>

ጥቂት መረጃ ትግራይ ስላለው ሁኔታ  (ግርማ ካሳ)

ጥቂት መረጃ ትግራይ ስላለው ሁኔታ

ግርማ  ካሳ

ወገኖች  አክሱም፣ አድዋ ሰላም ነው፡፡ በአክሱም ብዙ ዉጊያ  አለነበረም፡፡ ከተማ ውስጥ አንዲት ጥይት አልተተኮሰም፡፡
በአድዋ ምን አልባት በሁመራ/ማይካድራ ከነበረው ቀጥሎ ጠንካራ የሚባል ዉጊያ ነው የተደረገው፡፡ ከሁለቱም ወገኖች ብዙ ወገኖች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በብዛት የሞቱት ግን በሕወሃት ልዩ ኃይሉ ውስጥ የነበሩ የትግራይ ወጣቶች ናቸው፡፡ ያሳዝናል፡፡  የሕወሃት መሪዎች ልጆቻቸውን አሜሪካና አውሮፓ ልከው በድሃው የትግራይ ወጣት ሕይወት በዚህ መልኩ ነው ቁማር የተጫወቱት፡፡
ብዙ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት እጃቸውን ሰጥተዋል፡፡ የቆሰሉትም  ከቆሰሉ ከመከላከያ አባላት ያልተናነሰ ሕክምን እየተደረገላቸው ነው፡፡
በከተማ ዳር ከነበረው ጦርነት ባለፈ አድዋ ከተማም ልክ እንደ አክሱም ሰላም ነው፡፡ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የደረሰ አንዳች ጥቃት፣ የተወረወረ አንዲት ጠጠር የለም፡፡
ዛሬ ከወደ ራያ ቆቦ አንድ ጆሮ ጭው የሚያደርግ መረጃ ደርሶኛል። ህወሓት በራያ ግንባር ከሰሞኑ ልክ እንደማይካድራው አይነት ዘግናኝ መርዶ ሳታሰማን አትቀርም እየተባለ ነው። በራያ ንፁህ ዐማሮች ናቸው የተባሉትን በሙሉ ህወሓት ለቃቅማ ወደ መታረጃ ከምፖች መውሰዷን ከሥፍራው አምልጠው የመጡ ዐማሮች ተናግረዋል ተብሏል።
ውጊያው ተጀምሯል። እናም ህወሓት መሸነፌ ካልቀረ በማለት በራያ ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ለመፈጸም መዘጋጀቷ ነው የሚነገረው።
የሚገርመው ነገር ገና ውጊያው ከመጀመሩ በራያ መስመር የሕወሃት ታጣቂዎች ምሽጋቸውን ጥለው እየሄዱ ነው፡፡ ራያ አላማጣ ምን አልባትም ዛሬ ወይ ነጋ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ወጣች የሚል ዜና ብትሰሙ አትደነቁ፡፡
ራያን እና ማይጨዉን አልፋችሁ ያለው እንደርታ ነው፡፡ በ እንደርታ  ሕዝቡ በህወሃት ላይ ተቃውሞ ለማሰማት እየተዘጋጀ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ ምን አልባትም መቀሌ መከላከያ ሳይመጣ ሕዝቡ ራሱ ከሕወሃት ነጻ ሊያወጣት ይችላል፡፡
Filed in: Amharic