>
5:18 pm - Friday June 15, 9162

የአብይ አህመድ (የኦሮሙማ)፥ ካርዶች...!!! (ጌራወርቅ ዝናቡ)

የአብይ አህመድ (የኦሮሙማ)፥ ካርዶች…!!!

ጌራወርቅ ዝናቡ

በኦህዴድ የበላይነት የሚዘወረው መንግስታዊው የኦሮሙማ ቡድን፥ እንደአደጋ የሚያያቸውን አልያም potentially አደጋ ሊሆኑኝ ይችላሉ የሚላቸውን ሀይሎች ከሚመታበት ስልት አንዱ፥ ከጀርባ ሆኖ በስውር እጁ (Assassin tactic)  እነዚህ ሀይሎችን በተቀናቃኝና ተፎካካሪ ቡድኖች በመከፋፈል፥ እርስበእርስ እንዲመታቱ በማድረግ ማጠፋፋት፣ ማዳከምና፥ የተዳከሙ ተፃራሪ ቡድኖችን በእግሮቹ ስር በማስገባት እንደአስፈላጊነቱ በየተራ እያፈራረቁ በማቅረብና በማራቅ ተገዢ ማድረግ ነው…!
 
አብይ አህመድ የሚመራው የኦሮሙማ መንግሥት ፥ ይዞት የተነሳውን ፋሽስታዊ ግብ በከፍተኛ ፍጥነት እያሳካ የሚገኝበትን አሰራር /modus operandi/ መፈተሽ ፥ እንደ አማራ እየደረሰብን ያለውን ነገር አጥርቶ ለመመልከት፣ በየጊዜው የድንገት የሚመስሉ ክስተቶች በስሌት ተቀምረው እየተተወኑብን መሆኑን ከመረዳት በዘለለ፥ የዚህን መንግሥት detail anatomy ማወቅ፥ በቀጣይ አስተማማኝ መፍትሔ ለማምጣት እንደ ግብአት ይረዳል።
የአብይ አህመድ መንግስት የኦሮሙማ ፕሮግራሙን እያስፈፀመ የሚገኘው በዋናነት ሶስት አደገኛ ስልቶችን በመጠቀም ሲሆን፥ እነሱም፦
1. ቀውስ በመጥመቅ (The Strategy of Chaos Fermenting)
2. ድምፅ-አልባ ወረራ በመፈፀም (The Strategy of Silent Invasion)
3. በብልጭልጭ ገፅታ ተላላውን ህዝብ በማደንዘዝ፥ አላማን ማስፈፀም (The Strategy of mesmerizing  and duping the gullible-mass by visible activity to hide the real intention)
እነሆ ዝርዝሩን በቅደም ተከተል እንዲህ እንመለከተዋለን።
 
1. ቀውስ ጠመቃ (The Strategy of Chaos Fermenting)
በአጠቃላይ ሲታይ ጠላት/ተቀናቃኝ  በቀውስ ውስጥ ሲገባ፥ የትኩረትና የአቅጣጫ መዛባት ስለሚገጥመው፣ አብዛኛውን ጊዜውንና ጉልበቱን እንዲሁም ሀብቱን የሚያውለው የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት በመጣር ስለሚሆን፣ ከስትራቴጂክ ጉዳዮች ይልቅ እዚህና እዚያ የተፈጠረውን እሳት ለማጥፋት ስለሚጠመድ፥ እጁ በቀላሉ ተጠምዝዞ ይሸነፋል።
በተለይ የሚከሰተው ቀውስ በድንገተኛ ክስተት አልያም በተፈጥሮ አዝጋሚያዊ ሁኔታ ከመፈጠር ይልቅ፥ ሆን ተብሎ አንድን አካል ለማጥቃት የሚፈጠር ቀውስ በሚሆንበት ጊዜ ፥ ለቀውስ ፈጣሪው ሰርግና ምላሽ፥ ቀውስ ለተደገሰለት ደግሞ በቀላሉ የማይወ’ጡት የአቀበት ላይ ጦርነት ነው የሚሆነው።
