>

"ወገን እንደ ትውልድ በጣም አሳፋሪ ወደ ሆነው የታሪካችን ምእራፍ ደርሰናል!!" (አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ)

“ወገን እንደ ትውልድ በጣም አሳፋሪ ወደ ሆነው የታሪካችን ምእራፍ ደርሰናል!!”

አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ

ዛሬ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማይካድራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ  ምርመራ ሲያደርግ ቆይቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል! ወንጀሉም በጀርመን ናዚዎች ላይ ቀርቦ በነበረው   crimes against humanity ክስ የሚያስጠይቅ እንደሆነ  :ፈጻሚዎቹም ራሳቸውን ‘ሳምሪ’ ብለው የሚጠሩ  የተደራጁ የአካባቢው ወጣቶች እንደሆኑ
ከኗሪውም ውስጥ  በተለይ አማራዎችን እየመረጡ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዳረዱ አሳውቋል!…
ዜናውን እነ BBC ን ጨምሮ የአለም መገናኛ ብዙሃን እየተቀባበሉት ነው!
 ምናልባትም ሴጣን ያደራጃቸው ካልሆኑ በስተቀር እነኚህ ትግራዋይ ወጣቶች ይህንን አስከፊ ወንጀል ለመፈጸም የሚያስችለውን በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ የጭካኔ እና የአውሬነት ጥግ ከየት እንዳመጡት መገመት  አልችልም!!
ስድስት መቶ ሰዎችን በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ማጣት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአለምም…,በጠቅላላው  ለመላው የሰው ልጅ አሳፋሪ ነው! አንገትም የሚያስደፋ ነው!!
ይህንን ወንጀል እና ፈጻሚዎቹን ለማውገዝ አቅም የሚያጥረው ሰው በሙሉ ‘የሞራል ሰው’  ነኝ የሚል ቢሆን እስከዛሬ ስለራሱ ያለውን አመለካከት ቆም ብሎ እንዲፈትሽ እመክራለሁ!
‘ሃይማኖተኛም ሰው’ ነኝ የሚል  ‘እውን እኔ ክርስትያን ነኝን!? በቤተክርስትያን ደጆችስ ለምን ይሆን የምመላለሰው!?’
‘እውን እኔ ሙስሊም ነኝን!? የአላህ ፍጥረት በገዛ ወገኑ እንዲህ ያለጥፋቱ  ሲታረድ በተራ ፖለቲካ እና ጥምብ በሆነችው ዘረኝነት ታጅዬ ለነኚህ ሟቾች ያውም ለሃገሬ ልጆች እንዴት አንዲት  የእዝነት ቃል ለማውጣት ከንፈሬን ማላቀቅ ተሳነኝ!? ‘ ብሎ ራሱን ይጠይቅ! ወገን እንደ ትውልድ በጣም አሳፋሪ ወደ ሆነው የታሪካችን ምእራፍ ደርሰናል!!
ህወሃት በ27 አመት አገዛዟ ሰውን በማንነቱ ብቻ ሆ ብለው በመንጋ  በድንጋይ ወግረው የሚገሉ :ዘቅዝቀው በአደባባይ ሰቅለው ከበው የሚጨፍሩ  ትውልዶችን እንዳፈራች አይተን: ‘ጉድ! ጉድ!’  ብለን ሳናበቃ ራሷ በምታስተዳድረው ክልል ጭራሽ ቤት ለቤት እየዞሩ ህጻን: አዋቂ :ወንድ ሴት ሳይሉ ለማረድ ከኢትዮጵያዊነትም ስነምግባር ሳይሆን ከሰውነትም ስታንዳርድ ውጪ የሆነ ጭካኔ እና ብልግና የተላበሱ   ‘የሰው አውሬዎችን’ እንዳበቀለች እያየን ነው!!
በዚህ በቃቹ ይበለን!
የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ሲዋትቱ ምንም በማያውቁት ነገር እንደ በግ ለታረዱት ወገኖቻችን ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን!
የእውነትና የግፉአን አምላክ  በነኚህ የሰው አውሬዎች ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ  ፍትህ ሲፈጸም ያሳየን!!
ድርብ ድርብርብ ድል ለመከላከያ ሰራዊታችን!!
Filed in: Amharic