>

ወቅታዊ የአቋም መግለጫ...!  (የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)

ወቅታዊ የአቋም መግለጫ…!

 የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
ፋሽሽትና  ኣሸባሪዎች ኣብይ ኣሕመድና ኢሳያስ ኣፈወርቂ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረሱት ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ የኣይበገሬው የትግራይ ህዝብ ኣንድነት ይበልጥ እንደ ኣለት የሚያጠናክር ነው!
የትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የፋሽሽትና አሸባሪዎች አብይ አሕመድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የተስፋፊው ታጣቂና ከሌሎች የውጭ ሃይሎች ጋር በቅንጅት ከሁለት ሳምንታት በፊት በኣየርና በምድር የጀመሩት ዘግናኝ ጭፍጨፋ አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡
ወራሪዎቹ ኣብይ ኣሕመድ፣ ኢሳያስ ኣፈወርቂና የተስፋፊው ታጣቂዎች፣ ኣፍሪካዊ ካልሆነ ኣገር ያገኙት የድሮን ድጋፍ እየታገዙ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ በአየርና በምድር የሚያካሂዱት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን ዜጎች፣ ለሞትና ለኣካል መጉደል እንዲሁም በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለመፈናቀል እና ለስደት ተዳርገዋል። በአጠቃላይ ወራሪዎቹ ኣረመኔዎች፣ በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄዱት ባሉት የዘር ፍጅት ስፍር ቁጥር የሌለው ሰብአዊና ቁሳዊ እልቂት እየደረሰ ነው፡፡ በመሆኑም ጥቅምት 29/2013 ዓ/ም መቐለ- መሰቦ በሚባል ኣከባቢ የኣሸባሪው ኣብይ ኣሕመድ ጀት ኣውሮፕላን ባወረደው የቦንብ ናዳ የኣንዲት የ8 ዓመት ህፃን ሂወት ኣልፏል፡፡ በርካታ ሰዎችም ቆስለዋል ለውቅያ የደረሰ እህልም ተቃጥለዋል፡፡ በተመሳሳይ ህዳር 4/2013 ዓ/ም ዛላምበሳ ከተማ ላይ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ተጨፍጭፈው ኣልቀዋል፡፡ በኣጭሩ ዛላኣንበሳ ከተማ ኣሸባሪውና ኣምባገነኑ ኢሳያስ ኣፈወርቂ በ1990 ዓ/ም እንዳወደማት ሁሉ፣  በተመሳሳይ በአሁኑ ወቅትም ይህንን ዘግናኝና የጥፋት ድርጊት አብይ ኣሕመድ፣ ከተስፋፊው ታጣቂ  ወራሪ ሃይል እንዲሁም ከሌላ ኣፍሪካዊ ካልሆነ ኣገር ጋር ተቀናጅተው ታሪክ ይቅር የማይለው ጭፍጨፋና ውድመት አድርሰዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የተነሱት ፋሽሽቶችና አሸባሪዎቹ ኣብይ አሕመድና ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጥቅምት 7/2013 ዓ/ም መቐለ ከተማን በኣየር በመደብደብ የሁለት ንፁሃን ዜጎች ህይወት ቀጥፈዋል፡፡ በርካታ የስቪል መኖርያ ቤቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚሁ የተዋጊ ጀቶች ድብደባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ወጣት የቆሎ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ክፍሎች ወድመዋል፡፡ ከቀናት በፊትም በኣምባገኑ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ትእዛዝ በሑመራ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ የኣካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም  ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡  በዚሁ በሑመራ ከተማ መስጊድ ጨምሮ የተለያዩ ማህበረ ኢኮኖሚ ተቋማት ወድመዋል፡፡
