>

በድሆች ደምና ላብ የበለጸጉት ትህነጎች ታሪክ ሊሆኑ ቀናት ቀርተዋል... ትህነግ 'ነበረት'...!!! ( ደጀኔ አሰፋ)

በድሆች ደምና ላብ የበለጸጉት ትህነጎች ታሪክ ሊሆኑ ቀናት ቀርተዋል… ትህነግ ‘ነበረት’…!!!

ደጀኔ አሰፋ

መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለው እርምጃ እጅግ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል!!!
አሁን ወደ ፍፃሜዉ እየሄድን ነው!!! ከቀናት በኃላ ትህነግ ታሪክ ይሆናል!!!! ትህነግ ‘ነበረት’!
ከዚያ በፊት ግን የጁንታው አምስቱን ዋነኛ አመራሮች የዘረፉትን የሃገር ሃብት በሰሯቸው ቤቶች እና የነበራቸውን የቤተ ዘመድ እንቅስቃሴ በወፍ በረር ለማስታወስ ያህል እነሆ:-
1ኛ) ጌታቸው አሰፋ – 
በመቀሌ ፣ በአዲስ አበባ እና ብራስልስ (ቤልጅየም) እጅግ ገራሚ እና ፍፁማዊ የቅንጦት ቤቶች አሉት::
ሚስቱ እጅግ ዘመናዊ ሴት ነች:: የተቀናጣች እና extravagant ስትሆን ሾፕ የምታደርገው (ገበያ የምትሄደው) ዱባይ : እንግሊዝ ለንደን እና አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነው። ሴትየዋ የጌታቸው ሚስት በመሆኗ ሾፕ የምታደርገው እነ አንጀሊና ጆሊ እንዲሁም ታዋቂ ሃብታም አርቲስቶች እና ንግስቶች ደንበኛ የሆኑባቸው እጅግ በጣም ውድ ቦታዎች ናቸው። ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጉጉል ላይ ሰርች በማድረግ በአንድ ሾፒንግ ወጪ የምታደርገውን ገንዘብ ለመገመት ይረዳል::
የጌታቸው አሰፋ ሴት ልጅ ትምህርቷም ኑሮዋም በአውሮፓ ሲሆን የእሷም ሳምንታዊ ወጪ የትየለሌ ነው:: የሴትየዋ ታናሽ ወንድም በአዲስ አበባ ከተማ የስቶክሆልም ባር እና ላውንጅ ባለቤት እንደሆነ ይታወቃል። ጌታቸው አሰፋ ቁንጮ ቢሊየነር ነው::
2ኛ) ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል – 
በመቀሌ ፣ አዲስ አበባ እና ሆንግኮንግ ከተሞች እጅግ ቅንጡ ቤቶች አሉት። በተለይ ደብረፅዮን በጣም የሚወደው እና እንደ ዋና መኖሪያ ቤቱ የሚመለከተው በሆንግኮንግ የሚገኘውን ዘመናዊ ቤቱን ነው:: በምርጫ ደረጃም ከአዲስ አበባ ይልቅ ሆንግኮንግን የሚመርጥ ሲሆን በህክምናም ሆነ በሌሎች ሰበብ አስባቦች እዚያው ሆንግኮንግ ሄዶ ማሳለፍን እና መዝናናትን ይመርጣል። ሆንግኮንግ የሚገኘው የደብረፅዮን ቤት ሚሊዮን ዳላሮች የፈሰሱበት እጅግ ዘመናዊ የቅንጦት ቤት ከመሆኑ ባሻገር ሙሉ የሴኩሪቲ እና በፊልም እንደምናያቸው አይነት የመዝናኛ መሰረተ ልማቶች የተሟሉሉት ነው:: ደብረፅዮን እና ሆንግኮንግ ልዩ ፍቅር አላቸው።
የደብረፅዮን ውድ ባለቤቱም የዚሁ ትሩፋት ተቋዳሽ በመሆኗ እጅግ ሃብታም ሴት ነው:: ለይምሰል ይሁን አለያም ስራ ወዳድ ሆና ባይታወቅም ጁንታው መቀሌ መመሸጉን ተከትሎ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ እጅግ በጣም ውድ የሆኑ የጌጣ ጌጦች እና ቅንጡ አልባሳት መሸጫ ሱቅ ከፍታለች:: የተመረጡ ቱጃሮች ብቻ ይገበዩበታል::  ደብረፅዮን እና ባለቤቱ ያፈሯቸውን ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት እና የሚያኖሩት በትግራይ አለያም በአዲስ አበባ ሳይሆን በተመረጠችው አውሮጳዊቷ ሃገረ #ጀርመን ነው።
 