ይህንን ጠንቅቆ የሚያውቀው የአብይ አህመድ የኦሮሙማ ፋሽስታዊ መንግሥት፥ የማያባራ ቀውስን በአማራ ህዝብ ላይ በመፍጠርና አማራን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕረፍት በመንሳት፥ የኦሮሙማ ፕሮግራምን እዚህ ግባ የማይባል ተግዳሮት ሳይገጥመው እያስፈፀመ ይገኛል።
ይህ ፋሽስታዊ የኦሮሙማ መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የማያባራ ቀውስን እየፈጠረ ያለው በሁለት ስልት ሲሆን፥ እነሱም፦
ሀ. አማራ ተጋላጭ የሆነባቸውን ስስ ብልቶች በመምታት (Backdoor Strategy)
ለ. እርስበርስ ማበላላት (Playing opponents against each other)
ወደ ዝርዝሩ ስንገባ፦
ሀ. አማራ ተጋላጭ የሆነባቸውን ስስ ብልቶች በመምታት (Backdoor Strategy)፦
ከመላው የአማራ ህዝብ ውስጥ፥ ወደ 40% የሚሆነው ህዝብ ፥ ወያኔ ትግሬ፥ “የአማራ ክልል” ብሎ ከከለለው ስፍራ ውጪ ይኖራል። ይህ “ከአማራ ክልል” ውጪ የሚኖረው በቁጥር ከመላው የአማራ ህዝብ 40% የሚያህለው ህዝባችን ፥በጠላት ስሌት መሠረት፥ የአማራ ስስ ብልት (Soft Belly) ተደርጎ የተወሰደ ሲሆን፥ አሁን ባለው የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ደግሞ፥ በሚከተሉት ሶስት ተመጋጋቢ ምክንያቶች የተነሳ ለጠላት ጥቃት ፍፁም ተጋላጭ ሆኗል፦
1ኛ. ሀገሪቱ በክልል ስትዋቀር፥ የአማራ ሰፋፊ ግዛቶችና መሬቶች ከእነ ህዝቡ በየአቅጣጫው ተቆራርጠው፥ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲጠቃለሉ መደረጉንና፥ በተካለሉበት ክልል ውስጥ በገዛ ርስታቸው፥ “መጤ” ተብለው ከመፈረጃቸውም በላይ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎም ይሁን ውክልና እንዳይኖራቸው፥ በክልላዊ ህገመንግስት የታገዱ በመሆኑና አሁን በሚኖሩበት አካባቢ ፥ “ጠላት፣ ወራሪ” በሚል ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና የፖለቲካ ፕሮግራም ሰለባ መሆናቸው፤
2ኛ. ብአዴን ከዛሬ ሰላሳ አመት ጀምሮ፥ “ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ አማራዎችን በጠላትነት ፈርጄ የምዋጋቸው ነፍጠኞች ናቸው” የሚል አቋም አራማጅ መሆኑ፤ ከዛሬ ሶስት አመት ጀምሮም ብአዴን ለፖለቲካ ፍጆታ፥ ይህንን አቋሙን የቀየረ ቢመስልም፥ በተግባር ሲፈተሽ ግን አሁንም እንደበፊቱ፥ ይህ ከክልሉ ውጪ የሚኖረውን ወደ ሃያ ሚሊየን የሚጠጋ አማራ በጠላትነትና በነፍጠኝነት በምንቸገረኝ የሚያየው በመሆኑ፥ ይህ ህልቆ መሳፍርት የሌለው ከመላው የአማራ ህዝብ ቁጥር 40% የሚያህል ህዝብ፥ መንግስታዊ መዋቅርን የያዘ፥ የእኔ የሚለው መንግስትና ተቆርቋሪ ባለመኖሩ፥ ይህ በሚሊየን የሚቆጠር ህዝባችን፥ አማራን እንደህዝብ ማጥቃት ለሚፈልግ ጠላት ሁሉ፥ ተጋላጭ ስስ ብልት (soft belly) ሊሆን ችሏል።
