>

የደህንነት ሹሙ አመለጠ...!!! (አርአያ ተስፋ ማርያም)

የደህንነት ሹሙ አመለጠ…!!!

አርአያ ተስፋ ማርያም

በቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበረውና ከጌታቸው አሰፋ ቀጥሎ ቁልፍ ሚና የነበረው ዶ/ር ሃሺም ቶውፊቅ ካናዳ መግባቱን ማረጋገጥ ተችሏል። ይህ ሹም ትውልዱ ሀደሬ ቢሆንም የህወሀት አባል በመሆን ሲያፍን፣ ሲያስገድል የቆየና የስብሃት ቡድን ወደ መቀሌ ሲሸሽ አብሮ የሸሸ ነበር። ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ካናዳ ኤምባሲ ገብቶ ቪዛ ከወሰደ በኃላ በቦሌ ወጥቶ ካናዳ መግባቱ ታውቋል። ዶ/ር ሃሺም ከመጋረጃው ጀርባ መሰሪ ጥፋት ሲፈፅም የነበረ ሲሆን የተለያዩ ቁልፍ ስልጣኖች ነበሩት። እነሱም በደህንነት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ፣ የፍትህ ሚ/ር ሚኒስትር ዴኤታ፣ የፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የህግ አማካሪ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ሆኖ የሰራ ሲሆን የፖሊስ ኮሌጅ ሃላፊ እያለ ለገዳዲ መንገድ ላይ ኮብራ መኪና እያሽከረከረ የዘጠኝ አመት ታዳጊ ገጭቶ የገደለና ማንም ያልጠየቀው ወንጀለኛ ነው! ለኢትዮጵያ ስር የሰደደ ጥላቻ እንዳለው በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ።
< ዶ/ር ሃሺም ቶውፊቅ 
Filed in: Amharic