የኦሮሞን አሻራ በአዲስ አበባ ላይ መጣልና ኢፔርያል ኦሮምያን የመፍጠር ስውር ፖሊሲ…!!!
መርእድ አስፋው
* ኦሮሞ ኢሊቶችና ሙሁሮች ሁሌም የሚያባንናቸው ጨበጥኩት ሲሉ የሚያመልጣቸው አንድ ቅዥት አላቸዋል።
6 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ ወያኔ በሰራው ካርታ በኦሮምያ የተከበቧል። የሰለጠነችና ሀብታም ክልል “አዲስ አበባ” የምትባል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገር አለች። አዲስ አበባን ፡በማታለል ፣ በማስመሰል ፣ ከልተቻለም”በብልጫ ወይም በ”በሜጫ “መውሰድ የሚል ቅዥት …!
ሽገር ፓርርክ ሲመረቅ አላማው ሁለት አይነት መሆኑን በማስረዳቴ በጠ/ሚራችን ደጋፊዎች ስድብናቁጣ ደርሶብኛል። የሽገር ፓርክን አላጣጣልኩም። ከሸገ ፓርክ በላይ የሆነ ችግር ያለባት ከተማ መሆኗን ለመጠቆም ነው የሞከርኩት።ሀሳቤን የተረዱ አንዳንድዶች ደግሞ ደርሶ ሲዩት አምነዋል።እኛ ኢትዮጵኖች ችግራችን ወይ እንውዳለን ወይ እንጠላለን። ለሁለቱም ምክያታችን በቃ “ስሜት”ነው።እርግጥ ነው ለመውደድ” ስሌት” አያስፈልገውም።ፍቅር ሂሳብ ስላልሆነ።
ግን ከመንግስት ጋር ሲሆን የመውደድም ሆነ የመጥላት ግዴታ የለብንም።የኛ መንግስታት ሁሌ የመጀመረያው አንድ አመት እና ሁለት አመት ጥሩ ናቸው።መውድድ ያለብን ጥቅማችንን አስከብሮ ሲገኝ መጥላትም ያለብን ከጠበቅነው በታች ሆኖ ካገኘነው መሆን አለበት።በጥቅማቸው እና በጉዳታቸው እንዳንመዝናቸው ምንግስቶቻችንን የሚራምዱት የዘር ፖለቲካ ህሊናን ጋረደው።ፓለቲካ በዘር ሲሆን “የኔ” የሚል ይገባበታል።የኔ ነት ሲገባበት ደግሞ ፓለቲካ መሆኑ ቀርቶ “ሀይማኖት” ይሆናል”። ፖለቲካ” ሀይማኖት” ሲሆን ደግሞ “አቋም” ይሆናል። ሁሉም ዝግ ሆነ ማለት ነው።
ወደ ጠ/ሚ አብይ አሻራ ወደሆነው ሽገር ፓርክ እንምጣ። የሽገር ፓርክ የታሪክ ሽሚያ ነው ያልነው አሁን የበለጠ እየታየ መጥቷል። ጠ/ሚ አብይ የአዲስ አበባ አዲስ ጎጆ ወጭዎች ፎቶ መነሻ ቦታ አጥተው ሲንከራተቱ አጥር ላጠር ሲሄዱ አይቼ ነው የሽገር የወንዝ ዳርቻ ሀሳብ የመጣልኝ ነው ያሉት።
ይሄ በመሰረቱ ውሽት ነው።ይህን ፕሮጂክት በተመለከተ አንድ ቋሚ ሰው አቶ ተፈራ ዋልዋ መናገር ይችላሉ።ይህ የአዲስ አበባ ሚኒስፓሊቲ ኮሌጅ መጀመሪያ ያደረገው የጥናት ፕሮጄክት አዲስ አበባን የሚቋርጡ ሶዎስቱ ወንዞችን ማእከል የተደተረገ ጥናት ነበር።ሁኔታው ሳይጠናቀቅ ወያኔ መጣች። ተፈራ ዋልዋ በከንቲባነት በነበሩ ግዜ ፕሮጄክቱን ስለአመኑበት እንዲውም ከአዲስ እበባ ማስተር ፕላን ጋር ተጣምሮ እንዲሰራ ፈቀዱ።
