የኦነግ/ኦህዴድ ሰሞነኛው የፖለቲካ ቁማር :- “በኦሮምያ ስለምንጨፈጭፋቸዉ አማሮች ዝም በሉ! ማይከድራ ላይ ብቻ ጩሁ!”
ሸንቁጥ አየለ
* በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጀመረዉ አለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ እንዲከስም አሜሪካ በሚኖሩ ታዋቂ አርቲስቶች በኩል ኦህዴድ/ኦነግን ነጻ የሚያደርግ አዲስ ክስ ሊያስጀምር ነዉ
—————
* አዴፓ ከቻለ ፋኖን አድኖ ይገድላል ካልቻለ ሽምግልና በመላክ ይታረቅና ወደ እስር ቤት ይወረውርሃል !
* በአንጻሩ ኦህዴድ – በኦሮሚያ የሚኖሩትን የሌሎች ብሄሮች በኦነግ ስም ጠራርጎ ለማስወጣት – ቀን ከሌሊት ይተጋል በግፍ የሚጨፈጨፉ አማሮችን እንኳንስ ከፍጅት ሊያስጥል በክልሉ ያለ ወገናቸው እንዳይጮህላቸው ይፍናል!!!
——————
የኦነግ/ኦህዴድ ፖለቲካ ቁማር ምጥቀቱ ሲራቀቅ ኦሮሞ ክልል ላይ በአስር ሽህዎች ላይ የተፈጸመዉን እና እየተፈጸመ ያለዉን በአማሮች ላይ እየተከናወነ ያለዉን የዘር ጭፍጨፋ ባላዬሁም ያልፈዉና በማይከድራ በ452 አማሮች ላይ የተፈጸመዉን የዘር ጭፍጨፋ ግን አወገዝኩላችሁ ይለናል::
እንዴዉም በአለም አቀፍ ደረጃ የዘር ማጥፋት ክስ ለማድረግ ከአንዳንድ የአማራ/የኢትዮጵያ/ ታዋቂ አክቲቪስት/አርቲስት/ጋዜጠኛ ነን ከሚሉ ሰዎች ጋር እንቅስቃሴ ጀምሯል ::የኦነግ/ኦህዴድ/አቢይ የሚመራዉ ክልል የፖለቲካ ቁማር ጨዋታዉን በአዲስ ሰሞነኛ ዘይቤ ይዞ ከች ብሏል::ማይከደራ ላይ ብቻ አፍጥጥ::ሌላዉን የአማሮች የዘር ፍጅት ግን እኛን ስለሚያስወነጅል እርሳዉ የሚል የሞኝ ብልጥ የፖለቲካ ቁማር ይዞ ከች ብሏል::እነ ታዋቂ አርቲስትም በዚሁ ሰሞነኛ ቁማር ተበልተዋል::እናም የኦህዴድ/ኦነግ ቆሻሻ የወንጀል ጆንያ ለመሸከም ደፋ ቀና እያሉ ነዉ::
በዚህ የማይከድራዉ የዘር ፍጅት የሚከተሉትን መሰረታዊ ሀቆችን ለመካድ/ለመገልበጥ ተነስቷል::
1.በኦሮሞ ክልል የተደረጉ የዘር ፍጅቶችን በሙሉ በማስረሳት ኢትዮጵያዉያን ብሎም አለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አማራዉ ሙሉ ትኩረቱን በማይከድራዉ ጭፍጨፋ ላይ ብቻ እንዲያደርግ ከፍ ያለ ቁማር መጫወት ዋናዉ አላማ ነዉ::እንዴዉም አንዳንድ ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን የማክድራዉ ጭፍጨፋ በ452 አማሮች የዘር ፍጅት መወሰኑ አበሳጭቷቸዋል ነዉ የሚባለዉ::በሽዎች ቢሆን ነበር የበለጠ የሚጪህዉ የሚል በህዝብ ደም ላይ የሚቆመር ሂሳብ ይዘዉ ተነስተዋል ነዉ የሚባለዉ::
2. በኦሮሞ ክልል በተዋህዶ እምነት ተከታዮች:በአማራ ማህበረሰብ እና በልዩ ልዩ ነገዶች ላይ በአንድ ጊዜ ብቻ ከሃያ ሽህ በላይ ኢትዮጵያዉያን ላይ የዘር ፍጅት በኦህዴድ/ኦነግ መሪነት መደረጉን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዘር ማጥፋት ክስ በኢትዮጵያ መንግስት ብሎም በኦህዴድ/ኦነግ እና በህዉሃት ላይ በጥምረት ተመስርቷል::ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን መሪዎች ግን ይሄን ክስ እንዲቀር ለማድረግ ከላይ በተጠቀሱት አንዳንድ የአማራ/የኢትዮጵያ/ ታዋቂ አክቲቪስት/አርቲስት/ጋዜጠኛ ነን ባይ ሰዎች የሚመራ እና የማይከድራዉን ፍጅት ብቻ የሚያካትት የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠቅስ የዘር ፍጅት ክስ ለመመስረት እየተንቀሳቀሱ ነዉ::
ይሄዉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪነት እየተንቀሳቀሰ ያለዉ አለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ክስ ጉዳይ ኦህዴድ/ኦነግን በጅጉ ስላሳሰበዉ ይሄን ክስ ለማስቀረት በታዋቂ አርቲስቶች/አክቲቪስቶች/ጋዜጠኞች በኩል የማይከድራዉን ጭፍጨፋ ብቻ የያዘ የአለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ክስ ለመመስረት ብዙ ዶላሮች መድቧል::
3.ኦህዴድ/ኦነግ በኦሮሞ ክልል አሁንም በዬቀኑ እንደ ጎርፍ የሚፈሰዉን የአማራ ህዝብ ደም : በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገገዉን የዘር ፍጅት ሁሉ አልተከሰተም እናንተ ማተኮር ያለባችሁ በማይከድራዉ ጭፍጨፋ ላይ ብቻ ነዉ የሚል ከባድ እንቅስቃሴ ዉስጥ ነዉ::
መቼም የኦህዴዳዉያንን/ኦነጋዉያንን የተራቀቀ የፖለቲካ ቁማር ጨዋታ አልቻልነዉም አይደል? እነ አርቲስት እንትና በኦነጋዉያን ቁማር ለሁለተኛ ጊዜ ተጠልፈዉ እና በኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን እግር ስር ተንከባለዉ እዉቅናቸዉን በአማራ ህዝብ ደም ለወንጀለኛዉ ኦነግ/ኦህዴድ ንጽህና ማወጃ ሲያዉሉት መንጋዉም አብሮ በእልልታ ከበሮ እየደለቀ ይጨፍር ይሆን?