 ፋሽስት እና ኣሸባሪው ኣብይ ኣሕመድ ከዚህ በፊት በትግራይ ህዝብና የልማት ተቋማት ላይ ባደረገው የቦንብ ናዳ በንፁሃን ወገኖች ያደረሰው እልቂትና ያወደመው ንብረት፣ ኣይኔን ግንባር ያርገው በማለት ሽምጥጥ ኣርጎ እንደካደው ሁሉ፣ ህዳር 07/2013 ዓ/ም መቐለ ላይ ባካሄደው ዘግናኝ የኣየር ድብደባም እስካሁንዋ ሰኣት ባለው የተጣራ መረጃ የሁለት ንፁሃን ዜጎች ህይወት በከንቱ ኣልፈዋል፡፡ በሌሎች ወገኖችም የኣካል ጉዳት ደርሰዋል፤ ነገር ግን ህዳር 08/2013 ዓ/ም እንደተለመደው እውነት የሆነውን ነገር ውሸት የማለት ኣባዜ የተጠናወታቸው፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጀሮና ኣይኑ የተነፈጋቸው የፌደራል ሚድያዎች ኣይናቸው በጥቁር ጨርቅ ሸፍነው ትላንት መቐለ ላይ የተካሄደው የኣየር ድብደባ ውሸት ነው በማለት ሲዘላብዱ ውለዋል፡፡ ይህ ኣስነዋሪ እና ኣሳፋሪ ድርጊታቸው ዋነኛ መለያ ባህሪው  ውሸት የሆነው የጌታቸው ኣሸባሪ ኣብይ ኣሕመድና እነዚ የውሸት ቀረርቶ ኣዳማቂ ሚድያዎች፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያላቸው ንቀት በጋሃድ ያሳዩበት ነው። ሆኖም የትናንቱ የመቀሌ ድብደባ ኣለም ኣቀፍ ሚድያዎች በምስልና ድምፅ ኣስደግፈው በመላ ዓለም ስላሰራጩት ኣሸባሪው ኣብይ ኣሕመድና በእሱ ሳንባ የሚተነፍሱ ሚድያዎቹ ቅጥፈትና ቧልት እርቃኑ ወጥቶ በመጋለጡ ውርደት ከመከናብ ሊያመልጡ ኣልቻሉም።
ስለዚህ ይህንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየሰሙና እያዩ ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ እንዲሁም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሃይማኖቶቹ ተከታዮቹና በቤተ እምነቶች በኣጠቃላይ በንፁሃን ላይ እየደረሰ ያለው ህልቆ መሳፍርት የሌለው ዘግናኝ እልቂትና ግፍ እንዲሁም እየወደመ ያለው የመንግስትና የህዝብ ሃብት ኣስመልክተው በይፋ ሊያወግዙ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ የሃገር ሽማግሌዎችም ኣምባገነኑና ፋሽሽቱ ንጉስ ነኝ ባይ ኣብይ ኣሕመድ ከአረመኔው ከኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር እጅና ጓንት ሆኖው የትግራይ ህዝብ ጨምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች  ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋ እንዲያበቃ ፋሽሽቱ እና ኣሸባሪ ኣብይ ኣህመድን በድፍረት ይብቃህ አደብ ግዛ ሊሉት ይገባል፡፡
በተለይም እየደረሰ ያለው እልቂት ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆነው የኣማራ ህዝብ ኣሸባሪው እና ኣረመኔው ኣብይ ኣህመድና በስመ የኣማራ ህዝብ የሚነግዱ ሆድ ኣደር የፖለቲካ ደላሎች፣ የትግራይ ህዝብ ጨምሮ ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር እንድትጋጭ እና ደም እንድትቃባ፣ በአጭሩ ልጆቹህ በማወናበድና በማደናገር ሳይወዱ በኣስገዳጅ ጦርነት እሳት ላይ ማግደው በየኣውደ ውግያው ያሞራ ሲሳይ እንዲሆኑ ፈርደውባቸዋል፡፡ ስለሆነም ጠላትህ ልትለይ ይገባል፡፡ የትግራይ ህዝብ ጨምሮ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ያንተ ጠላት ኣለመሆናቸውም በውል ልትገነዘብ ይገባል። ይልቁኑም ዋነኛ ጠላቶችህ ጉያህ ላይ ተወሽቀው የፋሽሸቱ ኣብይ ኣሕመድ የንግስና እድሜ እንዲራዘም ቀንና ሌሊት የሚሰሩ በንፁሃን ደም የተጨማለቁ የኣሸባሪው ኣብይ ኣሕመድ ጋሻ ኣሻግሬና ጀሌዎቻቸውን ፊት ለፊት ተጋፍጠህ ራስህና ልጆህን ወራሪዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄዱት ካለው  ኣውዳሚ ጦርነት ማራቅ ኣለብህ፡፡
በዋነኛነት ግን አረመኔው ኣብይ ኣሕመድ ኣሃዳዊ የንግስና ህልሙ እውን ለማድረግ፣ ቀንና ሌሊት እያደረሰባቸው ያለው ግፍና ሰቆቃ ኣሽቀንጥረው ለመጣል ግዜው ኣሁን መሆኑን ኣውቀው ፣ የኢትዮጵያ ብሄር ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች እያካሄዱት ያለው ትግል በኣግባቡ ተደራጅተው ሊያጣጥፉት ይገባል፡፡
የዓለም ማሕበረሰብ እና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ተቋማትም፣ ፋሽሽቶቹ ኣብይ ኣሕመድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂና የተስፋፊው ታጣቂ ሃይል በቅንጅት በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ እያካሄዱት ያለው የእልቂትና የዘር ማጥፋት ጦርነት፣ ምስራቅ ኣፍሪካን ኣተራምሶ፣ የቀይ ባህርንና ህንድ ውቅያኖስን የኣሸባሪዎች መፈንጫ የሚያደርግ መሆኑን በውል እንደምትገነዘቡት ይገመታ፡፡  ነገር ግን  መገንዘብ ብቻ በቂ ኣይደለም፡፡  ዋናው ቁም ነገር ይህንን የጥፋትና የሽብር ጥቃት ይዋል ይደር ሳትሉ በተግባርና በይፋ ልታወግዙት ይገባል፡፡ ፋሽሽትና አሸባሪዎቹ ኣብይ አሕመድ፣ ኢሳያስ ኣፈወርቂና ጭፍራዎቻቸው በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀሙት ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት ጦርነት፣  በኣጠቃላይ ይህን የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት እና  የጀርመን ናዚ  በኣይሁዳውያን ላይ የፈፀመው ሰብኣዊ እልቂት ተመሳሳይነት ያለው ዘግናኝ ፍፃሜ እንደ ጀብድ ቆጥረው ደጋግመው እያሰራጩት ያሉት በፋሽስት ኣብይ ኣሕመድ የሚተነፍሱ በኣገር ውስጥ እና በውጭ ኣገር ያሉ ሚድያዎች እና ጦማሪዎች ጭምር በዓለም ዓቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ፊት እንዲቀርቡ የማድረግ ሃላፊነታቹ  ልትወጡ ይገባል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ወራሪዎቹ አብይ ኣሕመድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂና የተስፋፊው ታጣቂ ጦር ኣፍሪካዊ ካልሆነ ኣገር ጋር ተቀናጅተው እያካሄዱት ባለው የጥፋት ጦርነት ምክንያት፣ የተፈናቀሉት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሰብኣዊ እርዳታ በኣስቸኳይ እንዲደርሳቸው፣ በኣጭሩ ይህንን ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄዱት ያሉት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ተግባራት እንዲቆም  በማስገደድ የሰብኣዊ እርዳታ ሰጪ ተቋማት ሃላፊነታቹ እንድትወጡ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በመጨረሻም ፋሽሽቱ አሸባሪው አብይ አህመድ የትግራይ ህዝብን ለማንበርከክና በድህነት የጨለማ አዙሪት እንዲዳክር የተለያዩ ተቋማት ባየር ድብደባ አጋይቷል፡፡ ይኸውም የተከዜ ግድብ እና የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ጨምሮ በርካታ የልማት ተቋማት በቦምብ ኣጋይቷዋል፡፡ በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ጎሮሮ ለመዝጋት በርካታ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ክልከላዎች አካይደዋል፡፡ ህዳር 8/2013 ዓ.ምም ፋሽሽቱ አብይ አህመድ ከዚህ በፊት የፈፀማቸው እኩይ ተግባራት በማጠናከር 34 የትግራይ የልማትና የፋይናንስ ተቋማት ኣካውንት በህገ ወጥ መንገድ አግደዋል፡፡ ሆኖም ይህ ሁሉ የፋሽሽትና የአሸባሪዎቹ አብይ አህመድ ኢሰያስ አፈወርቂና የተስፋፊው ታጣቂ የጥፋት መልእክተኛ አስነዋሪና ታሪክ ይቅር የማይለው እኩይ ተግባራት አይበገሬው የትግራይ ህዝብ አንድነት ይበልጥ እንደ አለት የሚያጠናክር እንጂ ፈፅሞ ሊያንበረክክ እንደማይችል ወዳጅም ጠላትም ሊያውቅ ይገባል፡፡
ትግራይ የወራዎች መቀበርያ እንጂ መፈንጫ አትሆንም!!
ህዳር 8/2013 ዓ/ም  መቐለ
Filed in: Amharic