ፕሮጄክቱን ያጓተተው የውንዝ ዳር ቤቶች ይነሳሉ መባሉ ነበር። እንዴት ይነሱ? ወዴት ይነሱ? በሚል ጥናት ሲደረግ ነበረ ። ከንቲባው በወቅቱ ሀላፊነቱን ኢንጅነር መስፍን ለሚመራ የኢንጅነሮች ስብስብ ሰጡ። መለስ ዜናዊ በዚ መሀል ተፈራን ዋልዋን ከቦታው አነሷቸው ።ይህም የተደረገው ሆን ተብሎ ነው።ለምን ከተባለ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በፍጥነት ሊከናውን ከቻለ ለወይኔዎች የመሬት ዘረፋ ምቾት ስለማይሰጥ ነበር።ስለዚህ ጠ/ሚ አብይ አስቀድሞ የነበረን ነገር እውን አርገውታል።በውንዝ ተፋሰሶች ዙሪያ ማለቴ ነው።፡መንግስት ሄዶ መንግስት በመጣ ቁጥር አዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዲኖራት አይፈለግም “የቁማር መጫውቻው ካርድ” ስለሆነ። የኢትዮጵያ መሪዋች ከትግሬም ይምጣ ከኦሮሞ ወይም ከአማራ… የገጠርቱ ኢትዮጵያ ተወላጆች ስለሆኑ አመራሮቹ ዘሮቻቸውን ለማስፈር ደጋፊዎቻቸውን ለማስፈር ለመሬት ዘረፋው ምቹ ስለሆነ ነው።
ጠ/ሚ አብይ ይህን ፕሮጂክት የመረጡት የኦሮሞን አሻራ በአዲስ አበባ ላይ የመጣል እቅዳቸው ነው ።በአብዛኛው የኢፔርያል ኦሮምያን ለመፍጠር ታቅዶ የተሰራ ነው።
የአዲስ አበባን ህዝብ ሳላስቆጣ እንዴት “ሆራ ፊንፊኔን መስራት እንደሚችሉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ታልሞ የተሰራ ነው። እግረመንገዳቸውንም ስማቸውን ለመትከል የተደረገ የታሪክ ሽሚያ ነው። ለዚ ነው የጠ/ሚ አብይ የአዲስ አበባን ህዝብ ሳይሆን የሽገር መጋላን ውበት ነው የፈለጉት የምንለው።ንጹህ ውሀ የለለባት ብቸኛዋ የአፍሪካ ከተማ አዲስ አበባ።ቢያንስ በቀን ሶዎስት ጊዜ መብራት የሚጠፋባት በመሰረተ ልማት ኋለቀር አዲስ አበባ ።47% ነዋሪዎቿ ከደህነት ወለል በታች የሚኖርባት 17% ስራ አጥ ወጣት የሚኖርባት አዲስ አበባ… የዘር ፕለቲከኞች በሙስና የሚያላትሟት አዲስ አበባ።እውነተኛ ችግሮቿ ሳይሆን የታዩት ተብለጭላጭ ውበቷን ማስቀደሙ ነው የታየው።
ዛሬ ኢሬቻ አዲስ አበባ መከበሩ ችግር አይደለም።ችግር የሚሆነው ግን ኢሬቻን ሌላው ብሄር ላይ እና አዲስ አበቤዎች ላይ የመጫን ልምምድ ላይ መሆናቸው ነው።ከ150 አመት በኋላ አዲስ አበባ ላይ ለማክበር ችለናል ይላሉ። በየትኛውም መንገድ የታሪክ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። አዲስ አበባ በዛን ዘመን ስላልነበረች።ተከለከለን የሚለውም ላም ባልዋለችበት ታሪክ ነው።ለምን? ቀላል ነው ።አዲስ አበባ ሳትኖር ከልካይ ከየት ይመጣል? የኦሮምያው ብቅሉ ፕሬዝዳንት ወያኔ የጻፈችለትን ታሪክ ነው የሚነበው። የኦሮሞ ኢሊቶች እና ሙሁሮች የታሪክ ጉድለት(deficit) አለባቸው።ከመሪው ጀምሮ እስከ ሙሁሩ ድርስ።
