>

ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በትግረኛ ያስተላለፉት መልዕክት

ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በትግረኛ ያስተላለፉት መልዕክት

 “ቀናት እድሜ ለቀሩት ጁንታ ቡድን ብላችሁ ህይወታችሁን ልትገብሩም ሆነ ደማችሁን ልታፈሱ
(ኢ.ፕ.ድ)
>>የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ የስግብግቡን ጁንታ ግብአተ መሬት ለመፈፀም በመጨረስ ላይ እንገኛለን፤
>>ጁንታው ቡድን በሁሉም አቅጣጫ ተከቧል፤ መውጫና መግቢያ አጥቶ ታፍኖ የሞት ጣር ላይ  ይገኛል፤
>>ባሁኑ ሰአት ስግብግቡ ጁንታው አመራር ለመስጠት በማይችልበት ደረጃ ደርሶ ይገኛል፤ ልጆችህ ያለ ምግብ እና ውሃ የሞት እራት እየሆኑ ነው ስለዚህ ልጆችህ ሂወታቸውን እንዳይሰጡ በፍጥነት አድን፤
>>የልጆችህ ሞት የጁንታውን እድሜ ለሰአታት ወይም ለቀናት ከማራዘም ውጪ ምንም ትርጉም የለውም፤
>>ሰው ለሃገር እና አለማ እንጂ ለጥፋት ቡድን ብሎ ሊሞትና አካሉ ሊጎድል አይገባም፤
>>ከትግራይ ህዝብ በላይ የጦርነትን አስከፊነት የሚያውቅ የለም፤ ጁንታው ቡድን ለራሱ አይሞትም አካሉም አይጎድልም ስለዚህ የልጆችህ ደም ለጁንታው ቁማር መጫወቻ መሆን የለበትም፤
>> የልጆችህን ውድ ህይወወት ለማትረፍና ከአንበጣ የቀረውን እህልህን ወደ መሰብሰብ  እንድትመለስ ተጋግዘን ጁንታውን ቡድን ቶሎ ልንጨርሰው ይገባል ብዬ ጥሪዬን አቀርባለሁ፤
>>የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ስግብግቡን ጁንታ ቶሎ መተን ወደ ልማታችን ልንመለስ ይገባል ስለዚህ እያደረከው እንዳለሀውም መከላከያ ሰራዊትን አግዝ፤
>>በመስዋእትነት የገነባሀትን ኢትዮጵያ አሁንም በማዳን ታሪክህን  እንድታድስ ውድ አገርህ ጥሪ አድርጋልሃለች፤
>>በተለያየ የአመራር እርከን ያላችሁ ሲቪል መሪዎች ያለን ተቃርኖ በህወሓት ተሰግስገው ካሉ ጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ስለሆነ ራሳችሁን ከዚህ ጁንታ እንድታርቁ ጥሪ ቀርቦላችኋል፤
>> መላው የትግራይ የፀጥታ አባላት በሙሉ ባለፉት ጥቂት ቀናት የገጠማችሁን አይታችኋል የስርአቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሞት እያሰገቧችሁ ነው፤
>>ጁንታው ቡድን አይደለም ደማቸውን ለመስጠት ሂወታቸውን ለመገበር ይቅርና የተኩስ ድምፅ ለመስማት እንኳ አይፈልጉም፤
>>ለዚህ ቀናት የቀሩት ጁንታ ቡድን ብላችሁ ህይወታችሁን ልትገብሩም ሆነ ደማችሁን ልታፈሱ በፍፁም ኣይገባም፤
>> ኢትዮጵያ በእውነተኛ ልጆችዋ ታሸንፋለች!
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Filed in: Amharic