የደራ ተፈናቃዮች እምባ…!!!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
ዛሬ የባልደራስ ቢሮ በደራ ተፈናቃዮች ተሞልቶ ነበር። ሀፃናት፣እናቶች፣አባቶች እያነቡ፣ ኧረ በቀያችን ሰላም አጣን። አርሰን ነግደን መብላት አልቻልንም። ደራ የሽፍቶች ዋሻ ሆነ። መንግስት አስጨረሰን። ወየው ደራ ወየው…. እያሉ መሪር ብሶታቸውን አሰሙን።
አያሌ የደራ አማሮች ባልደራሶች ድረሱልን…… ድምጽ ሁኑልን….. እያሉ ጮሁ። የእነዚህ ወገኖች ጉስቁልና ከፊታቸው ገጽ ላይ ይነበባል። መንግስት ይሄ ሁሉ ሰው ከጉንዶመስቀል ወረዳ እየተፈናቀለ መከራውን ሲያይ ዘወር ብሎ አለማየቱ ብቻ ሳይሆን የችግሩም አካል ነው። እነዚህ የደራ አማሮች የደረሰባቸው በደል ብዙ ነው። በሽፍታ ከቀያቸው ከተፈናቀሉ በሁዋላ እንደተፈናቃይ የሚረዳቸው የለም። ስለሆነም በየመንገዱ ለልመና ተዳርገዋል። ደሮች ላይ የሚደርሰው በደል ለከት የለውም። ኢትዮጵያውያን ለነዚህ ወገኖቻችን ድምጽና ጠበቃ መሆን አለብን። እነዚህ ወገኖች የደረሰባቸውን ዝርዝር በደል በጋዜጣችን ላይ ይዘን እንቀርባለን። ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ ድጋፋችሁ እባካችሁ አይለያቸው።