3. ከብአዴን ውጪ የሚገኙ፥ አማራን እንወክላለን የሚሉ ድርጅቶችም ቢሆኑ፥ በተግባር ተፈትነው እንደታዩት፥ የአዲስ አበባን አማራ ጨምሮ፥ “ከአማራ ክልል ” ውጪ ያለው አማራን ትኩረት ነፍገውት ፥ ህዝባችንም አደራጅ እና አሰባሳቢ አጥቶ እንደ ዕጓለ ማውታ የተተወ ነው።
በሆድ ይፍጀው እንለፈው በሚል እንጂ፥ ከወራት በፊት በመተከል አማራ መፈናቀል፥ ሹፈት አይሉት ስላቅ ወለድ “እኔን ምን አገባኝ” የሚሉ ኩርንችቶችን የአመራር ድምፆች ከመስማት በላይ ዘግናኝ ነገር የለም። መሬት ላይ በተግባር የሆነውን የየዕለት ነውረኛ ተግባራቸውን እያየን፥ የዚህ አይነት ነገር በድምጽ መስማቱ በእርግጥ ብዙም አይገርምም።
የሆነው ሆኖ፥ ብአዴንም የሰኔው ቀውስ ሳያጋጥመው በፊት፥ “ወቅቱ አሁን ነው፥ ሀገራዊው ህገመንግስትን ለማሻሻል አቅም ቢጠፋ እንኳን፥ የመደራደሪያ አቅም ለመፍጠር ሲባል፥ “የአማራ ክልልን” ህገመንግስት እንደሌሎች ክልሎች ከ Demo-Centric ወደ Ethno-Centric ቀይሩት” ብለን ብንወተውትም፥ ገድለ-አብይ አህመድንና ተአምረ-ለማ መገርሳን ሲደግሙ ኖረው ፥ ከድርጅታዊ ቀውሳቸው ማግስት እንኳን ለህዝብ ሊተርፉ፥ እነሱም በአደባባይ በጎጥ ተቧድነው የአብይ ሎሌ ለመሆን የሚሽቀዳደሙ አበጋዞች ሆነው አረፉት።
ለማንኛውም፥ ከላይ በተዘረዘሩት ሶስት ተመጋጋቢ ምክንያቶች የተነሳ፥ “ከአማራ ክልል” ውጪ የሚኖረው ህዝባችን፥ የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ የኦሮሙማ መንግሥት  አማራን የሚያጠቃበት ስስ ብልት እንዲሆን ሰፊ ዕድል ሰጥቶታል።
በመሆኑም ላለፉት ሁለት ዓመት ከአምስት ወራት፥ የአብይ አህመድ መንግስት፥ ከለገጣፎ እስከ መተከል ፥ ቀውስን በመጥመቅና አማራን በማያቋርጥ እሳት ላይ በመጣድ፥ አማራ እንደህዝብ አንዱን ቀዳዳ ደፈንሁ ሲል፥ ሌላ ቦታ እየተቀደደ፥ ከአንድ የቀውስ ማጥ ወደሌላ የቀውስ ማጥ ሲዳክር፥ አብይ አህመድ መራሹ መንግስት፥ ፋሽስታዊ የኦሮሙማ ፕሮግራሙን፥ ያለአንዳች ተግዳሮት በማስፈፀም ላይ ይገኛል።
እርግጥ ነው፥ አማራን በቀውስ አረንቋ የመንከር ዘመቻው በዋናነት “የአማራ ስስ ብልት” ብለው የሳሉትን “ከአማራ ክልል” ውጪ የሚኖረውን ህዝባችንን ኢላማ ያደረገ ቢሆንም፥ የኦህዴድን ወታደሮች፥ የኦነግ አርማን በማስያዝ በአጣዬና በምድረ-ገኝ ወታደራዊ ዘመቻ በማድረግም ህዝብን አፈናቅለው አማራን እንደህዝብ ዕረፍት በመንሳት፥ እኛ የበቀደሙን የመተከል የዘር ፍጅት ጨምሮ ከኦሮሞ-ሰራሽ ቀውስ ጋር ስንታገል፥ እነሱ እዚህ ግባ የሚባል ተግዳሮት ሳይገጥማቸው ፋሽስታዊ ህልማቸውን እውን ለማድረግ ርቀው እየተጓዙ ይገኛል።
በደቡብ ክልል የጌዲዮ ዞን በኦሮሙማ የተሰለቀጠችው በቀውስ ጠመቃ ታክቲክ ነው፤ ቤኒሻንጉል የቋንቋ ፖሊሲውን የቀየረው፥ ለቤኒሻንጉል ፥ ቀውስን አቦልና በረካ አድርገው ግተውት፥ አመራሮቻቸውን በሁለት ዙር ደፈጣ ገድለው ነው።