3ኛ) ዓለም ገብረዋህድ
በመቀሌ ፣ አዲስ አበባ እና ሆንግኮንግ ከተሞች ውስጥ እጅግ ዘመናዊ እና ቅንጡ ቤቶች አሉት::
ዓለም ገብረዋህድ ሴት ልጁን በአውሮጳዊቷ #ስዊድን ሃገር ያስተምራል።
ዓለም የትህነግ የድርጅቱ ፅ/ቤት ሃላፊ ሲሆን ሁሌም ከጌታቸው አሰፋ እና ስብሃት ነጋ ጎን ተሰላፊ በመሆኑ ከደብረፅዮን ጋር ለበርካታ ጊዜያት በሽኩቻ አሳልፏል:: ደብረፅዮን የያዘውን የክልል መሪነት ስልጣን ለመቀማት አያሌ ሴራዎችን አካሂዷል:: በርግጥ መጨረሻ ላይ የሃይል ሚዛኑ ወደ አለም ገ/ዋህድ አጋድሎ የክልሉ ፕሬዝዳንት ለመሆን ጫፍ የደረሰ ቢሆንም የክልሉ ህዝብ የልብ ትርታ ወደ ደብረፅዮን በማጋደሉ ለይስሙላ ያህል ደብረፅዮን እንዲቀመጥ ተደርጏል:: ዋናው የፖለቲካ ስልጣን ግን በዓለም ገ/ዋህድ እጅ ማለትም ጌታቸው አሰፋ እና ስብሃት ነጋ ያሉበት ቡድን እጅ ነው:: ዓለም ገ/ዋህድ እንደ ስሙ የአለም ቱጃር ነው!
4ኛ) ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ –  
በመቀሌ ፣ አዲስ አበባ እና በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ በጣም ዘመናዊ ቅንጡ ቤቶች አሉት::
የዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ ሚስት የአርከበ እቁባይ እህት ናት። ሚስቱ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚካሄዱ ከፍተኛ ጨረታዎች ውስጥ ያለ ተቀናቃኝ ጨረታዎችን በግልፅ የምታሸንፍ ሴት ናት። ሚስቱ እና አዲስአለም በጣም ቱጃሮች ናቸው::
5ኛ) ጌታቸው ረዳ –
በመቀሌ በአዲስ አበባ እና በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ዘመናዊ ቤቶች አሉት:: ጌቾ የዛሬውን አያድርገውና ብዙውን ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ የሚያሳልፍ ሲሆን የቀን ወጭው እጅግ ከፍተኛ ነው:: የጌታቸው አሰፋ ጥብቅ ወዳጅ በመሆኑም ነገሮች ሳይካበዱበት በሄደበት ሁሉ ቅንጡ ነገሮችን በከፍተኛ ገንዘብ ወጭ ማድረግ እንዲችል አስችሎታል::
አዲስ አበባ በሚመጣበት ወቅትም እጅግ ውድ ከሆነው የጣሊያን ሬስቶራንት ውጭ አይመገብም:: ከሸራተን እና ከሂልተን ውጭ አይጠቀምም:: ፈርሞ ይበላል:: ፈርሞ ይጠጣል:: ፈርሞ ይጋብዛል:: ማንንም የመጋበዝ መብቱም የተጠበቀ ነው:: በዚህም በተለይ የቀድሞውን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን እየጠራ ሲያንበሻብሽ እና ሴራ ሲጠነስስ እንደነበር ልብ ይሏል::
