭተህ – ፈትተህ የለቀቅከው
ፊደል ቀርፀህ ሰጥተህ – ቀድመህ ያሳወቅከው
ሰላምክን ሲያውከው …
አጥንት ከስክሰህ – ባቀናሀት ሐገር
ትገባበት ጨንቆህ – ሰርክ ስትቸገር
በነፃ ገበያ ፥ በዘመነ ቁማር ፥ በርካሽ ሲሸጡህ
ዘርህን መንዝረው ፥ጎሳህን አስልተው ፥ ከመሃል ሲያወጡህ
እርጥብ አፈር ምሰው የቀበሩህ ለታ
ሰላሜ እንደዝናር ከነፍሴ ተፈታ!!
እንዴት ነህ አማራ?
ጀግናማ ጀግና ነህ ፥ ምንሽር ትራስህ
ለሐገር የምትተርፍ ፥ እንኳን ላንድ እራስህ
ገላህ ቢራቆትም ፥ ክብርህ ሁሌ ሙሉ
ካንተ የተጣላ – ፍፃሜው አያምርም – መውደቅ ነው እድሉ!!
የተነሳህ ለታ አጥር ላያቆምህ እሳቱ ላይፈጅህ
ከሰማየ ሰማይ ተቀብቷል እጅህ!!
እንዴት ነህ አማራ?
Filed in: Amharic