“ትግራይ ከሌላው በበለጠ ለምን አመረረ?”
እንግዳ ታደሰ
ይህን ርእስ በያዘ ጽሁፍ ከሁለት አመት በፊት መጽሃፍ ጽፎ #በኦስሎ መጽሃፉን ሲያስመርቅ ያስነበበን ኣይተ ግደይ ዘራጽዮን ነው።
ከሳምንታት በፊት በዚሁ ፌስ ቡክ ላይ #ሲናናቁ_አለቁ በሚል ርዕስ ስር stereotype ን’ አስመልክቶ ትግራይ ለዘመናት የተሰበከላት #አማራ ጠል ትርክት ሁሌም ጦርነት ውስጥ ማግዱኣት እንዴት ትገላገለው? በሚል እይታ የራሴን ምልከታ ማስቀመጤን ወደ ኋላ ሂዶ ፈትሾ ማግኘት ይቻላል።
ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት! ኣይተ ግደይ የህወሀት መስራች ሲሆን፣ ለበርካታ አመታት ህወሃትን ትቶ’ ወደ ስደት’ እስከ ገባበት ድረስ የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር ሁኖ #ትህነግን አገልግልዋል!
በግምት ከአስር አመታት በፊት፣ ካልተሳሳትኩ አፕሪል ወር መጨረሻ ላይ “#አሲምባ” በተባለው የኢህአፓ የፓልቶክ የመወያያ መድረክ ላይ አቶ ግደይ ተጋብዞ፣ የመጀመርያዋን አሩር የተኮሰው ኢህአፓ ነው አይደለም ህወሀት ነው በሚል እንካ ሰላንትያ ውይይት ውስጥ፣ የወልቃይት ጉዳይ ተነስቶበት፣ መሬቱ የጎንደር እንደሆነ! ህወሃት ወደ ሱዳን መውጫ በር ስትፈልግ ወደ ራስዋ እንደደባለቀችው አስረግጦ ተናግሮ ነበር። #አውዲዮውን መቸም አሲምባ ግሩፖች ያስቀመጣችሁት ይመስለኛል።
#ወደገደለው ልግባ- ፣
“ከትግል ትዝታዎቼ” የሚለውን መጽሃፉን ሲያስመርቅ አንድ እህት ስለ-ወልቃይት ስትጠይቀው ትግሪኛ ተናጋሪዎች ናቸው፣ ስለዚህ ከሚመሳሰሉበት ህዝብ ጋር መደባለቃቸው ችግር ያለበት አይመስለኝም ነበር ያለው። ቃል በቃል ባይሆንም። በእለቱ ፊልም ይቀረጽ ስለነበር ለዋቢነት ከዚያ ላይ ማግኘት ይቻላል ካወጡት።
#ትግራይ_ከሌላው_በበለጠ_ለምን_አመረረ? በሚለው ርዕስ ስር አንኳር አንኳሩን ከመጸሃፉ ጨምቄ ሳወጣው እንዲህ ይላል -ገጽ 15
*የትግራይ ህዝብ 95% የሚተዳደረው በእርሻ ነው። ትግሉ እስኪጀመር ድረስ አብዛኛው የመሬት ይዞታ ርስት ነበር። ይህ የመሬት ይዞታ ከብዙ ዘመን ጀምሮ እየተሸነሸነ በመሄዱ ህዝቡ እያደገ በመሄዱ ህዝቡ እያደገ በሄደ ቁጥር ለያንዳንዱ ቤተሰብ የሚደርሰው መሬት እያነሰ ይሄዳል። በሽሬና ራያ’ አካባቢ ሰፋ ያለ የመሬት ይዞታ ቢኖርም በአብዛኛው የትግራይ ቦታ መሬት ይዞታው ትንሽ ነው ይለናል ። ወረድ ይልና ደግሞ- አርሶ አደሩ ኑሮውን ለማሙኣላት የቀን/የኩሊ ስራ ለመፈለግ ወደ ኤርትራ፥ሁመራ፥ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ቡና ለቀማ ራቅም ብሎ ወደ ሱዳንና ሳውዲ ይሰደዳል ይለናል።*ስለዚህ መሬት ከአማራው ምድር ያስፈልጋል ማለት ነው በኔ እይታ።