አሁን ድረስ በመላ ሀገሪቱ የሚደረጉ በተለይም በኦሮሞ ክልል የሚደረጉ የዘር ፍጅት ተባብራችሁ እየመራችሁ ያላችሁ ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን እነ ታዋቂ አርቲስቶችን በገንዘባችሁ መግዛት እና ለአንድ ሰሞን መንጋዉን በማደናበር የተራቀቀ ቁማር መጫወት ትችሉ ይሆናል::
ሆኖም ማወቅ ያለባችሁ ቤያንዳንዱ ቀበሌ በወለጋ: በሻሸሜኔ: በአርሲ:በሃረር: በድሬዳዎ: በባሌ:በጅማ እና በልዩ ልዩ ቦታዎች የሚፈሰዉ የአማራ ደም: በማይከርዳ የፈሰሰዉ የአማራ ደም: በመተከል : በጉራ ፋርዳ የሚፈሰዉ የአማራ ደም ወደ ቅዱስ እግዚአብሄር እየጮህ ነዉና የእግዚአብሄርን ፍርድ ከቶም አታመልጡትም::በእግዚአብሄር ከመቀጣትም አትድኑም::የተቀደሰዉን የእግዚአብሄር ህዝብ : እግዚአብሄር ህዝቤ ያለዉን ኢትዮጵያዊ ህዝብ ደም አፍሣችኋል እና እግዚአብሄርን በፖለቲካ ቁማራችሁ ማታለል አትችሉም::ስለዚህም በዘር ማጥፋት ወንጀል ከመጠዬቅ አትድኑም::የናንተ በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠዬቅስ ቀላሉ ነዉ::ብዙ ተያያዥ ዳፋ ያለዉ ጥፋት ማስከተላችሁም እሙን ነዉ::
የሆነ ሆኖ ታዋቂነታችሁን ለኦህዴድ/ኦነግ የፖለቲካ ቁማር ልትሸጡ የተነሳችሁ በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ ታዋቂ አርቲስት/ጋዜጠኛ/አክቲቪስት ነን የምትሉ ሰዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጀመረዉን ክስ ለማቋረጥ እንቅስቃሴ ማድረጋችሁን ብታቆሙ ጥሩ ነዉ::አለዚያ በኦህዴድ/ኦነግ የፖለቲካ ቁማር መጠለፋችሁ እና ከህዝባችሁ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መነጠላችሁ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሄር የቅጣት መሳሪያም ከዘር አጥፊዎች ጋር መቀሰፋችሁ እሙን ነዉ:: ሃሃሃሃ… ለካ ኦነግ/ኦህዴድ እፊታችሁ የከመረዉ ዶላር ከእግዚአብሄር እዉነት አጣልቷችኋል::
ለማናዉም ኦነግ/ኦህዴድ የፖለቲካ ቁማሩን ከፍ በማድረግ የዘር ማጥፋት ክሱ ኦነግ/ኦህዴድን እንዳያካትት አሜሪካን ከሚኖሩ ከታዋቂ አርቲስቶች ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል::በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የተጀመረዉ አለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስም እንዲከስም በታዋቂ አርቲስቶች በኩል ቁመራዉን አጠናክሮ ቀጥሏል::
በነገራችን ላይ የነዚህ ታዋቂ አርቲስቶች/ጋዜጠኞች/አክቲቪስቶች ዝርዝር በቀጣይ በዝርዝር እናሳዉቃለን::ከኦነግ/ኦህዴድ ጋር የሚያደርጉትን የፖለቲካ ቁማርም እንዲያቆሙ ሽመልስ አብዲሳ እንዳለዉም ህዝብን convince/confused ማድረጋቸዉንም እንዲያቆሙ እናሳስባለን::