>

የጀመርኩትን ስራ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ፤ ሆኖም በግልጽ  ጥሪ አልተደረገልኝም!!! (ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ)

የጀመርኩትን ስራ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ፤ ሆኖም በግልጽ  ጥሪ አልተደረገልኝም!!!

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
“የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ነበርኩ!
 ይሄ ዕዝ የኢትዮጵያ ልጆች ስብስብ ነው! ሆኖም ህውሃት መሳሪያ ለመንጠቅ ሲል ጨፈጨፋቸው
 –
የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጥሩ መሪ ይፈልጋል። በተደራጀ መንገድ የህውሃት ቅስም መሰበር አለበት። ይሄ ካልሆነ ሀገራችን ሰላም አታገኝም። የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ነበርኩ። ይሄ ዕዝ የኢትዮጵያ ልጆች ስብስብ ነው። ሆኖም ህውሃት መሳሪያ ለመንጠቅ ሲል ልጆቹን ጨፈጨፋቸው። ነገ የተጨፈጨፉት ልጆች ስም ዝርዝር ሲገለፅ ብዙ ቁጣ ይቀሰቅሳል።
ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ የምፈልገው የልዩ ሃይል መሪ መሆን ነው። የጀመርኩትን ስራ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ። ሆኖም officially ጥሪ አልተደረገልኝም።
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ – ለበለስ ሚዲያ የተናገሩት
Filed in: Amharic