የብልጽግናውና የህዋሓቶቹ ስብስብ ቡድኖች ወዴት እየሄዱ ነው.. !?!
አስገደ ገብረስላሴ – መቐለ ፤
* 12ተኛው ሰአት ሊሞላ ሶስት ቀን ቀርቶቷል ! ! ! !
የህዋሓት ኢህአደግ መንግስትም ፣ገዥ ፓርቲም የሆነው የሀገራችን ተፎካካራ ፓርቲዎች ከ1997 ዓ ም ጀምረው በየጊዜው የሽግግር መንግስት ፣(ባለአደራ ጊዚያዊ መንግስት ይቋቋም ብለዋል) ። ኢህአደ ግን ለቀረበለት ጥያቄ ሊፈጸም ( ሊደረግ ከሆነ) በመቃብር ህዋሓት ኢህደግ ይፈጸማል እንጅ አይታሰብም በማለት ጥያቄው አፈነው ። እንዳው ለአብዛኞቹ ለስልጣናችን አስጊ ናቸው ያላቸው የተፎካካሪ ፓርቲ አማራርና አባሎቻቸው ወደ ቃሊቲ ፣ ዝዋይ ፣ ሽዋ ሮቢት በክልል ወህን ቤቶች በማቆያ ፣እሱር ቤቶች በሰንዳፋ ፣በብር ሸለቆ ፣በደዴሳ ወ ዘ ተ ወረወራቸው ፣ ደጋፊዎቻቸውም የሚኖርባ አገራቸው ጠበበቻቸው ። ቀጥሎም በ2002 / በ2007/ በ2012 ዓ ም ፣የኢትዮጱያ ቢሄራዊ ዲሞክራሲያዊ የአንድነት መድረክ ፓርት የሚባል ከ10 በላይ ፓርቲዎች ያቀፈ ከ75 % በላይ የኢትዮጱያ ህዝቦች እወክላለሁ የሚል ፓርቲ አስቀድሞ ሩቅ በመመልከት ፣የነበረውና ያለው የኢህአደግ መንግስት ሀገራችንና ህዝቦቻ በሚፈልጉት አቅጣጫ ሊመራ ስለማይችል ከሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲ እና ያገባናል ከሚሉ የማህበረሰብ አካላት ገዥ ፓርቲም ጭምር በሚያቋቁሙት የምክክር በመግባባት የተመሰረተ ውይይት ተደርጎ እንድ መግባባት ላይ ከደረሱ በኃላ የተብብር ሸንጎ ከ6 ወር ለማይበልጥ ጊዜ አመራሩ በመረከብ ምርጫ ከተደረገ በኃላ ለተመሰረጠው መንግስት ማስረከብ እንዲችል ይቋቋም ።የዚህ ሸንጎ ዋና ተልእኮውን የሁሉም ፓርቲዎች ዩሁንታ ያለው ገለልተኛ ምርጫ ቦር ድ በማቋቋም ፍትሀዊ ነጻ ፓመኝ ዲሞክራሲያዊ በህዝቦች ሁንታ የተመረጠ መንግስት መመስረት ነው ።
በሌላ በኩሉ በአገር ውስጥም በዲያሰፖራም የነበሩ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ፓርቲዎችም የ1997 ዓ ም ፣ከዛ በኃላ ይነሱ የነበሩ ፣የሽግግር መንግስት መስርቶ ህገመንግስት ከተሻሻለ በኃላ ምርጫ ይካየድ ይሉ ነበር ።አንዳንዶቹ ደግሞ ባለአደራ መንግስት ይመስረት ይሉ ነበር ። ለሁሉም ጥያቄዎች አሁን መቐለ ላይ ተሰባስቦ ያለው የህዋሓት ስብስብ መንግስትም የማእከላዊ መንግስት ኮር ሆኖ በበላይነት ቦታ ይዞ በነበረበት ይነሱ ለነበሩ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎች አሁን በአዴን ፣ኦሆዴዴን ፣ዴሄዴን ፣አጋር ፓርቲዎች ያሳባሰበው ፣ብልጽግና ፓርቲም ጭምር አብረው እንደ አንድ ስትንፋስ ሆነው የአንባ ገነን አንባ ገነኖች በመሆን የሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲ ፣ታዋቂ ፖለቲኮኞች ግለሰቦች ፣ቡዱኖች ፣ወዘተ አፍነው ነሮዋል ። አሁን ተፈጥሮ ላለው ሀገራዊ ቀውሲ ግን ዋነኛው ፈዋሽ ሳይንሳዊ መፍትሄ የአብዛኞቹ ተፎካካሪ ፓርቲ መስመር ነበር ። የኢህአደግ አንባገነን ገዥ ፓርቲ ግን ለቀረበለት ሳይንሳዊ የግጭት የአፈታት ዘዴ ባለመቀበሉ እኖሆ ሀገራችን ወደ መፈራረስ አደጋ ገደል አፍ ተንጠልጥላ እንመለከታለን ።
እንግዲህ ዋና አጀንዳዬ እየሰማነው እየተመለከትነው ያለነው በ11ኛ ሰአት የህዋሓት የአመራር ቡዱን የነ አባይ ነብሶ (አስመላሽ ወ/ስላሴ፣ጌታቸው ረዳ፣ ፈትለወርቅ (ሞንጆርኖ )ገ/ዝሄር ደንፋት ነው ያልገባኝ ?እስከ ትላንትና አንድ አመት አከባቢ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ይቀርቡ ለነበሩ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ፍትሀዊ በሆነ መንገድ መልስ እንደመስጠት ፈንታ እኛን ገድላቹሁ በመቃብራችን ላይ የሚመሰረት ስግግር መንግስት ይሁን ፣ለ6ወር የሚቆይ መንግስት አይኖርም ፣ህገመንግስታችን ተንተርሰን እንሞታለን ሲሉን የነበሩ። የህዋሓት ስብስቦች ግን ዛሬ የጭነቀት ጭንቀት ፣ቦሚታቸው በመላስ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ማህበራት ህዋሓትም ፣ብልጽግናም ፣ሁሉም ያገባናል የሚሉ አካላት የተሳተፉበት ተሰብስበው ተመካክረው በመግባባት በመረጡት ባለ አደራ መንግስት ይቋቋም እያሉ ይሰማሉ ። የኣብይ አህመድ ስብስብም በዛው ኢህአደግ በነበረው ገታራ አቋም ነው ያው ?፡ ወይ ወደ ባሰው ወታደራዊ ፋሽሽታዊ አገዛዝ እየሄደ ነው ? አሁን መንግስትነቱ ሊያበቃ12ኛ ሰአት ተቃርባል ምን እንደሚያደርግ እንጃ ? ለኢትዮጱያ ህዝብም ለአለም ግራ አጋቢ ጨለማ ነው።