* የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው ትህነግ፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቀሌ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮችን አፍርሷቸዋል።
* የተማመነባቸው ከባድ ምሽጎቹ ፈራርሰው፣ በሽሬ መንገድ የደረሰበት ሽንፈት ያንገበገበው ጁንታ፣ በሽሬና በአኩስም መካከል የሚገኘውን አስፓልት በግሬደር ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታል።
አቤል ዘመን
ህወሓት መቀሌን ባህር አልባ ደሴት ሊያደርጋት ወስኖ በአራቱም አቅጣጫ ወደ መቀሌ የሚወስዱ መንገዶች ላይ ያሉ ድልድዮችን አውድሞዋቸዋል ሲል ያገሪቱ ቴሌቭዥን ይፋ አርጎዋል። ይህ ጉዳይ የሚያሳየው ህወሀት የመጨረሻውን እርከን መውሰዱን ነው እንዲህ አይነት ጦርነት በብዛት በጠላት የሌላ አገር ውጊያ ላይ የሚደረግ ነው ። እነኝህ የፈረሱ ድልድዮች ለደሀዋ አገር ብዙ ቢሊዮን ብሮች ፈሶባቸዋል ከዛም ባለፈ ለትግራይ ህዝብ የህልውና ያህል ነበሩ።
አሁን ጦርነቱ ወደ ከባድ ፈታኝ አዘቅት ውስጥ የገባ ይመስላል የመገናኛ ድልድዮች ፈረሱ ማለት የሎጅስቲክ አቅርቦት የከባድ መሳሪያ እንቅስቃሴ እና የወታደራዊ ገፍቶ ውጊያ መንገድ ቅርቃር ውስጥ ይገባል። ህወሓት ይህን ያደረገው በግዛቱ የበላይነቱን ለመውሰድ ነው ። ጦርነቱ ማለቁ አይቀርም ግን በቀላሉ ለማብቃት የሚችል አይሆንም ምናልባት የአገሪቱ ጦር የአየር ጥቃቱ ላይ ካላተኮረ በቀር።
ወይ ጉድ ስለዚህ ድልድይ ህወሀትየ ደረመሰች ማዶ ላይ ሆኖ የሚመጣው ላይ መተኮስ ነው ቀልዳቸው እኮ ኣይጠገብም ።
ጦርነት መጥፎ ነው ህይወት ብቻ አይደለም የድህነትን በሮች ከፍቶ የአመታት እዳ የሚጭን አክሳሪ የሰነፎች መንገድ ግን ደግሞ ህግ ማስከበር ግድ ነው ።
ይህ ጦርነት መች ያልቃል ለሚለው መልስ ማንም መስጠት አይችልም እስከዛሬ የተባሉት ሁሉ ስህተት ነበሩ በሁለት ቀን ያልቃል የሚለው የደፋሮች ገለፃ ቀርቶ ሶስተኛ ሳምንት ጀምረናል። በቅርብ ይጠናቀቃል የሚለውም ብዙ አይደለም ምክንያቱም ቅርብ በሚል ውስጥ አመታትም ወራትም ሊነጉዱ ይችላሉ።
የህወሀት ይህን የማድረግ ምርጫ ግን እጅግ አስገራሚ ነው በእርግጥ ከአማራ በስልጣን ዘማን የወሰዳቸውን ግዛቶች ጉዳዩ እንዳልሆኑ በይፋ ገልፆዋል ወልቃይት እና ራያ በባርነት ሲገዛቸው እንጅ አንድም ቀን የራሴ ብሎዋቸው አያውቅም። ለዚህም ነው የክልሉ የፀጥታ ቢሮ “ከአማራ ስለ ወሰድናቸው ግዛቶች አያገባንም አይጠቅሙንም በዛ ውስጥ የምናፈሰው ሀይል የለም ወተናል ” ሲሉ የተናገሩት።
ህወሀት ያፈረሳቸውን ድልድዮች እንደገና ለመስራት አገሪቱ በትንሹ ከሰላሳ ቢሊዮን ብር በላይ ማማጥ አለባት ።የህወሀት እርምጃ በወታደራዊ ህግ የመጨረሻ የከፋ የሚባለው ነው የመገናኛ መንገዶችን ድልድይ ማውደም ማለት እጅግ ትልቅ እርምጃ ነው ። ቀጥሎስ ምን ይሆን ? ያገሪቱ ጦርስ ከዚህ በሁዋላ ቀጣይ እርምጃው ምንድነው ? ነው ወይስ እንደ ቀበሮ ጦርነት ማዶ ለማዶ መካረም ነው ? ይህንስ እንዴት ማለፍ ይቻላል የሚለው ሳይንሳዊ ትንታኔ ይፈልጋል ። ህወሀት እውነትም አምርሮዋል የመጨረሻውን እራሱንም አገሪቱንም ህዝቡንም የሚጎዳ ውሳኔ መወሰን ማለት it might be the finnal call ።