>

የኦርቶዶክሳውያን ሰቆቃ በዘመነ ዐቢይ አሕመድ  (ዘመድኩን በቀለ)

የኦርቶዶክሳውያን ሰቆቃ በዘመነ ዐቢይ አሕመድ 

  ዘመድኩን በቀለ 

 

* ይሄ ምስኪን ገበሬ ማን ነው…!!
 
 ወዳጄ በብር ላይ የፋሲል ግንብ ተሥሎ ስለቀረበልህ በደስታ “ አጀንዳህን አትቀይር! ” ይሄም ተመዝግቦ ይቀመጥ። 
 
☞ “ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!” መክ፣ 10፥16
•••
… በየተራ መግደል ሲጀምሩ የታሰርሁበትን ገመድ ካጠገቤ የነበረው ህፃን ፈታልኝና በመስኮቱ ወጥቼ ስሮጥ በቀስትና በጥይት አልመው ቢተኩሱም ከጥይቱ ተረፍሁ። በቀስት ግን ጀርባየ ላይ ተወግቼ ጫካ ገባሁ። የወለደ አንጀት አላራምደኝ ሲል ከአጠገብ ካለው ጫካ ሆኘ ሳዳምጥ #ህፃናቱ_ሲታረዱ ልክ ፍየል ሲታረድ እንደሚሰማው ድምፅ ይሰማኝ ነበር። (ከሞት ያመለጡ ክርስቲያን ዐማራ የነገሩትን Thomas Jejaw Molla እንደዘገበው።)
•••
… ይሄን ስትቃወም ዐቢይንና መንግሥቱን ያሳጣህበት ስለሚመስለው “የጌታ ልጆች” ይንጫጩብሃል። ባለጊዜዎቹም ኡስስ ዝምበል ይሉሃል። ለውጡ እንዳይደናቀፍ ይሉሃል። ህወሓትን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጸመው ግፍ እየከሰሷት በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ለተፈጸመው በደል የዐቢይ መንግሥት ምን አገባው ይሉሃል። እሱ አትክልት እየተከለ ነው። መናፈሻም እየሠራልን ነው። እናም ጭጭ በሉ እንዝናናበት፣ አትረብሹን ይሉሃል። የደርጉን መንግሥቱ ኃይለማርያምን፣ የህወሓት ኢህአዴጉን መለስ ዜናዊን ሲወቅስ የሚውለው መንጋ አቢቹ ጋር ሲደርስ እሱ ምስኪን ምን አገባው ይልሃል። ባለ ሾርት ሚሞሪ ህዝብ እያለ እየሰደበውም እንኳ የኔጌታ ክፉ አይንካህ፣ ዝምብለህ ሥራህን ሥራ ይሉታል።
•••
… አሁንም የታረዱት በሙሉ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። መንግሥታችን ደግሞ ሃይማኖቱ የታወቀ ነው። ይህን ያህል ቁጥር ያለው ዜጋ በቀን ብርሃን አደባባይ ታርዶም ዐቢይ አሕመድ ሆዬ ጥቂት እንኳ አይፀፅተውም። ሰንደቅ ዓላማው ዝቅ ብሎ አይውለበለብም።  መግለጫም እንኳ አይሰጥም። የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እንኳን አያደርግም። ለሞጣ፣ ለቤሩትና ለሱዳን የጎርፍ መጥለቅለቅ ያሳየውን ድንጋጤ እንኳ አያሳይም። ትንፍሽም አይልም። ፀጉሩ ሽበት እንኳ አያበቅልም። እንዲያውም ልጁ እያማረበት፣ ሜካፑን ቢያበዛም የተወለወለ መስታወት መስሎ፣ እየወፈረ፣ ደረቱ እየሰፋ እንደ ልጃገረድ ሴትም ጉችጉች ያለ ጡት የመሰለ ነገር እያወጣ ነው ያለው። ፊቱ የበሰለ ቦንቦሊኖ መስሏል። ይህን የአቢቹን ሁኔታ ያዩ ባለጊዜዎቹ “የጌታ ልጆች” በጌታ የተቀባ የጌታ ቅባት የፈሰሰበት ነው ይሉታል። አይ ቅባት። የዐማራና የኦርቶዶክሶች የደም ቅባት። ሜድኢን ኦሮሚያ ወቤኒሻንጉል የሆነ ግሩም የደም ቅባት።
•••
…ኦሮሞን አፈናቅሏል ያለውን የሶማሌውን አብዲ ኢሌን ለማሰር፣ ዘብጥያም ለማውረድ ምንም ዓይነት ጊዜ ያላባከነው ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ክልል በየቀኑ ዐማራና አገው ኦርቶዶክሳውያንን የሚያሳርዱትን የክልሎቹን ባለ ሥልጣናት በሕግ አይጠይቅም። ስለመተከል አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች “የቤጉ ክልል መንግሥት” ሙሉ በሙሉ ስፖንሰር ያደረገው ጥቃት እንደነበር የሚያረጋግጡ ናቸው ይላል ምስጋና ዘጊዮን። ለምሳሌ ይላል ምስጋናው። ለምሳሌ:- ጥቃቱ ከመፈፀሙ አንድ ቀን በፊት ሁለት ፖትሮል የጉምዝ ልዩ ኃይል ወደቦታው አቅንቶ ጉምዞችንና ሺናሻዎችን አሽሽተዋል። ይሄ ማለት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አመራሮች ድራማቅን አስቀድመው አሳምረው ያውቁ ነበር ማለት ነው። አባ ገዳው አቢቹ ኦሮሙማን እያስፋፉለት፣ ዐማራና ኦርቶዶክስን በሚገባ እያጸዱለት ስለሆነ አይነካቸውም። እንዲያውም ጭራሽ ተገዳዩና ሟቹ ዐማራ ለገዳዮቹ ካባ አልብሶ በደንብ የቀሩትን እንዲያጸዱለት ያደፋፍራል፣ ተመስገን ጥሩነህንም ያዘዋል። ( ጎንበስ በል አለው አቢቹ ደመአ መኮንንን)
•••
ይህ ምስኪን ገበሬ ማነው? 
 
