
እና ጎሜዝ ስለ እነ እስክንድር ነጋ ዶ/ር አብይን ተማጸኑ

ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)
በምርጫ 97 ላይ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢ ቡድንን የመሩት ፣የምርጫውንም ነጻ እና ገለልተኛ ያለመሆኑን በቅድሚያ ያጋለጡት አና ጎሜዝ “የአሸባሪነት ክስ” የተመሰረተበት የባልድራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች እና ሊቀመንበር የሆነው እስክንድር ነጋ እንዲፈታ ጥሪ አቀረቡ ።
በህብረቱ ውስጥ እኤአ ከ2004 እስከ 2019 ያገለገሉት የቀድሞዋ የህዝብ እንደራሴ አና ጎሜዝ በወዳጆች መረብ ትዊተር ገጻቸው ላይ በሰፈሩት አጭር የተማጽኖ ማስታወሻ”እስክንድር ነጋ ዳግም በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈታ መወትወታችን በእጅጉ ያማል፣ያሳዝናል።ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ሆይ እባክዎትን እስክንድር ነጋን ነጻ ያውጡት ፣ዜጎችን በህገወጥ መንገድ በጅምላ የማሰሩ እርምጃም ይቁም” ሲሉ ተማጽነዋል።
በበርካታ ኢትዮጵያኖች ዘንድ “ሀና ጎበዜ ” በሚል የሙገሳ ስም የሚታወቁት ፖርቱጋላዊቷ አና ጎሜዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ በተለይ በሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ በግንባር ቀደምትነት ሲሞግቱ እና አቋማቸውን በግልጽ በእየመድረኩ ላይ ሲያሳውቁ ከነበሩ ጥቂት ምእራባዊያን ባለስልጣናት መካከል አንዷ እንደነበሩ እና ይህም አቋማቸው በቀድሞው የህውሃት/ኢህአዲግ አገዛዝ ለከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና ሰለባነት እንደተዳረጉ እና የቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ ሳይቀሩ በኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ላይ በቀጥታ እንደ ወረፏቸው ይታወሳል።
(
………………………… …..
This is so painful! So sad we need to use the hashtag #FreeEskinder again in #Ethiopia today. Please,
@abyi
@PMEthiopia
@AbiyAhmedAli
liberate Eskinder Nega & stop jailing people unlawfully.