ጌታቸው ረዳ የራያን ትግል እንዲቀለብስ ተብሎ ሃላፊነት ተሰጥቶት የነበረም ሲሆን ከ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ለዚሁ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ተበጅቶለት ተጠቅሞበታል:: ሆኖም ግን በተሰጠው ገንዘብ የራያን ትግል መቀልበስ ባለመቻሉ በስብሃት ነጋ እና ጏዶቹ መራራ ትችት እና የስድብ ናዳ ማስተናገዱም ይታወቃል::
የሌሎቹን የጁንታው አመራሮች በቀጣይ የምመለስበት ቢሆንም በአጠቃላይ ግን ትልቋ ኢትዮጵያ በጁንታው እጅ ወድቃ ስትሰቃይ እንደነበር ግልፅ ነው:: እንደ ፓሬቶ ህግ የሃገሪቱ 80% የሚሆነው ሃብት 20 በሚሆኑ የጁንታው አባላት እጅ ተይዟል:: ድህነት እና ኑሮ ውድነት ከስራ አጥነት ጋር ተዳምሮ የሃገራችንን ናላ አዙሮታል:: ወጣቱ ተስፋ ቢስ እና ስደተኛ እንዲሆን ዳርጏል::
ብጥብጥ እና ረብሻ መገለጫችን እስኪመስል ድረስ ሃገር በማያባራ መናጥ ውስጥ አልፋለች:: ገንዘቡም ስልጣኑም የእኔ ብቻ በሚሉ ስግብግቦች ሳቢያ ሃገራችን ተገፍታ ተገፍታ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባት አልፏል:: በዚሁ በዘረፉን ገንዘብ በጅምላ አስጨፍጭፈውናል:: ልጆቻቸውን ውጭ ሃገር ልከው ድሃውን ወጣት ይማግዱታል!!! እኛኑ ዘርፈው ድጋሚ ደማችንን በየቦታው አፍስሰዋል:: ከእኛው ሆድ ተቀንሶ የሃገራችን ድንበር ይጠበቅበታል ብለን በገዛነው በእኛው መሳሪያ የመከላከያ ሰራዊታችንን በተኛበት አርደውታል:: መሰረተ ልማት ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ገድለው ጥለዋቸዋል:: ብቻ ሃዘናችን ብዙ ነው!
መንግስት አሁን የህዝቡን ብሶት ይስማ!
ፍትህን በማድረግ ህዝቡን ይካስ!
መንግስታችን ይህን የጀመረውን ኦፕሬሽን እንደጨረሰ ከኢንተርፖል እና ከሌሎች ተቋማት ጋር ተጣምሮም ቢሆን : በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ተሳትፈውበት ቢሆን… የተከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ ይህ ከኢትዮጵያውያን አፍ ላይ በጁንታው የተዘረፈውን የደም ገንዘብ ያስመልስ!!! ቢችል በክህደት የታረዱትን የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላትን እና ቤተሰቦቻቸውን በዚህ ገንዘብ ያቋቁም!!! #መታሰቢያ_ሃውልትም ያቁምላቸው!!! ዝንተ አለም የማይወጣ ሃዘን አለብን!!!! ተክደናል!!! በሃገራችን ጥቁር ታሪክ ተመዝግቧል!!! ህዝቡ ብሶት አለበት!!!
ድል እና ክብር ለሃገር መከላከያ ሰራዊት!!!!
እጅግ ብሩህ ዘመን ለኢትዮጵያችን!!!!
Filed in: Amharic