  
ሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በዐማሮችና በኦርቶዶክሳውያን ላይ ከተፈጸመው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር በተያያዘ ይህ ከስር የምታዩትና በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለ ምስኪን ገበሬ ፎቶ በማኅበራዊ ሚድያው ላይ በስፋት ሲሰራጭና ሲዘዋወር ሰንብቷል። በፎቶውም ብዙዎች አንብተዋል። ብዙዎች አልቅሰዋል። ብዙዎች ሁላችንም የገበሬ ልጆች ነንና ከባድ ኃዘን ተሰምቶናል። እርግጥ ነው ገበሬው የተገደለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ነገር ግን ቤኒሻንጉልም ኦሮሚያም ውስጥ ግን አይደለም። ደቡብ ነው። ደቡብ ኢትዮጵያ ጉማይድሌ። 
 
•••
ሌላ የዘር ማጥራት በደቡብ ውስጥ እየተፈጸመ መሆኑን የምስልና የቪድዮ መረጃ ከደረሰኝ ሰነባብቷል። ነገርየውን የማጣራት ጊዜ ስለወሰደብኝ ብቻዬን አምቄ ይዤው ቆይቻለሁ። አሁን ግን የደረስኩበትን ድምዳሜ ይዤ ወይ ከነገ እሁድ ወይም ደግሞ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ደቡብ ውስጥ ራሱ የመከላከያ ሠራዊት እንዴት አድርጎ ዐማሮችን እየረሸነና ከአካባቢው እያጸዳ እንደሆነ እንመለከታለን። ወገኖቼ በስሱ ለማበድ ተዘጋጁ።
 
•••
እናም ይሄ ፎቶ ቤኒሻንጉል ውስጥ የተገደለ የዐማራ ገበሬ አይደለም። ይህ መስኪን ገበሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ገበሬ ነው። የተገደለውም በኮሎኔል ፍስሓ ኪዳኑ በሚመራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አማካኝነት ያው የፈረደበት ዐማራ ነህ ተብሎ በእርሻ ሥራው ላይ ሳለ የተረሸነ ምስኪን የጉማይዴ ብሔረሰብ ገበሬ ነው። ይሄንና ይሄን የመሠሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ባሉ የትግሬዋ ህወሓትና የኦሮሞዎቹ ኦህዴድ ኦነግ ተላላኪዎች ጥምር ግኑኝነት እየተፈጸሙ ስላሉ የዘር ማጥፋቶች በተከታታይ ይዤላችሁ ለመቅረብ እሞክራለሁ። የቀጠሮ ሰዎች ይበለን።
 
በነገራችን ላይ ፦ 
 
• በጉማይዴ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በይፋ እንዲዘጉ ተደርጓል። የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት ዝርዝርም ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
 
• ነገርየው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ሳይኖረው አይቀርም። አክቲቪስት የሌላቸውን፣ ሚዲያ የማያውቃቸውን የኢትዮጵያ ነገዶች ዐቢይ፣ ኦነግና ህወሓት በጋራ አጽድተው ኢትዮጵያን ለማን ሊያስረክቧት እንደሆነ ግን እስከ አሁን አልተገለጠልኝም። 
 
• መረጃውን በማጠናቀር ከቦታው ድረስ ሄደው የዘገቡልኝን፣ የቪድዮና የፎቶ መረጃ ሰብስበው ከቦታው የላኩልኝን ወንድሞቼን በሙሉ አመሰግናለሁ። ጥቂት መረጃዎች ፍትህ መጽሔት ላይ እንዲወጡ ተደርገዋል። አሁን ግን ሚሊዮኖች እንዲሰሙት እናደርገዋለን። 
 
#ማስታወሻ| ፦ በለውጡ ስካር ላይ ያላችሁ ባለጊዜ ቤንጤዎችና የአባ ገዳ ልጆች ተረጋጉ። የእናንተን ደስታ የሚረብሽ ዜና ቢሆንም ምንም ልንረዳችሁ አንችልም። እናም ተረጋጉ።
—–
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ….
…የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጋሽ ኦባንግ ሜቶ ግን ይሄን ተናገረ …” የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ በማንነቱ የተጠቃ ብሔር ለበቀል መነሣቱ አይቀርም። ገዳዮች ይሄን አስተውሉ። “
•••
ሻሎም !   ሰላም !
መስከረም 8/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic