ለ30 ዓመት የታፈነ የአማራነት ድምጽ በዳንሻ ተሰማ…!!!
ታደለ ጥበቡ
-ከ30 ዓመት በላይ ብዙ ማይካድራዎችን አይተናልና ከትግራይ የሚመጣን አስተዳደር ከትህነግ ለይተን አናየውም!
-የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፤ የራሳችንም አሳልፈን አንሰጥም፤ ማንነታችን አማራ ነው።
-TpLf is A terrorist part we need justice
-የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይላችን፣የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚኒሻ አባላት እንኮራባቹሃለን
-ዛሬ የነፃነታችን ቀን ነው
-ማንነታችን ለአብሮነታችን ምሶሶ ነው
-ቀና በል ወልቃይት ጠገዴ
-ለተገፋው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ድምፅ ለሆናችሁን ሁሉ እናመሰግናለን!
-ትህነግና የተደራጁ የትግራይ ሰፈራ ነዋሪዎች የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ትህነግ ለአማራው ሕዝብ ካለው ጥላቻና ማንፌስቶው የመነጨ ነው።
– “ራያ መሬቱ የትግራይ ህዝቡም ትግሬ ነው!” ያልሽውን ስትገረፊ ታወሪዋለሽ!!!
-ከትግራይ የሚመጣ ጥሩ ጎረቤት እንጅ አስተዳደር ፈፅሞ አንቀበልም!
-የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ወደ ቀደምት ማንነታችን እና አስተዳደራችን በመመለሳችን ደስተኞች ነን!
-ወልቃይት ውስጥ ያሉ የትነግ ቅሪቶች ባፋጣኝ ትጥቃቸውን እንዲያወርዱ እንጠይቃለን!
-የተከበረው የኤረትራ ወንድም ሕዝብ ተቋርጦ የነበረው የአማራ እና የኤርትራ ህዝቦች ሁለተናዊ ግንኙነት ስለጀመረ እንኳን ደስ ያለን!
-የማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ የፈጸሙት በጦር ወንጀል ይጠየቁ
-ሱዳን የመሸጉት የማይካድራ ጨፍጫፊዎች ተላልፈው ለህግ ይቅረቡ