>
5:26 pm - Monday September 15, 3119

ኧረ ባካችሁ…!!!  ኧረ ባካችሁ…! (አሰፋ ሀይሉ)

ኧረ ባካችሁ…!!!  ኧረ ባካችሁ…!

አሰፋ ሀይሉ

ለበሰበሰው ኢትዮጵያን በዘርና ጎሳ ከፋፍሎ ላባላው አፓርታይዳዊ ሥርዓት ጦሶችና መዘዞች ሁሉ – ወያኔ ደሞ የጦስ ዶሮ ሆና ታርዳ የተጣለችበት – ሌሎቹ የሥርዓቱ አጋፋሪዎችና ቅምቡርሶች ሁሉ ደሞ እጃቸውን በወያኔ ደም አጥበው ከደሙ ንፁህ ሆነው የቀረቡበት – ሁኔታ ነው ያለው ወገን!?
ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የተሰቀለው፣ የተጨፈጨፈው፣ የነደደው፣ የፈራረሰው ሁሉ – አንድም ሳይቀር የወያኔ ሥራ ነው! በዚህ ጅብ ሥርዓት ላለፉት አሰርት ዓመታት በሥልጣን ስግብግብነት የተፈጠረው ሀገራዊ የህዝብ ሀብት ዘረፋ ሁሉ የወያኔ ሥራ ነው!
ሣዕረን የገደለችው ወያኔ ነች! ኢንጂነር ስመኘውንና አሳምነው ጽጌን የገደለችውም ወያኔ ነች! በአዲስ አበባ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከመስቀል አደባባይ እየነጠቀች ስትረጋግጥ የነበረችው ወያኔ ነች! በመስቀል አደባባይ በጠ/ሚው ላይ ቦምብ ያፈነዳችውም፣ ጠ/ሚውን በጠባቂቆች በቤተመንግሥት ቆልፋ አላስወጣ አላስገባ ያለችውም ወያኔ ነች!
እነ ጃልመሮን ያሰለፈችው ወያኔ ነች! ታሪካዊውን የሐረር የልዑል ራስ መኮንን ኃውልት ያፈራረሰችው ወያኔ ነች! የቤኒሻንጉልን ቀስተኞች ያሰለፈችው ወያኔ ነች! በጉራፈርዳና በጌዴዖ ላለቀው ለተፈናቀለው ሁሉ ህዝብ ተጠያቂዋ ወያኔ ነች! ለሱዳኖች መናጨት፣ ለሶማሊያዎች መበላላት፣ ለኬንያዎች ደም መፋሰስ ሁሉ ዋናዋ ጦስ ወያኔ ነች! ይሄን እኔ የምጽፈውን ራሱ የምታፅፈኝ ወያኔ ነች!
ከዚህች ሸይጣን ሸር..ጣ.. ወያኔ ጋር ታዲያ ምን ልሁን ብለህ ትደራደራለህ? እንዴት አድርገህ አብረሃት ትቀመጣለህ? ሳናውቃት እኮ ነው አብረናት የኖርነው! ድርድር የለም ከሠይጣን ጋር! እኛን ጻድቃኑንና ቅዱሳኑን – እናቶች በእንባቸው፣ መላዕክታት በክንፋቸው ይጋርዱናል! ከ27 ዓመቱ ግፍ – የግፍም ግፍ – ይኸው የጦስ ዶሮዋን ወያኔን አርደን ላባዋን በትነናል – ከደሙ ንፁህ ነን – ወላሂ ለአዚም የለንበትም! ሁሉን ነገር አጥንተን ያወቅነው ገና አሁን ነው! ሳናውቅም ግን ወያኔን እየታገልናት ነበር! ቢሆንም የወያኔን ክፋት ካለዛሬ አላየነውም!! አፎ በሉን! ….
ህጋዊው ዶክተር ሙሉ..!! የሣተላይቱ ሣይመንታኒየስ ሲቹዌሽን ሩም አዋጊ… ከፔንታጎን እኩል ያደረግከን.. ድል ከደጁ… ብርሃኑ ጁ..! ግስላው፣ ነበልባሉ፣ አንቀጥቅጡ፣ አርዱ፣ …! ኡ ኡ ኡ….!!! ‹‹ጂሃዳዊ ሀራካት›› ዶኪመንታሪን የሚያስንቅ ፕሮፓጋንዳ… ሁለት ሰዓት ባልሞላ ቶክሾው …?! እንዲህ ባንዴ በኩንታል አምጥቶ ዝርግፍ.. ስድስተኛ ዓመቱን በያዘ የዘመነ ወያኔ ፓርላማ ላይ?!! ጉድ! ጉድ! ጉድ!! ኧረ ምነው ግን ጨከንክሽብን እመብርሃን?!
… ቆይ የት እንሂድ?!! ያቺ የመጠቀች ሳተላይትም ደብዛዋ ጠፋ! የት እንሂድ እንደው የእውነት?!! ደሞ ጭብጨባው! ሆሆሆ!! ለመለስ ጭብጨባ! ለኃማደ ጭብጨባ! ለአብዮት ጭብጨባ! በቃ እንዲህ አጨብጫቢ ሆነን ቀረን! አጨብጭበን ቀረን በሿሿ!?!! ኧረ ባካችሁ…!?!!  ኧረ ባካችሁ… “humble” እንሁን!?! ሀሀሀሀ…! ኧረ ኳሷን በመሬት እናድርጋት…! ኧረ ባካችሁ… ለጭብጨባችንም ‹ሪፎርም› እንሥራለት!?! ኧረ ባካችሁ…!?!
አስተያየት መብት ነው!
ፈጣሪ ይቅር ይበለን!
Filed in: Amharic