>

እርግጠኞች ናችሁ  ሮኬቱ ከትግራይ ነው የሚተኮሰው?  (ዘመድኩን በቀለ)

እርግጠኞች ናችሁ 

ሮኬቱ ከትግራይ ነው የሚተኮሰው? 

ዘመድኩን በቀለ

 

ሦስቴ ተኩሰው ታርጌቱን ያልመታላቸው ዐቢይ አሕመድ አስተካክላችሁ ተኩሳችሁ አውድሙ እንጂ ብሎ ቀን የሰጣቸው ነው የሚመስለኝ። አቶ ለማ መገርሳና ዶፍተር ዐቢይ አሕመድ የዛሬ ዓመት ይሁን ያለፈው ዓመት ብቻ ከባሕርዳር የሚሳኤል መቃወሚያ አንስተው ወለጋ ላይ ማስተከላቸው ይነገራል። ለዘንድሮ ቀጠሮ ይዘው መሆን አለበት። የሆነች ሴራ ቢጤማ አለች። ሴራ ለሴሪዋም አልበጀ። ብልጥግና ሰምተሻል። አሁን ቀጥሎ የሚተኩሱት 4ተኛው ሮኬት ምን ላይ ያርፍ ይሆን…?
… በሁሉም አቅጣጫ የህወሓትን ጦር ደምስሰን መቀሌን ዙሪያዋን ከበን ጠላትን ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ቆመናል። “ጁንታ“ ብለው የዳቦ ስም ያወጡለትንም የወንበዴ ቡድን የተደበቀበትንም ሥፍራ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አውቀነዋል። ጁንታውን ከመደምሰሳችን በፊት ግን የመጨረሻ 72 ሰዓታት የእጅ መስጫ ዕድልንም ሰጥተነዋል። ( ከልክ በላይ ነው ግን ያዘኑለት ለጡት አባታቸው ለጁንታው)
ዕርግጥ ነው የሰሜን ዕዝን ሮኬቶች እና፣ ሚሳኤሎቹን ዘርፈውናል። ሆኖም ግን መሣሪያዎቹን የምንቆጣጠረው ከማዕከል ሆነን ነው። መሣሪያዎቹ ከአዲስ አበባ ስለተቆለፉ ከትግራይ ምድር ወደ የትም ሊተኮሱ አይችሉም። ብሎ ወነጉ መርዳሳ የሚሉት የአየር ኃይሉ ሶዬ ከነገሩን በኋላ ጎንደርና ጎጃም በሮኬቶቹ ሲደበደቡ ወዲያው ወጥተው አሮጌ ሮኬቶች ጠጋግነው ነው እንጂ የተኮሱት አሉን። ወዲያውም እሱም ቦታው ታውቆ ተደምስሷልም አሉን። አልቆየም ወያኔዎቹ መርዳሳ መግለጫ ሰጥቶ ሳይጨርስ ወዲያው ለባህርዳር አስበው የተኮሱት ሮኬት የገበሬ ማሳ ላይ አርፎ በቆሎ ሲጠብስ አመሸ።
… እነሆ ዛሬም ተከበበ፣ ተደመሰሰ፣ ጠፋ፣ ከበባ ውስጥ ወድቆ መቀሌ ነው የቀረው የተባለው ህወሓት ከማይፀብሪ አለመውጣቱ፣ ጠለምትም ላይ እየተዋጋ መሆኑን እየሰማን ነው። ሊሞት እያጣጣረ ነው እየተባለ እንኳ ሟቹ ወንበዴ ለባህርዳር አውዳሚ ሮኬት መላኩን አላቆመም። ጅብን ጭካኔውን አውቆ እግሩን አሳጥሮ፣ ልብም ነስቶ ፈሪ አድርጎ እንደፈጠረው ሁሉ ህወሓት አቅም ያአጣች ፈሪ፣ ደግሞም ገንዘብ እንጂ ተዕውቀት ነጣም ሆና እንጂ፣ ደግሞም ኒዩክለርም ቢሆን አጣች እንጂ፣ በመርፌ፣ በኪኒና ፣ በኤድስና በወባ፣ ብላ ብላ አላልቅ ያላትን ህዝብ ቢቻላት፣ አቅምም ቢኖራት ሙሉ ዐማራን ዶግ አመድ አድርጋ ብትጠፋ ደስታዋ ነበር። የራሷን የአክሱምን አውሮጵላን ማረፊያ በግሬደር ያረሰች፣ ተርሚናሉንም በእሳት ያጋየች፣ ለባህርዳርና ለጎንደር የሚራራ አንጀትም የላትም። ደንታዋ ነው እንዴ ሂዊ?
… በዚህ ወገን ግን ለመቀሌ የታዘነውን ያህል፣ ለዚህ አጥፊ ቡድን የተሰጠውን በነፃነት የመኖር ዕድል ያህል፣ የትግሬ ህዝብ እንዳይሰቃይ የታዘነውን ያህል፣ ሳይራብ ወደፊት ሊርበው ይችል ይሆናልና በሚል የሚታሰብለትን ያህል፣ ለመቀሌ ለከተማዋ የታዘነውን ያህል፣ በቁሙ ኢትዮጵያ ምድራዊ ሲኦል እንድትመስለው የተፈረደበትን ያህል፣  ለዐማራው ህዝብ፣ ለዐማራ ከተሞች ለጎንደርና ለባሕርዳር ያለመታዘኑ ይገርመኛል።
