>

ብዙ ሊያናግሩን ይፈልጋሉ! ዛሬ ደግሞ "አማራ ብቻውን ይግጠመን" አሉ! (ጌታቸው ሽፈራው)

ብዙ ሊያናግሩን ይፈልጋሉ! ዛሬ ደግሞ “አማራ ብቻውን ይግጠመን” አሉ!

ጌታቸው ሽፈራው

የመጀመርያው ነገር የእቃ እቃ ጨዋታ አይደለም። አማራዎች በብዛት ተለይተው ቢረሸኑም የካዳኸው  የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ነው። በቀን ሰራተኛ  የምታሰራውን ስራ ተጎንብሶ ሲያግዝ የነበረውን መከላከያ ሰራዊት ነው የካድከው።  ትምህርት ቤት የሰራልህን መከላከያ ሰራዊት ነው የከዳኸው። እሱ እንቅልፍ አጥቶ አንተ እያንኮራፋህ እንድታድር ያደረገውን መከላከያ ነው የካድከው። አንተ መሸታ ቤት ለመሸታ ቤት እየተንዘላዘልክ እሱ ድንጋይ ተንተርሶ የኖረልህን መከላከያ ነው ያጠቃኸው። ከሃዲ! ከኋላው አድብተህ ያጠቃኸው ሰራዊት እንደምርቃት ቆጥሮልህ ዝም ሊልህ አይችልም። እያቀመሰህ ነው! ማቅመስ ብልህ ማቅመስ ብቻ እንዳይመስልህ፣ አለኝ ያልከውን ኃይል እየለበለበው ነው። አለኝ ያልከውን መሳርያ በእጁ እያስገባ ነው። ክህደትህ፣ ቅሌትህ፣ አልጠግብ ባይነትህ፣ እብሪትህ ያመጣብህ ስለሆነ ይበልህ፣ ደግ አደረገ!
ሲቀጥልማ!  መከላከያ ሰራዊቱን ሳያስበው መትተህ ወደአራት ኪሎ ልትምዘገዘግ ስትጥር ዳንሻ ላይ ጉርቦህን ያነቀህ አማራ ነው።   በየጥሻው የወደቀው አስከሬን ጎርፍ ከሱዳን ያመጣው እንዳይመስልህ በእብሪት ተነሳስተህ መከላከያን አጥቅተህ አማራን እረማመድብሃለሁ ስትል የአማራ ገበሬ ግንባር ግንባሩን የመታው ነው። ሰው ካለህ የወደቀው ምኑን ተመታ ብለህ መጠየቅ ብቻ ነው።  አስከሬን ቀርቶ ቁስለኛ ማንሳት የማትችል ፈርጣጭ መሆንክን አማራው “ለሚመለከተው ሁሉ” ብሎ ደብዳቤ ፅፎ ማሕተም አሳርፎብሃል። አስከሬን አልቀበርክ፣ ቁስለኛ አላነሳህ። እኔን አትጨቃጨቀኝማ ጠይቅ ወረድ ብለህ! እየተርበተበተ የተያዘውን ደግሞ እግዜሩ ይወቀው።
ያም ሆኖ ግን አማራ እንደ አንተ ክፉ አይደለም። አንተ ንፁሃንን ሰብስበህ ስትጨፈጭፍ አማራ ጨፍጫፊህን እጁን ይዞ እያሳከመ፣ እየተንከባከበ ነው። አማራ በመራዥነቱ ብቻ ሳይሆን በሞራል የበላይነቱ ነው አናትህ ላይ የወጣብህ!
ያልሆነ ነገር  እየተናገርክ እብሪት አታስመስልብኝ። እብሪት እንደጣለህ ስለማውቅ እብሪትን እጠላለሁ። ግን አማራ ብቻውን ይግጠመኝ ስትል አማራ ጋር ገጥመህ የሆንከውን መነገር አለብህ። ልመደው ሽንፈትን!  አሁን እንኳ አላርፍ ስላልክ ልታውቀው ይገባል። ወልቃይት ጠገዴ ባዶ እጁን የገባ አማራ ሳይቀር የታጠቀው አንተ “ሂድ አራት ኪሎ ግባ” ብለህ የላከውም ወታደር ትጥቅ ነው።  እረኛ ሳይቀር የአንተን ትጥቅ ይዞታል!
ሲሰልስልህ! አንተን በቀን ወዲያ ማዶ የሚያደርስህ መከላከያ ሰራዊት በራስህ ሰዎች ሲመራ እያለ እነ ጎቤ መልኬ አስር ሳይሞሉ  አንድ ጉብታ ላይ ሳምንት ገትረው የሚያውሉት ነበር። ገበሬውን ለምነህ አስፈራርተህ ያስለቀምከው አስከሬን ይመስክር! አንተ ወንበዴ ሆነህ ብቻ ሳይሆን ገዥ ሆነህ አማራ በነፍስ ወከፍ ጠመንጃ ገትሮህ ነው የኖረው።  ዛሬ ከከተማ ከተማ የሚነዳህን መከላከያ ሳትከዳው፣ የራስህ ሌቦች እያዘዙት እያለ የአማራ ፋኖ አንድ ሸለቆ እንዳይሻገር ሲያደርገው ነበር!
ወይኔ ረስቸው!  የራስህ ኃይል ከመቀሌ እየተንከለከለ መጥቶ ጭዳ የሆነልህኮ በአንድ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ነው። የመን ድረስ  ሄዶ ሰው አፍኖ ያመጣው የአንተ ሰው   ጎንደር ቀበሌ  18 መጥቶ እንደ በዓል ዶሮ ተንደፍድፎ ነው የቀረው!
እብሪተኛ አታስመስሉን። እብሪት ነው የጣላችሁ። አማራ ያለ ምክንያት ተሻግሮ አያጠቃም። ብዙም ታግሶሃል። መከላከያውን አጥቅተህ፣ ዳግመኛ ወደአራት ኪሎ ተራምደኸው ልታልፍ ስትል ግን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የእኔ የምትላቸው ሰዎች ጉድጓድ ስር እንዲደበቁ አድርጓል። ረዥም ጊዜ በር ዘግተህ፣ ገንዘብ አፍስሰህ ያወጣኸውን እቅድ በነፍስ ወከፍ መሳርያ የቀጨብህ አማራው ነው! በእብሪትህ  ግማሽ ክፍለ ዘመን ታለቅሳታለህ!
ምን ልጨምርህል? ትንሽ እረፍት ውሰድ እስኪ!
Filed in: Amharic