የግምባሩን ውሎ በጨረፍታ…!?!፦
ታዬ ቦጋለ
1 * አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ፦ የሙለር ሪልስቴት ባለቤት እና ሌሎች 24 ሰዎች ትላንት አመሻሹ ላይ ገቢ ተደርገዋል።
2 * ወንበዴዎቹ የባንክ ዘረፋዎችን አጠናክረው ቀጥለዋል።
3 * ሽፍቶቹ፦ የፀጥታ አካላትን፣ የመነኩሴ፣ የቄስ፣ የሼክ፣ የአሮጊት፣ የአእምሮ ህመምተኛ ወዘተርፈ አሳች አለባበስ በመልበስ በየስርቻው ለስለላ ሲልከሰከሱ እየተያዙ ነው። በቁሬያለው፣ ልዌጭ፣ መወልወያ ያለው… ተሰልፈው በደደቢት የተበላበት ‘ሙድ’ ለመሰለል እየተጋጋጡ ይገኛሉ። በዐይነ ቁራኛ ተመልከቷቸው፤ ከህዝብ የሚሰወር ነገር የለምና!
4 * አዲስ አበባ ከሚገኙ የአባይ ፀሀዬ (ስኳሬ) ሆቴሎች አንዱ በቁጥጥር ስር ውሏል። ከኢትዮጵያ ህዝብ ተዘርፈው የተገሸሩ ታላላቅ ህንፃዎች ተሽጠው፤ ትግራይ ስትረጋጋ ገንዘቡ በተዘረፉ ባንኮች እንዲገባ እንመክራለን፦ እሾህን በእሾህ!
5 * የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፦ ደደቢት አክሱም አላማጣ ማይጨው አዲግራት ፀለምት ማይፀብሪ አዳርቃይ… ወንበዴዎችን በመደምሰስ ላይ ሲሆን፤
ዳንሻ፣ በአከር፣ ንጉሥ፣ ሁመራ፣ ማይካድራና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የመከላከያ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸዋል።
6 * በጁባ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ የነበረው ግደይ ኃይሌ ወደኢትዮጵያ እንዲመለስ የአየር ትኬት ከተቆረጠለት በኋላ እዚያው ተሸብልሏል።
7. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የትኛውንም የውጭ አሸማጋይ እንደማይቀበሉ ትላንትም መረር ብለው በተለያዩ አውታሮች አስታውቀዋል። በተያያዘ ዜና እነደብረፅዮን “ስለነፍስ አደራድሩን” እያሉ ነው፤ ድርድር የለም ከየጎሬህ ወጥተህ እጅ ስጥ!
8. ወንበዴዎቹና ቡችሎቻቸው ኢትዮጵያን የማጥላላት የትዊተር ዘመቻ ከፍተዋል፤ አፀፋውን ለመስጠት ኢትዮጵያውያን ዛሬ የተጠናከረ የገፅታ ውበት ዘመቻ ይጀምራሉ። (የገፅታ ቅብ የሚለው ቃል አይመቸኝም፤ የሚቀባው ጥላሸት ወይስ ቀለም? ቀለሙስ እንዴት ይቀባል?)
የሶማሊ ክፍለሀገር ፕሬዚደንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ዑመር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቢሊኔ ስዩም እና በርካቶች በዓለማቀፍ ዘመቻው በተለያዩ ሚዲያዎች እውነታውን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ እየገለጡ ነው።
9. በርካታ የተሳኩ የአየር ድብደባዎች ተደርገዋል። ጀት ተመቶ ወደቀ የሚለው የእነባሪያቸው ረዳ ወሬ፦ “ግድቡ ተሽጧል” እንዳሉት ሁሉ ጠብደል ውሸት ነው።
10. አሜሪካ ዲሲ የተካሄደው ሰልፍ የአቦይ ስብሓት ነጋ ስርወ መንግሥት አባላት መሆኑ ተረጋግጧል።
ኢትዮጵያ ትቅደም!
አሸባሪ ወንበዴ ይውደም!