>

አሻዴ ሀሰንና የክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች በክልሉ ለሚጠፋው ህይወት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል (ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ)

አሻዴ ሀሰንና የክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች በክልሉ ለሚጠፋው ህይወት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል

ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ


በቤንሻንጉል ጉምዝ በድንባጤ ወረዳ ዛሬም እንደ ትናንቱ በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንደደረሰ እየተሰማ ነው፡፡ በዚህ ክልል ውስጥ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ ዘግናኝ በደሎች እየተፈፀሙ ይገኛል፡፡ የፌዴራሉም ይሁን የክልል መንግስታት ተቀዳሚ ተግባራቸው የዜጎችን የመኖር ዋስትና ማስጠበቅ ነው፡፡ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ያልቻለ ግለሰብ ስልጣኑን ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡ ወይም ለሚጠፋው የሰው ልጅ ህይወት ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡ 

ባለስልጣናት/መሪዎች ለሚያጠፉት ጥፋት ተጠያቂ እስካልሆኑ ድረስ የአሸባሪውን የህወሐት ባህሪ መላመዳቸው አይቀርም፡፡ ስለዚህ የቤንሻንጉል ጉምዝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻዴ ሀሰን እና የክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች በክልሉ ለሚጠፋው ህይወት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል

Filed in: Amharic