>

ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በመዋቅሩ ተደራጅተው ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!  (አባይ ነህ ካሴ)

ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በመዋቅሩ ተደራጅተው ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!

አባይ ነህ ካሴ

* የሕግ ባለሞያዎች፥ በሀገር ውስጥ እና በውጪ አህጉረ ስብከት የቤተ ክርስቲያን ውክልና እየተሰጣቸው ግፈኞችን እንዲፋረዱ ወሰነ!
• በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመሩ ኹለት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ሰላም መንግሥትንና የፖሊቲካ ኃይሎችን በቀጥታ ያነጋግራሉ፤
• ሕዝብ እየተገደለና አገር እየጠፋ ያለው፣ በፖሊቲካው ትርምስ በመኾኑ፣ በቅራኔ የተፋጠጡ ኃይሎች ሰላም እንዲያወርዱ ይማፀናሉ፤ ለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ካሳን፣ ለተፈናቀሉት መመለስን፣ በሐሰት ተከሰው በእስር ለሚንገላቱት መፈታተን፣ ለተደፈሩት ይዞታዎች መከበርን እንዲያነብር መንግሥትን ይጠይቃሉ፤
• የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን የመዘርጋቱ ሥራ፣ ቀደም ሲል በተላለፈው ውሳኔ መሠረት በአስቸኳይ እንዲጀመር፣ ምልአተ ጉባኤው ጠቅላይ ጽ/ቤቱን አሳስቧል፤
• ለድንገተኛ አደጋዎች እና ችግሮች ፈጣን ምላሽ እና ርዳታ የሚሰጥ አስተባባሪ አካል፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በማእከል እንዲቋቋም መመሪያ ሰጥቷል፤ በተለይ የውጪ አህጉረ ስብከት፣ ፋይናንሳዊ፣ ማቴሪያላዊ እና ሞያዊ ድጋፎችን እንዲያስተባብሩለት ተስማምቷል፡፡
Filed in: Amharic