ቅድመ ኮሮና የነበረውን ጊዜ እንደምናስታውሰው፥ አብይ አህመድ ከሀገር ሲወጣ፥ ሀገሪቱ ውስጥ ቀውስ የሚፈጠረው በድንገት የሚፈጠር ከመሰለህ ተሳስተሃል።
ዝርዝር ዕቅድ ለቀውስ አስፈፃሚው አካል ሰጥቶ፥ እሱ “ሽርሽር” ይወጣል፥ አማራ ሰለባ ይሆናል፣ እኛ ስንንጫጫ ከጀርባችን በለሆሳስ አላማቸውን ያስፈፅማሉ።
ሀጫሉ የሚባለውን ዘፋኝ በገደሉት ማግስት፥ በአማራ ላይ ያንን ሁሉ ሰቆቃ እያወረዱ፥ አማራ ሲታረድና በሩቅ ያለነውም ስንጮህ፥ አጅሬዎቹ ከነበረው ጊዜ ሁሉ በከፋ ሁኔታ የአዲስ አበባን መሬት እንደአንበጣ እየወረሩት ነበር።
ላለፉት ሁለት አመት ከአምስት ወራት ውስጥ በሀገሪቱ ውስጥ በተለይም በአማራ ላይ የደረሱት የዘር ማጥፋትም ይሁኑ ማፈናቀሎች፥ በድንገት አልያም “ያረኮረፉ በለውጡ ምክንያት ጥቅማቸው የተነካ ቡድኖች” የፈፀሙት ሳይሆን፥ አብይ አህመድ መራሹ ፋሽስታዊው የኦሮሞ ቡድን፥ እኩይ የፖለቲካ አላማውን ለማስፈፀም፥ ቀውስ መፍጠርን እንደስልት ስለሚጠቀምበት ብቻ ነው!!!
“A crime is like any other work of art. Every work of art, divine or diabolic, has one indispensible mark —the center of it is simple, however much the fulfillment may be complicated. . . .
“Every clever crime is founded ultimately on some one quite simple fact—some fact that is not itself mysterious.
The mystification comes in covering it up, in leading men’s thoughts away from it.”
G. K. Chesterton’s legendary “Father Brown” in The Queer Feet.
በኦህዴድ የበላይነት የሚዘወረው መንግስታዊው የኦሮሙማ ቡድን፥ እንደአደጋ የሚያያቸውን አልያም potentially አደጋ ሊሆኑኝ ይችላሉ የሚላቸውን ሀይሎች ከሚመታበት ስልት አንዱ፥ ከጀርባ ሆኖ በስውር እጁ (Assassin tactic)  እነዚህ ሀይሎችን በተቀናቃኝና ተፎካካሪ ቡድኖች በመከፋፈል፥ እርስበእርስ እንዲመታቱ በማድረግ ማጠፋፋት፣ ማዳከምና፥ የተዳከሙ ተፃራሪ ቡድኖችን በእግሮቹ ስር በማስገባት እንደአስፈላጊነቱ በየተራ እያፈራረቁ በማቅረብና በማራቅ ተገዢ ማድረግ ነው።
ኦህዴድ መራሹ ፋሽስታዊው የኦሮሙማ ቡድን ፥እርስ በእርስ የማበላላትን ስልት እንደ ፖለቲካ ግብ ማስፈፀሚያ እንደሚጠቀም መረዳት ለሚፈልግ ሰው፥ “ሾልኮ ወጣ” የተባለውን የሽመልስ አብዲሳን ንግግር መለስ ብሎ ማዳመጥ ይችላል። በንግግሩ ውስጥ በአዲስ አበባ ጉዳይ አዋጪ የሆኑና ያልሆኑ ስልቶችን ሲዘረዝር፥  “በፊንፊኔ ጉዳይ፥ እርስበርስ እንዲመታቱ ማድረግ አንችልም” ይላል። ያው በአዲስ አበባ ውስጥ እርስበርስ ለማበላላት የሚሆን ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ ነው ይህ ስልት ውድቅ የሆነው።