*-በ-18ኛው ክፍለ ዘመን ትግራይ በአመት ሶስት ጊዜ ያመርት እንደነበረና ለም አካባቢ እንደነበረ ይነገርለታል።ትግራይ ከውጭ ለሚመጣው ወረራ የጦር ግንባር ስለሆነ በውጊያ የሚሳተፈውም ይህ ህዝብ ነበር። ከሌላ የኢትዮጵያ አካባቢ ለሚመጣውም ሰራዊት በስንቅና ሌላ አገልግሎት የሚሸከመውም የትግራይ ህዝብ ነበር። የትግራይ ህዝብ የሃገር ድንበር የመከላከሉ እንጂ እግረ መንገዱን የሚያጋጥመውን ችግር ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን በቂ ግንዛቤ ያላቸው አይመስለኝም። ከአድዋ ጦርነት-1888 እስከ1928 የጣልያን ወረራ ድረስ ብቻ 20 ትላልቅ ጦርበቶች ተደርገዋል፣ይህ ማለት በአማካይ በየሁለት አመት ጦርነት ነበር ማለት ነው።ሰላም ሳይኖር ማምረት አይቻልም። ለዘመቻ የመጣው ሰራዊት ስንቅ የሚያገኘው ከህዝቡ ስለነበረ ገበሬው ደህና ምርት ቢኖረውም ባይኖረውም ለዘማቹ ሰራዊት ማቅረብ ይገደዳል። ሰራዊቱ በአካባቢው በሚቆይበት ጊዜ ለአጋሰሱም ግጦሽና ምግብ ያስፈልገዋል።ዘማቹ ሰራዊት ለምግቡ ማብሰያ እና ራሱንም ለማሞቅ እሳት ይፈልጋል….ለዚህም ዛፎችን ይቆርጣል ያወድማል።ይህን አስመልክቶ ጆን ያንግ ካፕላን የተባለ ጸሃፊ እንዲህ ይላል፣የሚኒልክ ጦር የሚመገበው ከህዝቡ ነው፣የህዝቡን ስንቅና የዘር እህልም ሳይቀር ጨርሶታል፣ለእርሻ የሚገለገልባቸውም በሬዎቹ ታርደውበታል።ከዚያም ተከትሎ ለ-7 አመታት ያህል ረሃብ አጥቅቶታል።
*-ጦርነት በኢኮኖሚ የሚያደርሰው ጉዳት ብቻ ሳይሆን የወገን ዘማች ሰራዊት በህዝቡ ላይ የሚፈጥረው የጥላቻ ስሜት ጠባሳም ቀላል አይደለም።ዘማች ሰራዊቱ በህዝቡ ላይ የሚፈጥረው የጥላቻ ስሜት ጠባሳም ቀላል አይደለም። ዘማች ሰራዊቱ ላይ ጠበቅ ያለ የስነምግባር ዲሲፕሊን መመሪያና ደንብ ስላልነበረው የገበሬውን ሚስትና ሴት ልጅ በሃይል እስከ መድፈር ይሄዳል፣አርሶ አደሩንም ያንገላታዋል። #አያቶቻችን -በዚያን ጊዜ የነበረውን ችግርና የሰራዊቱን ጭካኔ ሲገልጹት #ዘበነ ሸ -በማለት ይገልጹታል “የሸዋ ዘመን” ለማለት ነው። ከዚያን ዘመን ጀምሮ የትግራይ ህዝብ እየቆረቆዘና እየተዳከመ ሄዱኣል ይላል የአቶ ግደይ መጽሃፍ።
ከብዙ በጥቂቱ ትግራይ ከሌላው በበለጠ ለምን አመረረ? የሚለው ትርክት ከህወሃት ፈጣሪዎች እስከ አሁን ድረስ ባለው ትውልድ ውስጥ ስለተሰበከለት #ከባሩድ ማሽተት ትግል ውስጥ ይወጣል ማለት አይደለም ። ትግራይ በቦታ ማነስ ለሚፈጠርባት ምሬት መፍትሄው የዘር ክልልን አጥፍቶ በሴቲት ሁመራ በራያ በዜግነትዋ የራስዋ ምድር እንደሆነ በኩራት መናገር እንጂ በዘር ክልል ፖለቲካ መርዙን ልጆችዋ አምጥተውባት የሰው መሬት መቀላወጡንና መውሰዱ ከጦርነቱ አዙሪት አያወጣትም። ይህ ክፉ ትርክት ከዚያች ምድር መውጣት አለበት።