>

አገር አፍራሽ መረጃ በማሰራጨት ተጠርጥረዋል ባላቸው ግለሰቦችና ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ - ሪፖርተር

አገር አፍራሽ መረጃ በማሰራጨት ተጠርጥረዋል ባላቸው ግለሰቦችና ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ
ሪፖርተር

የአገር ክህደት ወንጀል በመፈጸም በተጠረጠሩና 27 ወታደራዊ ሹማምንት፣ አክቲቪስት  ዳንኤል ብርሃኔ፣ እዝቅኤል ገቢሳ(ዶ/ር)፣  አወል አሎ ቃሲም(ዶ/ር)ና ሌሎች አምስት ግለሰቦች በአገር ውስጥና ባህር ማዶ ሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ እንደገለፀዉ፣ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው ሰባት በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን ጠቁሟል፡፡
ተጠርጣሪዎቹም፣ሜጀር ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ ገብረኪዳን፣ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣይ፣ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ፣ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል፣ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን፣ኰሎኔል ጌትነት ግደያ፣ኮሚሽነር ረታ ተስፋዬ መሆናቸውን ገልጿል።
በተያያዘም ቀደም ሲል የነበራቸውን ወታደራዊ ኃላፊነትና የህወሃት ቡድን ጋር ያላቸውን ጥብቅ ትስስር ተጠቅመው ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል በመንግሥት ላይ ፈጽመዋል ያላቸውን፣ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ፣ ሜ/ጀ ገብረ አድሃና /ገብረዲላ/ ፣ ተክለብርሃን ወልደአረጋይ /ሳንቲም/ ፣ ሜ/ጀ ብርሃነ ነጋሽ /ወዲመዲህን/ ፣ ሜ/ጄ ማዕሾ በየነ ፣ ሜ/ጄ ኢብራሂም አብዱልጀሊል ፣ ሜ/ጄ ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ ፣ ሜ/ጄ ነጋሲ ትኩዕ ፣ ብ/ጄ አባዲ ፍላንሳ ፣ ብ/ጄ ፀጋየ ተሰማ /ፓትሪስ/ ፣ ብ/ጄ ምግበ ኃይለ ፣ ብ/ጄ ተክላይ አሸብር /ወዲ አሸብር/ ፣ ብ/ጄ ኃይለሥላሴ ግርማይ /ወዲ ዕበይተ/ ፣ ብ/ጄ ሙሉጌታ በርሔ ፣ ኮ/ል ተወልደ ገብረተንሳይ ፣ ኮ/ል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ ፣ ኮ/ል ደጀን ግርማይ ፣ ኮ/ል የማነ ገብረሚካኤል ፣ ኮ/ል ገብረሀንስ አባተ/ /ወዲአባተ/ ፣  ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን /ወዲ አድዋ/ ይፋ አድርጓል።
በመጨረሻም በአገር ውስጥና በውጪ አገር ተቀምጠው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም አገር በማፍረስ ተግባ
Filed in: Amharic