ነገር ግን ተሞክሮ ያልተሳካባቸውና የተሳካባቸው ቦታዎች መኖራቸውን ደግሞ ልብ ይሏል።
በትግሬ ክልል ወያኔ ትግሬን ለመከፋፈል፥ አብይ አህመድ አንዴ ሽማግሌና ወጣት፣ ሌላ ጊዜ “ደብረፅዮንን እርዱት” እያለ የጀማሪ ሙከራውን ቢያደርግም፥ “እባብ ለእባብ” ሆኖ ጠብ የሚል ነገር ሳያገኝ ቀርቷል። በሌላ በኩል ሶማሌዎችን በሙስጠፌና በአህመድ ሸዴ አቧድነው ሊያበላሏቸው ያደረጉትን ጥረት፥ በሳሎቹ ሶማሌዎች ቀድመው ነቅተው ሙከራውን አክሽፈውታል።
በአንፃሩ የአብይ አህመድ ኦሮሙማ ስውር እጅ እርስበእርስ የማበላላት ስልት ፍሬ ያፈራው “በአማራ ክልል” ነው። ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያትም የጠላት ብአዴን ጥንተ ስሪት ነው። ይህም ሲባል “ለውጥ” የሚባለው ነውጥ ሲመጣ፥ ጠላት ብአዴንን ለ27 ዓመታት በምስለኔነት በባርነት ሲመሩ የነበሩት በረከት ስምኦንና መሰሎቹ ገሸሽ ሲደረጉ፥ ትናንት ዋና ተላላኪና የወያኔ ትግሬ ዱቄት ተሸካሚ የነበረው በኋላም ራሱን “የለውጥ መሪ” ብሎ የሚጠራው ሀይል ከቅይዱ ተፈታ። የተፈታው ግን ከወያኔና ከወያኔ ምስለኔዎች የእነበረከት ጥርነፋ እንጂ በአዕምሮ የተፈታ አልነበረም። ስለሆነው ህዝብን አንድ አድርጎ በፍጥነት የዘመናት የህዝባችንን ጥያቄ ለመፍታት ከመሄድ ይልቅ፥ ለዘመናት ሲላላኩ እንጂ የራሳቸውን አጀንዳ ቀርፀው ያንን በተጠና መልኩ የማስፈፀም የስነልቦና ዝግጅትም ይሁን ብቃት ባለመኖሩ፥ “ለውጥ” ያሉት ነገር ሁሉ፥ paranoid political climate ፈጠረባቸው። ከዚያም rivalry groupሆነው በየፊናቸው ሲጠዛጠዙ፥ ሀይል ለማሰባሰብ ሲዳክሩ፥ አብይም የአቃፊ-አግላይ ሚናውን subtly ከተጫወታት በኋላ፥ ድርጅታዊ ቀውሳቸውን ከቢሮና ከፌስቡክ አውርደው፥ የአደባባይ ታሪክ አደረጉት። እነሆ ከዚያ ጊዜ ወዲህም፥ ከውጪ ሲታይ ያለ ይምሰል እንጂ፥ ጠላት ብአዴን፥ በየጎጣቸው በተሰለፉ አበጋዞች የሚመራ፣ አጋጣሚው ቢመቻችም የየጎጣቸውን ድርሻ ይዘው ጋብቻቸውን ለማፍረስ እያሰፈሰፉ የሚገኙ ሲሆን፥ ይህ internal cohesion አጥቶ የዕውር ድንብሩን እየሄደ ያለ ስብስብ፥ ዕድሜውን የሚያራዝመው፣ተቀናቃኜ በሚለው የራሱ አካል ላይ ነጥብ ለማስቆጠርም በየፊናው የአብይ አህመድን ጫማ በመላስና ማን የበለጠ ተላላኪ ነው በሚል ነው።
ከዳግም ምስረታዋ ጀምሮ ሶስትና አራት ትውልድ በአዲስ አበባ የኖርነው እንዲሁም “ከአማራ ክልል” ውጪ ተበትኖ የሚገኘው አማራዊ በቁሙ ተሽጦ፥ ላለፉት ሶስት አመታት ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የተፈፀመበት፥ አማራዊ የሆነ መንግስት ሌላው ቢቀር፥ “የአማራ ክልል” በሚባለው ቦታ አለመኖሩ ነው።
2. ድምፅ-አልባ ወረራ ( Silent Invasion )፦ 
የኦሮሙማ ድምጽ-አልባ ወረራ ስልት፥ ከቦታ ቦታ ይለያያል። ወረራ እንደሚፈፅሙበት አካባቢ አመቺነት፥ ስልቱም በዚያ ልክ ይቃኛል። የተወሰኑትን በምሳሌነት መመልከት ተገቢ ይመስለኛል።