… ወዳጄ አጥፍቶ ጠፊን በጊዜ ካላስወገድከው ይዞህ ነው የሚጠፋው። እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለው በድፍረት በአደባባይ ሰልፍ የወጡት የትግሬ ልጆች ሃገራቸው ያልሆነች ኢትዮጵያን አውድመው ለመውደም ለሰከንድ እንደማያመነቱም መታወቅ አለበት። አንድ እንኳ ተቆጪ ሽማግሌ በመሃላቸው ያለመኖሩም ይገርማል። ይደንቃልም።
… ፀረ ህዝብ ነው፣ ፋሽስት ነው፣ ጨፍጫፊ ነው፣ ይሉ ይከሱት የነበረው ደርግ እንኳ ገጠሩን ለቅቆ ከተማ ገብቶ እየተዋጋ ከተሞችን እንዲወድሙ ማድረግ ይችል ነበር። አስመራንም ለሸአቢያ፣ መቀሌንም፣ ጎንደር ደሴ ባህርዳርንንና አዲስ አበባንም ጥይት እንዳይተኮስባቸው፣ የሰው ነፍስም እንዳይቀጠፍባቸው፣ ንብረትም፣ ሃብትም እንዳይወድም ተጠንቅቆ ነው መሸነፉን አምኖ በጊዜ እጁን የሰጣቸው። ምክንያቱ ደግሞ ባንዳ የባንዳ ዘርና ልጅ ስላልሆነ። ኢትዮጵያን ብሎ ለኢትዮጵያ የሞተ ስለነበረ። ለዚያ ነው እንዲያ ያደረገው።
… እነዚህ ግን አውሬ ናቸው። የቆሰሉ ጅቦች። በቃኝ የማያውቁ ጅቦች። ለህዝባቸው የማይራሩ አረመኔ ጅቦች። እነዚህ ባንዳ የባንዳ ልጆች ናቸው። ከትግሬ ማኅጸን ያልተወለዱ አረመኔዎች፣ የሠሩትን ድልድይ የሚያፈርሱ፣ የገነቡትን ህንጻ የሚያወድሙ የቀንም የማታም ጅቦች። ለእነዚህ አውሬዎች አይደለም 72 ሰዓታት፣ 7 ሰኮንድ እንኳ መታገስ ከባድ ወንጀል ነው፣ ንስሐ የሌለውም ኃጢአትም ግፍም ነው።
… እንደ እኔ እንደ እኔ አሁን የዐማራ ክልል በተቻለው መጠን ከተከዜ ሐይቅ በታች ያሉ ነዋሪዎችን ለጊዜው እንዲጠነቀቁ ቢያደርግ መልካም ነው። ከተቻለ ወደ ከፍታ ቦታዎች ቢያሸሽ። ባህርዳርና ጎንደር የሚልኩትን ሚሳኤል እዚያው ተከዜ ላይ ጥለው በጦርነት አላልቅ ያላቸውን በውኃ ሙላት እንዳይፈጁት ነው ስጋቴ። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል ባይ አህያ ከዚህ በላይ ማሰብ አይችልም። እናም ምጥንቃቅ። ሦስቴ ተኩሰው ታርጌቱን ያልመታላቸው ዐቢይ አሕመድ አስተካክላችሁ ተኩሳችሁ አውድሙ እንጂ ብሎ ቀን የሰጣቸው ነው የሚመስለኝ። አቶ ለማ መገርሳና ዶፍተር ዐቢይ አሕመድ የዛሬ ዓመት ይሁን ያለፈው ዓመት ብቻ ከባሕርዳር የሚሳኤል መቃወሚያ አንስተው ወለጋ ላይ ማስተከላቸው ይነገራል። ለዘንድሮ ቀጠሮ ይዘው መሆን አለበት። የሆነች ሴራ ቢጤማ አለች። ሴራ ለሴሪዋም አልበጀ። ብልጥግና ሰምተሻል። አሁን ቀጥሎ የሚተኩሱት 4ተኛው ሮኬት ምን ላይ ያርፍ ይሆን?
• አሁን ጄነራል መርዳሳ እስቲ ደግሞ ብቅ ይበሉና በመጠኑ ይበጥረቁብን። ደምሲሰናል። ኬት እንደሚተተኩስ እንጃአባቷ ይበሉና በሳቅ ፍርፍር ያብሉን። ኦሮሙማ ጦርነቱ በአጭር እንዲቋጭ የሚፈልግ አይመስልም። ሰሞኑን 5ሺ የኦሮሚያ ወታደር በወልድያ በኩል ወደ መቀሌ ሄዷል። ዛሬ ደግሞ ፈረንጅ ወታደሮች በወልድያ ወደ ራያ ሲሄዱ ታይታዋል። ዐማራ ሞቶ ነፃ ያወጣውን ምድር በጸሎት ላይ የቆየው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እየሰፈረበት ነው? ወይስ ወደ መቀሌ ሄዶ በዚያ ሊሰፍር ነው?
… ኢትዮጵያ ግን እግዚአብሔር ይሁንሽ  !!
Filed in: Amharic