ሁሉም ኦሮሞ አዲስ አበባ ላይ አፍጧል።ጠ/ሚ አብይ የአዲስ አበባ እና የአራት ኪሎ መንግስት ከሆኑ ቆዩ። ወታደራዊ ሰልፍና የፖሊስ ማርሽ አዲስ አበባ ለይ እያደረጉ “ይደነፋሉ” …..አዎ አዲስ አበባን ካዲስ አበቤዎች ለመንጠቅ “ከንጦጦ አራትኪሎ” ከጅማ አባሻውል (አስመራ ) ሲመላለሱ ኢትዮጵያን በወያኔ እንድትፈርስ ፈቀዱ።እንዳውም አንዳንዴ ወይኔ ሆን ብላ የላከችብን ሰው ይሆን እንዴ ስል አስባለሁ? Who knows ይህ ሰው ሰላይ የነበረ ነው ። ስላዮች ደግሞ እንዴት እንደሚሰሩ የሚያውቋቸው ሰላዮች ብቻ ናቸው። ጠ/ሚ አብይ የሀገር ፖለቲካ የለውም ያልነው ለዚ ነው።አጠቃላይ ፖለትካው ስእል “ሽገር መጋላ ነው” ያልነው ለዚ ነው።
ይሄ ሁሉ “ለሆራ ፊንፊኔ የተከፈለ ዋጋ ነው” አታለልናቸው አደናገርናቸው ነጠቅናቸው እንዳለው ግልቡ የኦሮምያ ፕሬዝድንት ሽመልስ አብዲሳ። ጠ/ሚ አብይም ደብል ስታንዳርድ እየተጫወተ ነው። ያልገባው ነገር ግን የዲስ አበባ ህዝብ “የራሱን ሻማ በራሱ እጅ የሚለኩስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም”
የኢሬቻና ገዳ የኦሮሞ መሆንኑን እኛ እናምናለን የናነተም ነው የምትሉትን ግን አንቀበለውም ። አንዳንድ የኦሮሞ ሙሁራን የትግሬ ምሁራን የጻፍላቸውን ታሪክ ዋቢ እያደርጉ ኮንስፓየረሲ (conspiracy theories) (ያልተርጋገጠ ምንጭ አልባ በሬ ወለደ ታሪካቸውን )ይነዛሉ።አንዳንዶቹማ የሚያወሩት ምን እንደሆነ እንኳ አያውቁም።ከድፍረታቸው የተነሳ በእግዛብሄር ስራም ጣልቃ መግባት ጀምረዋል።
እነዚህ የኦሮሞ ዶ/ር እና ፕሮፌስሮች ማእረጉን በትምርት ያገንኙት ይሁን በስጦታ ልናውቅ አልቻልንም።ምክንያቱም የተማረ “አፉን ሲከፍት ጭንቅላቱ ይታያል” አብዛኛው የኦሮሞ ሙሁራን ግን “አፋቸው ሲከፈት ጉሮሮቸው ነው የሚታየው” ። ይሄ ዶክትሬት ሽክም እንደሆነባቸው ያሳያል። ለምሲሌ ዶ/ር ገመቺስ እና የባህል ፕሮፌሰር የሆነው ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ የመሳሰሉ መጥቀስ ይቻላል።
ህዝቅኤል ጋቢሳ ስለኢሬቻ ሲያስረዳ ፈጣሪ “አስቀድሞ ኦሮሞን ፈጠረ ይለናል.” የትኛው መጽህፈ ቁልቁሉ ላይ እንዳገኘው ” የብሾፍቱ ሆራ አርሰዴ ብቻ ነው የሚያውቀው”። እናም በዚ ብቻ አላበቃም ትንታኔው “ዋቃ”የኦሮሞ መለያ ነው። ውቄፈታ የኦሮሞ ብቻ ነው። ጥሩ. ሁሉም ይሁን።”እግዚብሄር አስቀድሞ ኦሮሞን ፈጠረ” ። ከዚያስ መቼም በጣም ደክሞት አረፈ መሆን አለበት። ግን ቀጥሎ ማንን እንደፈጠረ አልነገረንም ። እኛ መልሱን እንጠረጥራለን ያው እስክዛሬ እግዚብሄር ወደ ስራ አልተመለሰም መሆን አለበት።ሚስኪን” ዋቀዮ” እንዴት ቢደክመው ነው? ዋቀዮ ራሱ የአርሲ ሰው ነው ማለት ብቻ ነው የቀረው ፕ/ር ህዝቅኤል። ሽከና አሩሲ ይሄን ጉዳቸውን አፈሩን አራግፈው መጥተው ቢሰሙ ኖሮ በቀጥታ ዜግነታቸውን ማዳጋስካር ባደረጉ ነበረ።ጉድ ነው. ..አስቀድሞ የተፈጠረው ኦሮሞ ፊደል ፍለጋ ወደላቲን ተሰደደ። ከላቲን መልስ የኩሽ መሬት ላይ አረፈ።
