>
5:26 pm - Friday September 15, 7499

ደብረጽዮን ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል መባሉን አስተባበሉ...!!! DW

ደብረጽዮን ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል መባሉን አስተባበሉ…!!!

DW

 


 

“ከትግራይ ክልል አልወጣሁም… በመቀሌ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች  ጋር ውግያ ቀጥለናል…. !!!”
(ዶ/ር ደ/ፂዮን ገ/ሚካኤል)
የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል «ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል» ተብሎ የተነገረዉ ዘገባ «ሐሰት ነው» በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ደብረጽዮን «አሁንም በመቀሌ ከተማ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተዋጋን ነው።» ብለዋል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ባለፈው ቅዳሜ የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል። በወቅቱ ደብረጽዮን የመቀሌ ከተማን ለቀው መውጣታቸውን ለሮይተርስ በላኩት አጭር የጽሁፍ መልዕክት አረጋግጠዋል። የሕወሓቱ መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ወደ ደቡብ ሱዳን ሸሽተዋል የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ በሰጡት መልስ «ከትግራይ ክልል አልወጣሁም» ሲሉ ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል አቃባይ ቢለኔ ስዩም በበኩላቸው  «የፌዴራል መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በማረጋጋት ስራ ላይ ተጠምዷል፤ ተበታትኖ ላለ ወንጀለኛ ንግግር መልስ መስጠት ጉዳያችን አይደለም » ሲሉ ደብረጽዮን «በመቀሌ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች  ጋር ውግያ ቀጥለናል» ብለው መናገራቸውን ያጣጣሉበትን ሃሳብ ለሮይተርስ ነግረዋል።
Via-DW
Filed in: Amharic