ሀ. ጋምቤላ፦ ኦሮሙማ በጋምቤላ ላይ ከፍተኛ ወረራ እየፈፀመ ያለው፥ በኢንቨስትመንት ስም ነው /Invasion by means of Land grabbing/. ትናንት ወያኔ የጋምቤላን መሬት ለህንዱ ካራቱሪ፣ ለሳዑዲው፥ ሳዑዲ-ስታር ቸብችቦት ሲያበቃ፥ የተረፈውን ደግሞ እልፍ የትግሬ የአየር በአየር ነጋዴ በሜካናይዝድ የግብርና ኢንቨስትመንት ስም ተቀራምቶ፥ አንዲት ስንዝር ሳያርስ፥ በመሬቱ ከልማት ባንክ ገንዘብ ተበድሮ ከሀገር ያሸሸ ሲሆን፥ ተረኛው ኦሮሙማ ደግሞ፥ በግብርና ኢንቨስትመንት ስም እልፍ የኦሮሙማ ካድሬና ነጋዴዎች፥ የጋምቤላ መሬትን ከመቀራመት አልፈው፥ በወሰዱት መሬት ላይ በስራ ሰበብ በርካታ ኦሮሞዎችን እያሰፈሩ ሲሆን፥ ሽመልስ አብዲሳም የጋምቤላ ክልል ባለስልጣናትን ምክር በሚመስል ማስፈራራት፥ ኦሮምኛን በጋምቤላ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ አካትተው እንዲሰጡ መመሪያ ሰጥቶ ወደ ትግበራ ተገብቷል።
2. ጉራጌ፦ ኦሮሙማ በጉራጌ ዞን ወረራውን እያስፈፀመ ያለው ባህልን በሀይል በመጫን /Invasion by Culture Imposition/ ነው። “ጉራጌ ከመቶ ሃምሣ አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢሬቻን በዓል አከበረ” የሚለው ዜናን ልብ ይሏል።
3. ቤኒሻንጉል፦ ኦሮሙማ በቤኒሻንጉል ወረራ እያደረገ ያለው፦
ሀ. እጅ በመጠምዘዝ (Coercion)፦ አስቀድመው የኦሮሙማን ወደ ቤኒሻንጉል መስፋፋትን የተቃወሙ የቤኒሻንጉል አመራሮች፥ በኦህዴድ የደፈጣ ተዋጊ ወታደሮች ሰለባ እንዲሆኑ ከተደረገ በኋላ፥ ቀሪው እጁ ተጠምዝዞ በፍርሃት፥ የተባለውን እየፈፀመ ይገኛል።
ለ. በማማለል (Seduction)፦ እጁን የተጠመዘዘው አመራር፥ ይበልጥ እንዲለዝብ “የቤኒሻንጉል ክልል” የበጀት ድጋፍ “ከኦሮሚያ ክልል” እየተደረገለት የኦሮምኛ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ተካትቶ፥ በክልሉ የሚኖረው ህዝብ ሁሉ እንዲማር የማድረግ ሥራ በስፋት እየተሰራ እንዳለ የአደባባይ ምስጢር ነው።
4. ጌዲኦ፦ የጌዲኦ ዞን ከፊል ወረዳዎች በኦሮሙማ ተስፋፊዎች ወረራ የተፈፀመባቸው፥ በሀይል ነው (Invasion by armed forces). የተቀረው የጌዲኦ ይዞታም ቢሆን፥ ሲዳማ ራሱን የቻለ ክልል ከሆነ ወዲህ ከሌላው የደቡብ ክልል ተቆርጦ የቀረ የደቡብ ክልሉ “ካሊኒንግራድ” በመሆኑ፥ የጊዜ ጉዳይ እንጂ፥ ሙሉ በሙሉ በኦሮሙማ መሰልቀጡ አይቀርም።
5. አዲስ አበባ፦ የአዲስ አበባችን ወረራ እንዴት እየተፈፀመ እንደሆነ፥ ሁሉም ሰው የሚያውቀው ስለሆነ ያንን መዘርዘር፥ አንባቢን በከንቱ ማድከም ስለሚሆን፥ በዚሁ እንቋጨው።
ጊዜ እንደፈቀደ፥ የመጨረሻውን ክፍል በቀጣይ  እናያለን። መልካም ጊዜ!!!
Filed in: Amharic