እንዲህ አይነት በኮንስፓይረሲ ወሬና ተረት ላይ የሚንከባለሉ የታሪክ ሙሁሮች ናቸው ኦሮምያ ያቀፈችው። ኢሪቻን እና ገዳን ኦሮሞ ቋንቋን በሀይል እና አፖልቲካ ተጽኖ ኢትዮጲያዊያን ላይ ለመጫን ነበር ህልሙ… ግን ያቺ ኢትዮጵያ በ ወያኔ ሽፍጥ የለችም።ዛሬ10 ክልል ምናልባትም ቀጣይ 20 ክልል መንግስት ሊመጣ ይችላል።ምክንያቱ የውያኔው ስርእት ሁሉም የራሱን ክልላዊ ምንግስት እንዲፈጥር የኮሎንያሊስቶችን ልምድ አስርጻ ነው የሄደችው። የአንድ ብሄር የበለይነት ማምጣት ህልም ሆኖ ቀረ። ኦሮሞ እንደቁመቱ እንደውፍረቱ የሚል እንቶ ፈንቶም የለም።
ኦሮሞ ኢሊቶችና ሙሁሮች ግን አንድ ቅዥት ይቀራቸዋል። 6 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ ወያኔ በሰራው ካርታ በኦሮምያ የተከበቧል። የሰለጠነና ሀብታም ክልል “አዲስ አበባ” የምትባል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገር አለች።አዲስ አበባን ፡በማታለል ,፡በማስመሰል,፡ ከልተቻለም”በብልጫ ወይም በ”በሜጫ “መውሰድ የሚል ቅዥት ነው ያለው ። የጠ/ሚ አብይና የኦሮሞ ሙሁሮች የመጨረሻ እቅድ ይሄው ነው።ለጊዜው ይሳካ ይሆናል።መጨረሻው ግን ፈጣሪ ነው የሚያውቀው።አያምርም።አዲስ አበባ ደሴት አይደለችም ብሏል አራጁ ጀዋር መሀመድ። እንግዲያውስ ኦሮምያም ደሴት አይደለችም በብዙ ብሄሮች የተከበበች ነች።
ታሪክ ሙሁሮች ነን ብለው ሲያበቁ ማስረጃ ይሌለው በተረት ወይ በተለምዶ አነጋገር ወይ አሉሽ አሉሽ ላይ የሚጠነጥን ታሪክ ያወራሉ። ለምሳሌ አሁንም እንጥቀስ ዶ/ር ገመቹ “መቶ ሴቶች በግራ መቶ ወንዶች በቀኝ ተስልፈው ጸብል ተረጭተው ወልደማሪያም እና ወለተማርያም ተብለው ወደጦነት ይላካሉ? ይሉናል።ወደጦርነት ነውኮ. …ጦርነት ላይ ሆኖ የሚያማልል ስም ፍለጋ? ?ማስረጃ ቢጠየቅ “አሉባልታ”ይሆናል መጨረሻው። ያሳፍራል። የተማረ ሰው ካለተማረ የሚለይበት በሰውነቱ አይደለም። ንገር ግን በሚያፈልቀው የአማራጭ እና የላቀ አስተሳሰብ ነበር። የሰለጠነ አሰተሳሰብ፡ለችግሮች መፍትሄ የሚሆን አስተሳሰብ ።የእውቀት ብርሀን መፈንጠቅ ሲችል ነበር።የተማረ የሚባለው።ያ ካልሆነ ግን ዲግሪውም “ሽክም” ይሆናል።ሽክም።
” አዋቂ ሁን ፡ተማሪ ሁን ፡አስተማሪ ሁን አራተኛ ግን መሀይም አትሁን።ተብሎ ተጽፎል።”የቡርቃ ዝምታን”አንብቦ የኦሮሞ የታሪክ ሙሁር ነኝ የሚል ነው የበዛው።ተስፋዪ ገ/አብ አሜሪካና አባሻውል ሆኖ ምላሱን እያውጣባችሁ ነው።