>
9:35 pm - Tuesday March 21, 2023

የህወሀት ቁጥር አንድ አፈቀላጤ የአውራምባ ታይምሱ  ዳዊት ከበደ ታስሯል! (ቤላ ዳንኤል)

የህወሀት ቁጥር አንድ አፈቀላጤ የአውራምባ ታይምሱ  ዳዊት ከበደ ታስሯል!

ቤላ ዳንኤል

ትናንት ማታ 3፡00 ሰዓት አካባቢ ነው በፀጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው፡፡
ባለቤቱ እስካሁን ድረስ የት እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም፡፡ በቅርብ ወዳለ ፖሊስ ጣቢያ ብትሄድ፣ እስረኞች እዚያ እንዳደረ ቢናገሩም፣ መዝገብ ላይ ስሙ እንደሌለ ተነግሯታል፡፡
የህወሀት አንደኛው አፈቀላጤ የአውራምባ ታይምስ ሚዲያ ባለቤት እንዲሁም ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር የማፊያው አገዛዝ ተቃዋሚ ጋዜጠኞች እና ታጋዮችን ሲሰልል የነበረው “ጋዜጠኛ” ዳዊት ከበደ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ እርግጥ ሆኗል።
እንደምታስታውሱት ዳዊት ከበደ ፥ አጫሉ ከመገደሉ 3 ቀን ቀደም ብሎ “የግድቡን ርዕስ ሊያስቀይር የሚችል አንድ አዲስ አጀንዳ ጠብቁ። ከፈለጋቹ እንወራረድ!” ብሎ ነበር።
ይከሰታል ያለው ምን ይሆን?! ማን ነገረው?! እንዴት እንደዚህ እርግጠኛ ሆነ ?! ከማፊያው ጁንታ እና ሁለተኛው መንግስት ነኝ ሲል ከነበረው ከጃዋር ጋ ከነበረው ቅርበት አንፃር በደንብ ተጣርቶ ለህዝብ እንደሚገለፅ ተስፋ አደርጋለሁ!
ያንን አይነት አሰቃቂ ተግባር ያቀነባበሩት ሰዎች ግባቸው ከአጫሉ ህይወት ማለፍ ጀርባ በሚፈጠረው ትርምስ ላይ እንደሚሆን ምንም አያጠራጥርም። ያንን በማስታከክ በሕዝብ መካከል ቅራኔዎችንና ከባድ ግጭት በመፍጠር፣ በመንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር እና አገሪቱ ወደ ሌላ ዙር የፖለቲካ ቀውስ እንድትገበ ቀዳዳ ይፈልጉ የነበሩ ኃይሎች የተሳተፉበት ነው።
የአጫሉን ሞት ተከትሎ በርካቶች በማንነታቸው ተለይተው ተገድለዋል፣ ጥቃት ደርሶባቸዋል፣ ሀብት እና ንብረታቸው ተቃጥሏል፣ ብዙዎች ከመኖሪያ ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል። ያሰቡትን ያህል ማተረማመስ እና መንግስትን መገልበጥ ባይችሉም ፣ በጣም አሰቃቂ ጥቃቶች ተፈፅሟል።
Filed in: Amharic